የዓማርኛ ንግግር ስህተቶች
ትክክል √ | ስህተት Χ |
ምን አልክ? | ምን እያልክ ነው ያለኸው? |
እኔ የምለው | እኔ እያልኩ ያለሁት |
ሃሳብ | ህሳቤ |
የሚታወቁት/የምናዉቃቸው | እዉቅና ያገኙት |
መታደስ | ህዳሴ |
ምሳሌ | ተምሳሌት |
መልስ ሰጥተዋል | ምላሽ ሰጠዋል |
መጣሁ | መጣሁኝ |
ጅምር የተጀመረው የጀመርነው | ጅማሮ |
ተቀባይነት | ቅቡልነት |
ሰዉነት | ሰብአዊነት |
አለሁ | አለሁኝ |
ሄድኩ | ሄድኩኝ |
መጣሁ ወይም እየመጣሁ ነው | እየመጣሁኝ ነኝ |
ዓይነ ዉሃው አላማረኝም | የዓይኑ ቀለም አላማረኝም |
ከሙከራ/ከልምድ | ተሞክሮ/ተመክሮ |
ሃሳቡ ለህዝብ እንዲሰራጭ | ህሳቤው ለህዝብ ተደራሽነት እንዲኖረው |
ማዳበሪያው ለገበሬው እንዲደርሰው | ማዳበሪያው ለገበሬው ተደራሽ እንዲሆን |
ማስካካት | ማሽካካት |
ሰንደቅ ዓላማ | ባንዲራ |
የግድ ነው/ግዴታ ነው/እንገደዳለን | ግድ ይላል |
ማሰላሰል | ማንሰላሰል |
እንጥፍጣፊ | እንጭፍጫፊ |
ቢላዎ | ቢላ |
አስበን/አስበንበት/ከግምት ዉስጥ በማስገባት | ታሳቢ አድርገን |
ይሁን ወይም እሺይ | አሉታ |
አይሆንም ወይም እምቢ | አወንታ |
ጎታ | ጎተራ |
አስገራሚ ነገር | ገራሚ ነገር |
ከግምት ዉስጥ አስገብተን | ታሳቢግምት አድርገን |
የምንቀበለው/የምንስማማበት | ቅቡልነት ያለው |
የማንቀበለው/የማንስማማበት | ቅቡልነት የሌለው |
ተቀባይ የሌለው የማንቀበለው የማንስማማበት | ቅቡልነት የሌለው |
መተዳደር | መስተዳደር |
መተዳደሪያ | መስተዳደሪያ |
አስተዳደር | መስተዳደር |
አስተዳዳሪ | መስተዳድር |
ተዳዳሪ | ተስተዳዳሪ |
ክብር (ከበረ አስከበረ አክባሪ ተከባሪ) | አክብሮት |
ጥቅም | ጠቀሜታ |
የምናቃቸው ወይም የሚታወቁ | እዉቅና ያገኙ |
ያመለክታል | ያመላክታል |
ታማኝ ወይም የሚታመን | ተአማኝነት ያለው |
የማይታመን | ተአማኝነት የሌለው |
መልስ ሰጠዋል | ምላሽ ሰጥተዋል |
ክብር | አክብሮት |
እናከበረዋለን | አክብሮት እንሰጠዋለን |
አናከብረዉም | አክብሮት አንሰጠዉም |
አናከብረዉም | ክብር አንሰጠዉም |
ክብረ ቢስ ነው ወይም ወራዳ ነው | አክብሮት የሚሰጠው አይደለም |
ሃሳቡን አከብራለሁ | ለሃሳቡ ክብር አለኝ |
ንግግር:- ለአንድ ውይም ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚደረግ የቁም ነገር ንግግር
ወሬ:- የተረጋገጠም ይሁን ያልተረጋገጠ ተራ ወሬ ማዉራት
One thought on “የዓማርኛ ንግግር ስህተቶች”
Please leave your comments