ከመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራሮች እና ደጋፊዎች ጋር የተደረገ ዉይይት:- ክፍል አንድ

ከመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራሮች እና ደጋፊዎች ጋር የተደረገ ዉይይት:- ክፍል አንድ

በዉይይቱ ላይ የተሳተፉ
1. ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ
2. ፕሮፌሰር ሀብተጊዮርጊስ ቸርነት
3. አቶ ስለሽ ጥላሁን
4. አቶ ዘመነ ምህረት (የመኢአድ ም/ፕሬዝዳንት)

በዉይይቱ ላይ የሚከተሉት አንኳር ነጥቦች ተነስተዋል
1-ለቀድሞ የመኢአድ አባላት እና ደጋፊዎች የትግል ጥሪ ቀርቧል::በተለይም በዉጭ ሀገር ያለዉ የመኢአድ አባላት እና አመራር ይሄን ብዙ መስዋ ዕትነት የተከፈለበት ድርጅት ትግሉ በድል እስኪደመደም ብሎም ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲያዊነት እና ብልጽግና እስክትራመድ በትግል ሜዳዉ ላይ ጸንቶ እንዲገኝ ጥሪ ቀርቦለታል:: ድል እዚህ እና እዚያ ቢረግጡት: ከድርጅት ድርጅት ቢዘሉት ሳይሆን ጸንቶ በመታገል ብቻ የሚገኝ የመስዋ ዕትነት ዉጤት መሆኑን ተወያዮቹ በተለያዬ መልክ አቅርበዉታል::

ከመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራሮች እና ደጋፊዎች ጋር የተደረገ ዉይይት:- ክፍል አንድ
ማሙሸት አማረ

2- በአሁኑ ሰዓት መኢአድ አዲስ የአደረጃጀት እና የአሰራራ ስርዓትን በመዘርጋት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑም ተገልጿል:: ከወያኔ ምርጫ ቦርድ የተሰዬመዉ የእነ ዶ/ር በዛብህ ጥቂት ስብስብ መኢአድን እንደማይወክል በስፋት ተብራርቷል::ምርጫ ቦርድ ለማስመሰል እና ዉዥንብር ለመፍጠር ልክ እንደ አየለ ጫሚሶ እነ ዶ/ር በዛብህንም መኢአድን ለመጥለፍ እንዳስቀመጣቸዉ በስፋት ተብራርቷል:: እነ ዶ/ር በዛብህ እና እነ ሙሉጌታ የመኢአድ እዉነተኛ አመራሮችን እየጠቆሙ ከ122 አመራሮች በላይ ማሳሰራቸዉ በዉይይቱ ላይ ቀርቧል::

3-በሰሜን አሜሪካ እነ ዶ/ር በዛብህ መጥተዉ በነበረ ጊዜ ሀሰተኛ እና ህጋዊ አመራር እንዳልሆኑ በመንገር እንዳባረሯቸዉ የመኢአድ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጭ ማህበር አመራሮች አብራርተዋል:: እነ ዶ/ር በዛብህም አፍ አዉጥተዉ አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ህጋዊዉ ተመራጭ መሆኑን እንደማይክዱ ለሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማህበር አመራሮች እንዳብራሩላቸዉ ገልጸዋል:: ሆኖም ዘወር ብለዉ ግን መኢአድን የማፍረስ የብልግና ስራቸዉን መቀጠላቸዉ በጣም እንዳሳዘናቸዉ የሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ አመራሮች ገልጸዋል::

4-ከሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማህበር ተወክለዉ የቀረቡት ተወያዮች በስፋት እንዳብራሩት ስልካቸዉንም ሆንም ሆነ አድራሻቸዉን ለእነ ዶ/ር በዛብህ ማንም ሰዉ እንዳይሰጥ እንዳዘዙ በተለያዩ መድረኮችም የእነ ዶ/ር በዛብህን ሸፍጥ እንዳጋለጡባቸዉ እንዲሁም እነዚህን ህጋዊ ያልሆኑ እና እና በወያኔ የተሰዬሙ ሰዎች የሰሜን አሜሪካን የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማህበር ፈጽሞ እንደማያዉቃቸዉ ተብራርቷል::

5-ከ483 ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች ዉስጥ በ477 አባላት የተመረጠዉ ፕሬዝዳንት ማሙሸት አማረ እና ከእሱ ጋር ያለዉ አመራር ብቻ እዉነተኛ እና ህጋዊ የመኢአድ አመራራ መሆኑ በጥልቀት ቀርቧል::

6-በአሁኑ ሰዓት አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ህጋዊ አመራር መሆኑን አብዛኛዉ የመኢአድ አባላት እና ደጋፊ ከዉጭ ሀገር እስከ ሀገር ቤት ጠንቅቆ እንደሚያዉቅ በዉይይቱ ላይ ተነሷል:: ፕሬዝዳንቱ ማሙሸት አማረ በእስር ቤት ቢሆንም አሁንም ህጋዊዉ የመኢአድ አመራር አቶ ማሙሸት አማረ ብቻ መሆኑ በዉይይቱ በአትኩሮት ቀርቧል:: የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ወያኔ ከገባ ጀምሮ ከአስራ አራት አመታት በላይ እስር ቤት በወያኔ የሚማቅቀዉ ወያኔዎች የዚህ ጀግና ጥንካሬን እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰለፈዉን የመኢአድ ሀይል ሁሌም ስለሚፈሩ መሆኑ በዉይይቱ ተዳሷል::

7-መኢአድን ወያኔ ከማንኛዉም ተቃዋሚ በላይ የሚጠላዉ እና የሚፈራዉ ድርጅት ስለሆነ ድርጅቱን አፍርሶ ብቻ ሳይሆን የተወዉ ከ122 በላይ አመራሮች በላይ እና አባላቱን እያሳደደ ማሰሩን ተወያዮች አብራርተዋል:: በተመሳሳይም ወያኔ በአንድነት እና በቀድሞዉ ቅንጅት ላይ ምን አይነት የደባ አሰራር ተከትሎ ፓርቲዎቹን እንዳፈራረሳቸዉ ቀርቧል:: ሆኖም በዉይይቱ ላይ አጽኖት የተሰጠዉ መኢአድን እንደ ቅንጅት እና እንደ አንድነት ፓርቲ ማፈራረስ ፈጽሞ እንደማይቻል በስፋት ተብራርቷል::

8-በመኢአድ ላይ የሀሰት ዉዥንብር እና ስም ማጥፋት የሚያደርጉ ተቃዋሚ የሚመስሉ አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንዳሉ ተነስቷል:: በዚህም የመኢአድ ደጋፊዎች እና አባላት ላይ ዉዥንብር እንደሚያከናዉኑበት በዉይይቱ ላይ ቀርቧል:: መኢአድን ለማጥፋት ወያኔ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ነን የሚሉ አንዳንድ ሀይሎችም መኢአድን በእጅጉ እያጠቁት እንደሆነ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቦበታል:: ሆን ተብሎ መኢአድ ፈርሷል የሚል ፕሮፖጋንዳ ተቃዋሚ በሚመስሉ አስመሳዮች እንደሚነዛበትም ተነስቷል:: የመኢአድ ደጋፊዎች እና አባላት ይሄን መሰሉን አሉባልታ እና ሀሰተኛ ወሬ ነቅተዉ መጠበቅ እንዳለባቸዉ ተገልጿል::

9-በዉጭም ሆነ በሀገር ቤት ያለዉ ህዝብ የመኢአድን ተጋድሎ እና ሁኔታ ያለመረዳት ነገር እንዳለ ቀርቧል::ለዚህም ዋናዉ ምክንያት የሚዲያ አለመኖር ጉዳይ መሆኑ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል:: የመኢአድን ድምጽ ለማፈን ነጻ የሚዲያ አካላት ነን እያሉ የሚናገሩት ሀይሎች ሳይቀር (የአሜሪካ አማርኛ ድምጽ ጭምር) ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከፍተኛ ማግለለ በመኢአድ ላይ እንደሚያደርጉ ተወያዮቹ በተለያዬ ሁኔታ አቅርበዉታል::

ከመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራሮች እና ደጋፊዎች ጋር የተደረገ ዉይይት:- ክፍል አንድ10-አንዳንዶች የቀድሞዉ መኢአድ እያሉ የሚናገሩት ንግግር ስህተት መሆኑን ተብራርቷል::የቀድሞዉ ወይም የአሁኑ የሚባል መኢአድ የለም::መኢአድ አንድ ነዉ:: ትናንትም ዛሬም ወደፊትም አንድ መኢአድ ነዉ ያለዉ::

11-ማሙሸት ታሰረ: ፕሮፌሰር አስራት ታሰሩ መሪዎች ታሰሩ ወይም ሞቱ የሚለዉ ሀሳብ መኢአድን ሊያፈርሰዉ አይገባም::መሪ ቢሞትም ወይም ቢታሰርም ሁሉ አባላት እና ደጋፊ መሪ ሆኖ ድርጅቱን ማስቀጠል አለበት:: መሪ ማለት አንድ ግለሰብ ብቻ ነዉ የሚለዉ ባህላችን ሊለወጥ ይገባል:: እንዲሁም መሪዉ ሲታሰር ወይ ሲሞት ከትግል የማፈግፈግ ባህላችን መለወጥ እንዳለበት እና ሁሉም አባላት/ደጋፊዎች በጋራ መሪ መሆን እንዳለባቸዉ ግንዛቤ ሊያዝ እንደሚገባዉ ተብራርቷል::

12-በወያኔ ፈቃድ የሚደረግ ትግል የለም::የአንድ ድርጅት መሪዉ ሲታሰር ወይም ወያኔ አንድ ድርጅት ፈርሷል ብሎ ሲያዝ ማፍረስ: ምርጫ ቦርድ ፈቃድ ነሳሁህ ሲል የወያኔን ፈቃድ ተከትሎ ድርጅትን ማፍረስ ነዉር ነዉ:: መኢአድን ምንም አይነት ምድራዊ ሀይል አያፈርሰዉም::መኢአድ የተቋቋመዉ ኢትዮጵያን ነጻ ሀገር ዲሞክራሲያዊት እና የበለጸገች ለማድረግ ነዉ:: ይሄም ትግል የሚደረገዉ በወያኔ ፈቃድ አይደለም:: ፕሮፌሰር አስራትም ሆኑ ኢንጂነር ሀይሉ ሻዉል ወይም አሁን ያሉ የመኢአድ ጀግኖች ወደ ትግል የገቡት የወያኔን ፈቃድ ለማሟላት ሳይሆን ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰዉን ግፍ ለማስቆም ነዉ:: ስለዚህ መኢአድን ማንም ሊያፈርሰዉ አይችልም:: መኢአድ አሁንም ህያዉ ሆኖ እየተጠናከረ ያለ ድርጅት ሲሉ ተወያዮቹ አስምረዉበታል::

13-መኢአድ አንድ ነዉ:: ትናንተም  ዛሬም ነገም መኢአድ ነዉ:: በፈተና ዉስጥ የሚጓዝ ጽኑ ድርጅት ነዉ:: ብዙ ጀግና ታጋዮች የተሰዉበት: አሁንም በርካታ ጀግኖች መስዋዕትነት እየከፈሉበት ያለ ድርጅት ነዉ:: ስለዚህ የመኢአድ አባላት: አመራር እና ደጋፊ የነበራችሁ ሁሉ ወደ ትግል ሜዳዉ ተሰባሰቡ:: አዳዲስ የትግል ሀይሎችም ወደ መኢአድ ታዛ በመሰባሰብ ህዝባችንን እንታደግ የሚል ጥሪ ቀርቧል:: በተያያዥም የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ለማገዝም እና ትግሉ ድል ይመታ ዘንድ ለማስቻል በአሁኑ ሰዓት መኢአድ ስትራቴጅ ነድፎ : አዲስ የአደረጃጀት እና የአሰራራ ስርዓትን በመዘርጋት ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑም ሰፋ ተደርጎ ተብራርቷል::

 

ከሞረሽ ወገኔ ሬዲዮ ጋር ያደረጉትን ዉይይት ከታች ያለዉን ምስል በመጠቆም እንዲያዳምጡ ተጋብዘዋል

https://www.youtube.com/watch?v=gHoRZStE1qE