ድርጊቶችን ባግባቡ መግለጽ
ጠላ ይጠመቃል | ገንፎ ይገነፋል |
ጠጅ ይጣላል | አረም ይታረማል |
አረቄ ይወጣል | ቅቤ ይነጠራል |
እሸት ይጠረጠራል | ንፍሮ ይቀቀላል |
ፈረስ ይጋልባል | ቆሎ ይቆላል |
በቅሎ ይሰግራል | እንጀራ ይጋገራል |
ስጋ ይቆረጣል ይዘለዘላል | ሎሚ ይመጠጣል |
ዉሃ ይቀዳል | እንጨት ይፈለጣል ወይም ይሰበራል |
አጥር ይታጠራል | በቆሎ ይጠበሳል ውይም ይቀቀላል |
ድንጋይ ይካባል | ማሺላ ይቆረጣል |
አብሲት ይጣላል | ጤፍ ይታጨዳል |
ወጥ ይፈላል | ሸንኮራ አገዳ ወይም ጥንቅሽ ይመጠጣል |
ሙቅ ይሞቃል | አልጋ ይነጠፋል |
ነጋሪት ይጎሰማል | በገና ይደረደራል |
ከበሮ ይመታል | ዳቦ ይደፋል |