ወያኔ በአማራው ላይ የሚፈጽመዉን አሰቃቂ ግድያ በረቀቀ መልኩ ቀጥሎበታል

ወያኔ በአማራው ላይ የሚፈጽመዉን አሰቃቂ ግድያ በረቀቀ መልኩ ቀጥሎበታል

 

በወያኔና በዘረኛ ተከታዮቹ የተጨፈጨፉ ለጋ ህጻናት

ወያኔ በአማራው ላይ የሚፈጽመዉን አሰቃቂ ሁዋላ ቀር ግድያ በግልጽና በድብቅ በረቀቀ መልኩ ቀጥሎበታል። ኢትዮጵያን ለመበታተንና ትንንሽ ነገዶችን ወደ ባርነት ለዉጦ ያላቸዉን የተፈጥሮ ሃብት ያለ ማንአለብኝነት ለመዝረፍ ያሰፈሰፈው ወያኔ አሁን ደሞ ሌሎች ጸረ ኢትዮጵያ ክፍሎችን በማስታጠቅና በመምራት ሰላማዊያን የአማራና የኦሮሞ ነገዶችን በመጨፍጨፍ ላይ እንደሚገኝ የተለያዩ የሚታመኑ ምንጮች በማሳወቅ ላይ ናቸው።
ዓማራው ለሰላምና ለኢትዮጵያ አንድነት ሲል ለ፪፮ ዓመታት የተፈጸመበትን ግፍ በትእግስትና በብልሃት ገድቦት ቢቆይም ወንጀለኞቹ ወያኔና ሎሌዎቹ ይህንን ቅዱስ መንገድ አልወደዱትም። እንዲያዉም እንደፍርሃት ሳይቆጥሩት አይቀሩም።

የወያኔ ኑሮ የተመሰረው በኢትዮጵያዉያን ስቃይና ደም ላይ ሆኖአልና፦ ስለዚህ ሁሉም ቁርጡን አዉቆ ከእንግዲህ ከወያኔና ከባሪያዎቻቸው ቅጥረኛ ነፍሰገዳዮች እራሱንና ቤተሰቡን ይጠብቅ።

ከብራና ሬዲዮ ያገኘነዉን በቅርብ ጊዜ የተፈጸመውን ግፍ ከዚህ በታች ስለአካተትነው አንብበው ለህዝብዎ የሚያስቡና የሚቆረቆሩ ከሆነ ከተበዳዩ የአማራ ህዝብ ጎን እንዲቆሙና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ ጥሪ ተደርጎልወታል።

 

By Muluken Tesfaw (Branna Radio)

በቤኒሻንጉል ልዩ ኃይል ፖሊስ እገዛ ከ50 በላይ ዐማሮች ሲገደሉ ወደ 400 የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል፤

ችግሩ የተፈጠረበት ቦታ- ከማሽ ዞን፣ በሎጅጋንፎይ ወረዳ፣ በሎደዴሳ ቀበሌ

ቀን፤ ከጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ

መነሻ ምክንያት፤ የክልሉ ልዩ ኃይልና በወረዳው አመራሮች አስተባባሪነት የዐማሮችን ንብረት መዝረፍ እየተለመደ እንደመጣና በዚህም ምክንያት አልፎ አልፎ ግጭት ይፈጠር ነበር፡፡ በሎንደዴሳ ቀበሌ የዐማራ ንብረት ለማውደም የሄደ የጉምዝ ተወላጅና ባለንብረቱ ሰው መካከል ጠብ ተነሳ፡፡ በዚህ መካከል ሊዘርፍ የሄደው ሰው ይሞታል፡፡ ይህን ጊዜ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ኖኖ እና ወ/ሮ ጥሩነሽ እንዴት ዐማራ የእኛን ሰው ይገድላል! በሚል ቁጭት የልዩ ኃይል ፖሊሱን በማስተባበር በዐማሮች ላይ ጀምላ ጥቃት መድረስ ጀመረ፡፡

ውጤቱ- በቀበሌው ከ2000 በላይ አባውራዎች ሲኖሩ አብዛኛዎቹ ከሳር የተሠሩ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲቃጠሉ የቆርቆሮ ጣራ ያላቸው ብቻ ናቸው የተረፉት፡፡ በዚህም ከ400 በላይ የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡
የሰው ሕይወት፤ የተለያዩ ሰዎች የተለያየ ቁጥር ቢናገሩም እስካሁን ከ50 በላይ ሰው እንዳለቀ ያነጋገርናቸው ገልጸውልናል፡፡ አስከሬን በየቦታው ወዳድቆ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን አልተነሳም፡፡ አስከሬን ለማንሳት የሄዱ ሰዎች ተከልክለዋል፡፡ በጅምላ በጉድጓድ የተከማቸ አስከሬንም እንዳለ ተናግረዋል፡፡ መትረፍ የሚችሉ ሰዎች ከአስከሬን ጋር አብረው በአንድ ጉድጓድ በመጠራቀማቸው ሕይወታቸው እንዳለፈም ተናግረዋል፡፡ አቶ አልማው የተባለ የቀበሌው ነዋሪ በሕይወት ከአስከሬን ጋር ወደ ጉድጓድ በመጣሉ አብሮ ሊሞት እንደቻለ ምስክሮች ገልጸዋል፡፡

ከ300 የሚበልጡ ሕጻናትና ሴቶች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም፡፡ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ወደ አካባቢው የደረሰ ቢሆንም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ኖኖ ከእኛ አቅም በላይ አልሆነም እያለ እየመለሰ እንደሆነም ነግረውናል፡፡
ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አስከሬኖች አልተነሱም፡፡ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም ሊያሻቅብ እንደሚችል ነግረውናል፡፡