ሸንቁጥ አየለ
የበቀለ ገርባ ሃሳብ አሁን ለምን በብዙ ሰዉ ጆሮ ገባ? ብዙ ጥያቄዎች በዚህ ሰው አቁዋም ላይ እየተነሱ ነው:: “ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ የበቀለ ገርባ የፖለቲካ ካምፕ ምን ያህል ማትረፍ አለበት ማለት ነዉ?” ሰሞኑን ኢትዮጵያዉያን እየጠየቁት ያለ ጥያቄ ነዉ:: “ኢትዮጵያን ለማፍረስ የበቀለ ገርባን ካምፕ ማን ወሳኝ አደረገዉ?” ሁለተኛዉ ኢትዮጵያዉያን የተወያዩበት ጥያቄ መሆኑ ነዉ::
ሆኖም ለብዙወቻችን የዚህ ሰዉ አቋም አሁን ገና ግልጽ ሆነልን እንጅ በቀለ ገርባ ኢትዮጵያ ትፍረስ ሲል በጣም ብዙ ጊዜ አሳልፏል። ከእስር ቤት የወጣ ሰሞን “በኦሮሚያ የሚኖሩ ሌሎች ዜጎች..” እያለ ኢትዮጵያዉያንን በአባታቸዉ ሀገር መጤ እና ሁለተኛ ዜጋ አድርጎ ኦሮሚያ የሚባለዉ ወያኔ የሰራዉ ክልል የሱ የግል ሀብቱ አድርጎ ሲዉረገረግ ነበር:: እንዲህ አይነት ቀልድ በሆነ የፖለቲካ ግሽበት የታወረ ግን በቀለ ገርባ ብቻ አይደለም:: ብዙዎች አሉ::
ኢትዮጵያ ስትፈርስ እሳቱ እኩል ሁሉም ላይ እንደሚነድ አልገባ ያለዉ በቀለ ገርባ እኛ የምንለዉ ካልሆነ: እኛ ብዙ ካላተረፍን ኢትዮጵያ ለመፍረስ እራሷን ታዘጋጅ ሲል ሰሞኑን ዝቷል:: እናም ይሄ ዛቻዉ የመጀመሪያዉ የመሰላቸዉ አንዳንድ ሰዎች አሁን በሰሙት ነገር እየተገረሙ ነዉ::
ኢትዮጵያን ለማፍረስ እነ በቀለ ገርባ በሚያቀጣጥሉት አቢዮት እሳቱ ሊነሳ ይችላል::እሳቱ ሲቀጣጠል ግን ደብቁኝ ማለት አይቻልም:: ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ወደ እሳቱ ተያይዘን ገብተን እነደምንቀጣጠል ማወቅ ይገባል::
እናም ነዲዱ እሳት ሊነሳ ይችላል:: መቃጠል ያለብት ከተቃጠለ ብኋላ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም::ስለዚህ በቀለ ገርባ ተስፋህን ቁረጥ!! ኢትዮጵያ ፈጽሞ የማትፈርስ ሀገር ነች:: ኢትዮጵያ የአባቶቻችን ርስት : የሁሉም ኢትዮጵያዉያን የጋራ እርስት ነችና ማንም አያፈርሳትም:: እሳቱ መነሳቱ ግን መልካምም ሊሆን ይችላል::በርካታ አራሙቻን በልቶ ሊያጠፋም ስለሚችል::
ለበቀለ ገርባም ሆነ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ለሚል ሁሉ ሊነገረዉ የሚገባ መልዕክት አንድ ብቻ ነዉ:: ይሄ አይነት ሀገር የማጥፋት ሀሳብ የተጠናወታቸዉን ሰዎች እና ቡድኖች በማሽሞንሞን ይመለሳሉ ብሎ ማሰብ ከንቱ ግምት ነዉ:: ሊነገራቸዉ የሚገባዉ መልዕክት አንድ ነዉ:: ኢትዮጵያ ፈጽሞ አትፈርስም የሚለዉ:: ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነዲዱን ማቀጣጠል ይቻል ይሆናል:: መቃጠል ያለብት ከተቃጠለ ብኋላ ግን ኢትዮጵያ የተባለች ሀገር በእሳት ዉስጥ ተረማምዳ እንደ ወርቅ ተፈትና ብሎም ነጥራ ትወጣለች:: የኢትዮጵያ የሽህ ዘመናት ልምዷ ይሄዉ ነዉ::