አንድ ቀበሌን ወይም ኢትዮጵያን ነጻ ለማዉጣት ጉልበት ይጠይቃል

አንድ ቀበሌን ወይም ኢትዮጵያን ነጻ ለማዉጣት ጉልበት ይጠይቃል

ሸንቁጥ አየለ

 

አንድ ቀበሌን ወይም ኢትዮጵያን ነጻ ለማዉጣት ጉልበት ይጠይቃል
ሕገ ወጡ ክልል

ወያኔ ያቦካዉ መርዛማ ጭቃ ዉስጥ ቆመህ: ወያኔ የሰራዉን የህግ ማዕቀፍ እያጣቀስክ ስለምንም ነገር አትከራከር ማንንም ህዝብ አትዝለፍ:: በኢትዮጵያ ምድር ላይ የሚሆነዉን ነገር ሁሉ መወሰን የሚቻለዉ የምትቆምበት የክርክር ሜዳ አንተ ያበጀህዉ የምትነጋገርበት እና የምትከራከርበት ሁኔታ ብሎም በዉይይት እና በስምምነት ሊወሰን የሚችል አጠቃላይ ሀገራዊ ሂደት ሲኖር ነዉ::

ወያኔ የሰራዉን ክልል እያነሳህ እና እያጣቀስክ በማንኛዉም ነገር ላይ እከራከራለሁ ሀሳብ እሰጣለሁ ወይም ሰዉ አሳምናለሁ ብለህ ከተነሳህ ግን አንድ ግልጽ ያልሆነልህ ነገር አለ ማለት ነዉ:: እናም እራስህን መርምር::

በትክክል ወያኔን የምትቃወም እና የምትጠላ ጀግና ከሆንክ አንድ ነገር ወስነህ ተነሳ:: የወያኔ የሆነን ነገር ሁሉ አፍርሰህ እና ንደህ ተነስ:: የወያኔን አስተሳሰብ ናደዉ:: ሆኖም ከወያኔ የጭቃ ሜዳ ዉስጥ ገብተህ ክርክር እንዳትገጥም ከባድ ጥንቃቄ አድርግ::

በወያኔ የህግ ማዕቀፍ ዉስጥ ሆነህ ምንም ነገር እንዳታስብ:: ወያኔ የሰራዉን ክልል ሁሉ እንደሌለ ቆጥረህ በማሰብ ተነስ:: ይሄ አካባቢ ለዚያ ወይ ለዚህ ብሎ ወያኔ የሸነሸነዉን ሁሉ እርሳዉ:: ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ እንድትሆን የሚለዉን መርህ ይዘህ ተነስ::

በብሄርህ ልትደራጅ ትችላለህ ወይም በኢትዮጵያዊነት ልትደራጅም ትችላለህ አለዚያም እጅግ ከምታምናቸዉ ከሰፈርህ ልጆች ጋር ብቻ ሆነህ ወያኔ ለመደምሰስ ልትዘጋጅም ትችል ይሆናል:: አደረጃጀትህ ወያኔ ለመጣል ከሚደረጉ ታክቲኮች አንዱ ብቻ ነዉ:: የፍጻሜ ግብህ ግን በቅንነት መላዉን የኢትዮጵያን ህዝብ ለማዳን እና ሁሉም የሚስማማበትን አጠቃላይ ሀገራዊ መሰረት ለመፍጠር ቆርጠህ መነሳትህ ይሁን:: አባቶችህ የደከሙበትን መሰረት ወደ ታላቅ መሰረት የመዉሰድ ግዴታህን ለመወጣት ወኔ ካጣህ ግን ቀድመህ በወያኔ አስተሳሰብ ተሸንፈሃል ማለት ነዉ:: ወያኔ የሚፎክረዉ የቀደመዉን መሰረት ሁሉ ንጄዋለሁ ብሎ ነዉ::  ወያኔ በምቀኝነት የሚፏልለዉ ኢትዮጵያ የሚባለዉን ሀገር ወደ አለመኖር ጠርዝ ግፍቼዋለሁ ብሎ ነዉ::

ወያኔ የሰራዉን የተጨመላለቀ የክልል ጉዳይ የተወሳሰበ የጎሳ መርዛማ ጥላቻ በኢትዮጵያዉያን መሃከል እንዳለ ቁም ነገር አድርገህ አትዉሰድ:: በወያኔ መርዝ የተለወሱትን ሁሉ ከምድሪቱ ጠርገህ እና ደምስሠህ የመጣል ህሳቤን ይዘህ ተነሳ:: ጀግና ከሆንክ በቀበሌ ደረጃም ተዋጋህ ወይም በሀገር ደረጃም ተዋጋህ የጦርነቱ ድምዳሜ አንድ መስመር ላይ እንደሚገናኝ አትርሳ::

ሀገሩ መፈወስ አለበት:: ህዝቡ መዳን አለበት:: አንድን ቀበሌ ወይም አንድን ወረዳ ወይም አንድን ክልል ወይም ኢትዮጵያን በአጠቃላይ በጉልበት ከወያኔ እጅ ፈልቅቆ ለመዉሰድ ጉልበት ይጠይቃል:: ስለዚህ ዉጊያህ ስለአንድ ቀበሌ ወይም ስለ አንድ ክልል ሆኖ እንዳይወሰን ከመነሻህ ጥራት ባለዉ ሃሳብ ተንደርደር:: ኢትዮጵያን አድን ! የአባቶችህን ሀገር!!

ጀግነህ እና ታላቅ ሆነህ ተነስ:: ስለ ታላቂቱ የአባቶህ ሀገር ስለ ኢትዮጵያ ተነስ! አከናዉንም:: ኢትዮጵያን እጅህ ስታደርግ የምትወደዉን ሁሉ ታድናለህና:: ከዉጊያህ በፊት ግን የፍናፍንት ህሳቤ የሆነዉን የወያኔ ሃሳብ ሁሉ ረግጠህ ጣለዉ:: እንደቆሻሻም ቁጠረዉ::