ሸንቁጥ አየለ
በማህበራዊ ሚዲያዉ ላይ ሰሞኑን የተለቀቀዉን እና ወታደሮች በአማራ ማንነታቸዉ ጥቃት ደረሰባቸዉ የሚለዉን መረጃ እያነበብኩ በጣም ገረመኝ:: መገረምም ብቻ ሳይሆን ብዙ ጥያቄዎችም በህሊናዬ ተመላለሱብኝ:: ጠመንጃ የታጠቀ: በሰራዊት ክህሎት የሰለጠነ በሞት መሃከል ለመራመድ ቃል የገባ እሱ ሞቶ የህዝብ እና የሀገር ክብር ለማስጠበቅ ቃል የገባ ወታደር እንዴት በማንነቱ ሲጠቃ ዝም ይላል?
እንዴት ወታደር በማንነቱ ሲጠቃ ዝም ይላል? እረ ወዲያ ደስም አይልም! መግደል አድብቶ ማጥቃት እና የክብርን ጸጋ ማስመለስ ይገባል እንጅ ወታደር ሆኖ ተጠቅቶ ዝም ይባላል? ወታደር የሚኖረዉ ገሎ ለመሞት እንጅ ገሎ ለመኖር አይደለም:: በሞቱ የሌሎችን ክብር እና ሰላም አስጠብቃለሁ ብሎ የቆረጠ ወታደር በማንነቱ ሲዋረድ ምን ይሆን ብሎ ነዉ አንድ ወይ አስር ዘራፍ እያለ የማይገድለዉ?
ታጥቀህ? ሰልጥነህ? አላግባብ ሌላዉ በማንነትህ ሲያጠቃህ ዝም ትላለህ? ይሄ በጣም ያበሳጫል:: የምታበሳጨዉ ደግሞ አንተ ነህ::የሚያጠቃህ እማ እብሪተኛ ስለሆነ የሚያደርገዉን አያዉቅም:: ልክ አገር ሊወር የመጣ እብሪተኛ የሚያደርገዉን እንደማያዉቅ ሁሉ በስርዓቱ የሚደገፍ እብሪተኛም ሲያጠቃህ ምናልባትም እየሸለመህ ሊመስለዉ ይችላል:: እና ተጠቅተህ ዝም ትላለህ?
እረ አያሳምንም ! ይሄ ነገር በጣም የሚያናድድ ነዉ:: የተናደድኩት ደግሞ በናንተ በአማራነታችን ተጠቃን ባላችሁት ወታደሮች እንጅ በህዉሃት ወታደሮች አይደለም:: ጥጋበኛን ካልገደልከዉ ልክ እንደማይገባ ስለምታዉቅ መስሎኝ ወታደር የሆንከዉ? እብሪተኛን በመግደልም የህዝብና የሀገር ክብርን ለመጠበቅ ጨክነህ መስሎኝ ወታደር የሆንከዉ:: መረጃዎቹ እንደሚያመላክቱት ከሆነ አሁንም ህዉሃት ሰራዊት ዉስጥ በማንነታችን ጥቃት ይደርስብናል የሚል ወታደር ብዙ ነዉ:: ምን ትሰራለህ? ለምንድ ነዉ የማታድመዉ ታዲያ? አማራ በመሆኔ በወታደር ቤቱ ዉስጥ እየተበደልኩ ነዉ ብሎ የሚናገር ሰዉ እንዴት ነዉ ዉስጥ ዉስጡን እንደ ወታደር የማያድመዉ?
በጋራ አድሞ መግደል ባይቻል ግን በግል እየገደሉ መሞት በጣም ብዙ ነገሮችን ይለዉጣል:: ያንተንም ሆነ የሌሎች ወታደሮችን ክብር ያስጠብቃል:: ከፍ ሲል የኢትዮጵያን ህዝብ የዲሞክራሲ ጥያቄ ሂደት ያፋጥነዋል::ምክንያቱም እብሪተኛ አንድም ሆነ ብዙ ሲገደል ሌሎች እብሪተኞች ቆም ብለዉ ለማንሰላሰል ይገደዳሉ እና:: እንዴት ነዉ ነገሩ? እንዴት ወታደር በማንነቱ ሲጠቃ ዝም ይላል? አምስትም አስርም ሃያም እብሪተኛን በጅምላ በመረሸን እረ ጎራዉ ብሎ መፎከር ብሎም እየተታኮሱ እና ማንነትን እያስጠበቁ መሞት እኮ የወታደር የህይወቱ ግብ ነዉ::
የወታደር የህይወቱ ግብ እብሪተኛን እየገደሉ በክብር መሞት እንጂ በማንነቴ ተጠቃሁ ብሎ መሬት መቆርቆር እና አፈር መጫር አይደለም:: በአማራ ማንነቴ ተጠቃሁ ብሎ ማዘን በወታደር አያምርም::አርሶ አደር ተገፋሁ ብሎ መሬት ቢጭር እና ቢከፋ ያሳዝናል::መገፋቱም ያበሳጫል:: ወታደር በአማራ ማንነቴ ተጠቃሁ ሲል ግን ያናድዳል:: ያበሳጫልም:: የሚሞት ወታደር ምን ፈርቶ ነዉ እዚያዉ የሚያጠቃዉን እብሪተኛ ባገኘዉ ነገር እንገቱ ስር ወግቶት የማይሞተዉ?
አርሶ አደር ለማረስ ነዉና ጨክኖ የመግደል ክህሎት ስለሌለዉ ቢሸማቀቅ አይፈረድበትም:: ወታድር ግን በማንነቱ ተጠቅቶ: በዘሩ ተገፍቶ እና እብሪተኛ ጭንቅላቱ ላይ እንደተቀመጠበት እያወቀ ዝም ካለ ብሎም ተገፋሁ ብሎ መሬት ከጫረ ያናድዳል:: እኔ ተጠቃሁ በሚለኝ ወታደር በጣም ነዉ የምናደደዉ:: የማፍረዉም:: በሞቱ የሌሎችን ክብር ለማስጠበቅ የሚኖር ወታደር የራሱን ክብር እንዴት ማስጠበቅ ያቅተዋል?