ታሪክን እወቁ ያለአቅማችሁ አትንጠራሩ!!

 

ዶሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ

እንደ አያት ቅድመ አያቶቻችን ጥንታዊ ወግና ልማዳችንን ወኔን ተላብሠን ማንነታችንንና አገራችንን ማስከበር ሲገባን ወኔው ከድቶን የጠላት መሣሪያና መሳለቂያ ሆነን ብንገኝም በተደጋጋሚ የተሠነዘሩትን የእነ ተኮላ ሐጎስንና መሰሎቻቸውን ፍሬ ቢስ ፅሁፎች ከተመለከትን በኋላ፣ የመጣበትን የማያውቅ የሚሄድበትንም ለማወቅ ሥለሚያዳግተው ያለፍንበትን ታሪክ መቃኘት ግዴታ ሆኖብናል። ሥለሆነም ከዚህ በታች ያለውን እነ ተኮላ፣ መለስ፣ ሠየ፣ አብርሃም ያየህ፣ ገብሩ አስራት፣ አረጋዊ በርሄም ሆኑ ሌሎቹ ትግሬዎች የሚኩራሩበትን ንግስና የሌለዉን ወይም የማይገባዉን የትግራይ መሳፍንት ሁለት ምእተ አመት የማይሞላ አጭር የዘር ግንድ ወይም የሠባት ትውልድ ታሪክ ከሥር ከመሠረቱ ፈልፍለን በማውጣት ማንነታቸውን ማሳየት ተገደናል።

ከታሪክ እንደተገነዘብነው ቀይ ህንዶች (Red Indians) አንዲት ዛፍ ለመቁረጥ አያሌ የሀገር ሽማግሌ መክሮበት እሥከ ሰባት ትውልድ አንዳችም ጣጣ ያለማስከተሉን ከተገነዘቡ በኋላ ነው። እኛ ባለመታደል እንኳንስ የዛፍ መቆረጥ ከሰባት ትውልድ በኋላ በአካባቢ ተፈጥሮ ላይ የሚያስከትለውን መገንዘብ ይቅርና በዛሬው ትውልድ ላይ ሆን ተብሎ የሚፈፀመው ደባ ሊያስከትል የሚችለውን የባሠ መዘዝ በውቅቱ ተገንዝበን “ሣይቃጠል በቅጠል” ለማጥፋት ወይም ለማክሸፍ አለመቻላችን ነው። የተወሰኑ ዓመታት ወደኋላ መለስ ብለን የትግሬ የዘር ግንድ ሲወርድ ሲዋረድ እንዴት ተያይዞ እንደመጣና አሁን ለምንገኝበት ሁኔታ እንደዳረገን እንመልከት ።

ራስ ሥሁል ሚካኤል

ካሳ ምርጫ (አፄ ዮሃንስ)

ሹም አጋሜ ወልዱ
ወ/ሮ ታቦቷ
ቃለ ክርስቶስ
ወ/ሮ ወርቅዉሃ
ሹም አጋሜ ምርጫ ወ/ሮ ሥላሥ ድምፁ ትልቁ ራስ አርአያ ድምፁ
ራስ መንገሻ
ራስ ሥዩም
ራስ አርአያ ራስ መንገሻ ወለተ እስራኤል አልማዝ አስቴር
ራስ ጉግሳ አርአያ
ድጃች ኃ/ሥላሴ ጉግሳ

ሥሁል ሚካኤል

ከዐፄ ይኩኖ አምላክ ዠምሮ እስከ ዐፄ ኢዮአስ (1262-1761) ድረስ ከሰለሞንና ከንግሥት ሳባ የሚለዱት ነጋሢያን በሕጋዊ መልክ ከአባት ወደልጅ፣ ልጅ የሌለ እንደሆነ ወደ ወንድም ልጅ፣ ብዙ ልጆች ካሉ ለፈቀዱት እየተላለፈ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ ነበር።ታዲያ በዚህ ወቅት የዐፄ ዮሐንስ ቅድመ ቅድመ አያት የሆነው ሥሁል ሚካኤል በዐፄ ዳግማዊ እያሱ ጊዜ (1715-1747) ከትግሬ ተምቤን ወደ ጎንደር ቤተ መንግሥት በመምጣት ለንግሥቲቱና ለንጉሡ ገፀ በረከት ለመኳንንቶቹም ሥጦታ በማቅረብ የንጉሡ የዳግማዊ ኢያሱ ባለሟል ሆነ። ራሥ ወልደ ልዑል በ1759 ዓ.ም. ከሞቱ ወዲህ በ1760 ዓ.ም. በዐፄ ኢዮአስ ጊዜ ራሥ ተብሎ የእንደራሴነቱን ሥፍራ ያዘ። ዳግማዊ እያሱ የዐፄ በካፋ (1686-1723) እና የምንትዋብ ልጅ ሲሆኑ ከኦሮሞ ባለቤታቸው ከውቢቱ ኢዮአስን ወለዱ። ኢዮአስ ከአማራና ከኦሮሞ ነገሥታት የተወለደና ሁለቱን ወገኖች አንድ በማድረግ ላይ የነበረው ወጣት ንጉሥ ነበር። ነገር ግን ሥሁል ሚካኤል ለእንደራሴነት ያበቃውን ንጉሥ ኢዮአስን ለእናቱ ኦሮሞ ወገኖች ወግኖ ዐማሮቹን ያባቱን ወገኖች እንዲወጋ ካደረገ በኋላ በመጨረሻም የንጉሡን ህይወት በማጥፋት ስልጣኑን በሚከተለው መንገድ ወስዷል።

(ሀ) ንጉሥ ኢዮአስ በአማሮቹና በኦሮሞዎቹ ጠብ ጊዜ ተጨንቀው “ጠቡን ያበርድልኛል” ብለው በመጀመሪያ ላይ ለሥሁል ሚካኤል ሥልጣን አሥጨበጡ። ሥሁል ሚካኤል እንደቅፅል ሥሙ በዕውነትም ሹል ሥለነበረ በዘዴና በውስጠ ተንኮል በቅድሚያ ከኦሮሞዎቹ ጋር የህብረት መልክ አሳይቶ አማራዎቹን ከአሥጠቃና ራሥ ተብሎ ሥልጣን ጠቅልሎ ከጨበጠ በኋላ ቀጥሎ በኦሮሞዎቹ ላይ ተነሥቶ በይፋ ተጣላ። ለንጉሡም “ሄደን በመንግሥትዎ ላይ የሸፈቱትን (ኦሮሞዎች) እንውጋ” ቢላቸው “እምቢ” ብለው ቀሩ። ሥሁል ሚካኤል ኦሮሞቹን ሄዶ ወጋ። አሁን የአባቱንና የእናቱን ወገኖች ያጣው ንጉሥ ብዙ ባለሟልም ሥላለቀበት መካሪ አልባና ደካማ አድርጎ ያሥቀረዋል።

(ለ) ወደ ቤተመንግሥት ሠው ልኮ በእልፍኛቸው እንዳሉ ንጉሡን ኢዮአስን በሻሽ አሳንቆ ግንቦት 8 ቀን 1761 ዓ.ም. አሥገደለ። ሥልጣንም በእንደራሴው በሥሁል ሚካኤል እጅ ገባ። ነገር ግን ሕዝቡ የንጉሥ የዘር ግንድ የሌለውን ሥሁል ሚካኤልን በመሪነት ተቀብሎ እንደማይከተለው ሥለተረዳ ለግዛት የሚመቸውን የንጉሥ ዘር ያለውን የሠባ ዓመቱን ሽማግሌ የበካፋን ወንድም ዮሐንስን አነገሠ። ከራስ ሥሁል ሚካኤል እስከ ታናሹ ራስ ዐሊ ድረስ ያለው ጊዜ (1762-1845) ዘመነ መሣፍንት ተባለ። መሣፍንቱም በጦርነት እንደምንም ብለው የእንደራሴነቱን ሥልጣን ሲጨብጡ የነጋሢነት ዘር እንደሌላቸው ራሳቸው በማመን “ብንነግሥም ሕዝቡ አይቀበለንም” በሚል ሥጋት ልባቸው የፈቀደውን አንዳንድ የነጋሲ ዘር እያነገሡ እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ መነሣት ድረስ ቆዩ። የሥሁል ሚካኤል ሥልጣን ብዙም ሳይቆይ በ1764 ዓ.ም በላስታና በአማራ ገዥዎች በእነ ደጃዝማች ወንድወሰን ተነጠቀ። አንድ ዓመት በግዞት እንዳለ ደጃዝማች ወንድወሰን “አገርህ ግባ” ብሎ ፈቅዶለት በአድዋ 7 ዓመት ከቆየ በኋላ በ1772 ዓ.ም. ሞተ።

አፄ ዮሐንስ!

(ሀ) አንበሳው ቴዎድሮስ የእንግሊዝን መንግሥት ማሥጋቱን ሪቻርድ ፓንክርስት በተለያዩ ፅሁፎቹ ገልፆታል። ይኸውም በሱዳንና በግብፅ የጥጥ ተክል በሠፊው ታሥፋፋ የነበረችው ቅኝ ገዧ እንግሊዝ የአባይን ውሃ ለመሥኖ አገልግሎት ለዘለቄታ ለመጠቀም የማትችል መሆኗ ሥላሳሰባት ነበር። በቋፍ የነበረው ትምክህተኛው እንግሊዝ “አፄ ቴዎድሮስ ያጋዟቸውን ጥቂት የእንግሊዝ ሠላዮች ለማሥፈታት” በሚል ሠበብ ቴዎድሮስን ለመውጋት እንዲመቸው የቴዎድሮስን ባላንጣ ባላባቶችና መኳንንቶች በተለያዩ ሽንገላዎች የወርቅና የጦር መሣሪያ ድርጎ ለመሥጠት በማባበል እንዲያብሩለት ተማፀነ።

የሸዋው፣ የወገራ፣ የሠሜን፣ የጎጃም፣ የዳሞት፣ የአገው፣ የዐማራው፣ የላስታው የአውሳው፣ የአዳሉ (የአፋሩ) ወዘተ ባላባቶች አፄ ቴዎድሮስን ቢጠሉና ቢፈሩም ከፈረንጅ ወግነው በእሳቸው ላይ እንደማይነሱ በመግለፅ የጄ/ ናፒየርን የእንግሊዝ ሠራዊት መሪ ቅሥም ይሠብሩታል። ከሥንዴ መካከል እንክርዳድ ሥለማይጠፋ ጥቂት ባላባቶች ከአገር አንድነትና ከጥቁር ድል የነጭን ድል አድራጊነት በመምረጣቸው ከእንግሊዝ ጋር ተባብረዋል። እነኚህ ለእንግሊዝ ያደሩት ባላባቶች የእንደርታው ባልጋዳ አርአያ፣ የአጋሜው አረጋዊ ሰባጋዲስ እና ካሣ ምርጫ (አፄ ዮሐንስ) ነበሩ። በብዙ ሽህ የሚቆጠር የጋማ ከብትና የእርድ ከብት በመሰብሰብ፣ ኮተት በመሸከም መንገድ በመምራት ከዙላ እስከመቅደላ በማጀብ ወራሪውን አቅፈው ደግፈው የኢትዮጵያን ክብር ከማስደፈራቸውም ባሻገር ተተኪ የሌለውን ቴዎድሮስን ያሥገደሉ የሀገሪቱን ቅርስና ንብረት ያሥዘረፉ ናቸው።

(ለ) አፄ ዮሐንስ በምንደኝነት ጀግናው ቴዎድሮስን በእንግሊዝ ወራሪ ኃይል ለማስገደል ባደረጉት ትብብርና አሥተዋፅዖ በተሸለሙት መሣሪያ የኤርትራን ድንበር የደፈረውን ኢጣሊያንን መውጋት ቀርቶ ለማስፈራራት እንኳን አልቃጣቸውም። ይልቁንም “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ” እንደሚባለው ምንም ያልበደላቸውን የአማራውን ሕዝብ በጎጃም፣ በቤጌምድር፣ በወሎ ሲያጋዩትና ሲሰይፉት ቆይተው ሸዋንም ሊድርቡ ሲቃጡ በአንድ ለጋ የጦር አበጋዝ በበሻህ አቦዬ ጦር ደብረ ብርሃን ላይ መገታታቸው ይታወቃል። በተለይ ደግሞ በክርምቱ በነሐሴ ወር በ1880 ዓ.ም. “ድርቡሾችን እወጋለሁ” በሚል ሠበብ ወደጎጃም በመዝመት ጎጃም በሙሉ እንዲዘረፍ አዘው ወታደሮቻቸው ከዳር እስከዳር በጎጃም ተሠማርተው ሠውንም አጋዩት። ከብትም ሀብትም ዘረፉ።

ከብቷ የተዘረፈባት አንዲት የጎጃም አልቃሽም

“በላይኛው ጌታ በባልንጀራዎ
በቅዱስ ሚካኤል በጋሻ ጃግሬዎ በጽላተ ሙሴ በነጭ አበዛዎ
ጎጃምን ይማሩት ፈሪም አንልዎ”ብላ ገጠመች።

(ሐ) አፄ ዮሐንስ ከአፄ ቴዎድሮስ በኋላና ከአፄ ዮሐንስ በፊት የነገሠውን የራሳቸውን እህት ባል አፄ ተክለ ጊዮርጊስን ወግተው ከማረኳቸው በኋላ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ አይነት ምርኮኛውን ንጉሥ ዓይናቸውን በጋለ ብረት ጎልጉለው አሠቃይተው መግደላቸው አሌ የማይባል ሃቅ ነው።

(መ) ፅኑ ክርስቲያን በመባል የሚታወቁት አፄ ዮሐንስ ቁጥር ሥፍር የሌለው ቤተ ክርስቲያናትና ካህናት በጎጃምና በወሎ ሲያቃጥሉ እሥላሙንም ሃይማኖት ሲያስቀይሩ፣ እምቢ ያለውንም ሲሰይፉ ዳዊት ይደግሙ ነበር። አፄ ምኒልክ እሥከነገሱ ድረስ እሥላሙ ዜጋ በገዛ ሀገሩ መሬት አልባ ያደረገውን ደንብ የደነገጉም አፄ ዮሐንስ ነበሩ።

(ሠ) የሱዳኑ የመሃዲ ሠራዊት የእንግሊዝን የወራሪ ጦር አበጋዝ የጄ/ ጎንደንን አንገት ቀንጥሶ ብዙዎቹንም እንዳያመልጡ ወጥሮ በያዘበት ጊዜ እንግሊዝ አፄ ዮሐንስን እንዲያግዙት ይጠይቃቸዋል። እርሳቸውም ሠራዊት ልከው ከእንግሊዝ በማበር የሱዳንን መሃዲስቶች ወግተው የተከበቡትን የእንግሊዝና የግብፅን ሠራዊት አሥለቅቀው በኢትዮጵያ በኩል ወደግብፅ እንዲሄዱ ያደርጋሉ። አፄ ዮሐንስ ለቅኝ ገዡ ለእንግሊዝ መንግሥት ያላቸውን ከፍተኛ ታማኝነትና ታዛዥነት ለማሳየት ሲሉ በመሃዲስቶች ላይ ያደረጉት ውጊያ ውጤቱ ጎንደርንና ሕዝቧን ለጥፋት የዳረገውን የበቀል እርምጃ የሱዳኑ መሃዲ ጦር እንዲወስድና የቤጌምድር መጋየት ሆነ።

አፄ ዮሐንስ የአፋሯን ተወላጅ ወ/ት ዳቶንን ክርስትና በማስነሳት ጥበበ ሥላሴ አሰኝተው አገቡና ራስ አርአያ ሥላሴን ወለዱ። ራስ አርአያ የአፄ ዮሐንስ ብቸኛ ልጃቸው ሲሆን የሞተውም በወጣትነቱ ነው። ራስ አርአያ ከወ/ሮ ዘውዲቱ ልጅ አልወለደም። ነገር ግን በምሥጢር ከሌሎች ሁለት ሴቶች ሁለት ልጆች ወልዷል። ከአንዷ የተወለደው ራስ ጉግሣ አርአያ ሲሆን ከሌላዋ ሴት ደግሞ የጋዜጠኛው የጌታቸው ደሥታ አባት ደስታ አርአያ ነው። ራስ ጉግሳ አርአያ ደግሞ ደጃዝማች ኃይለ ሥላሤ ጉግሣን ወለደ።

ራስ መንገሻ የደጃች ጉግሣ ምርጫ ልጅ ነው።ጉግሣ ምርጫ የአፄ ዮሐንስ ምርጫ ወንድም ናቸው።በአንዳንድ የንባብ መፅሐፍ ደግሞ እንደምናየው ራስ መንገሻ የትልቁ ራስ አርአያ ድምፁ ልጅ ነው የሚል ነው። ትልቁ ራስ አርአያም የአፄ ዮሐንስ የእናታቸው ወንድም አጎታቸው ናቸው። አፄ ዮሐንስ ራስ መንገሻን እንደልጃቸው አሳድገዋቸዋል፣ የሚጠራውም በወላጅ አባቱ በደጃች ጉግሣ ሳይሆን በአፄ ዮሐንስ ነው። በ1881ዓ.ም. እነንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሲገቡ ራስ መንገሻ ከራስ አሉላ ጋር እምቢ ብሎ አመፀ። አፄ ምኒልክ እንጦጦ ላይ በ1882 ዓ.ም. ዘውዳቸውን ከደፉ በኋላ ራስ መንገሻን ለማስገበር ዘምተው ያለጦርነት አሳምነው ተመለሱ። እንደገና ራስ መንገሻ ከድቶ በአፄ ምኒልክ ላይ በመረብ ላይ በ1884 ዓ.ም. ከኢጣሊያ መንግሥት ጋር በዠኔራል ጋንዶልፊ አማካይነት ይዋዋላል። አፄ ምኒልክ ለሁለተኛ ጊዜ በዘዴና በትዕሥት ራስ መንገሻን እየተከታተሉ ባሉበት ወቅት ኢጣሊያም ድጋፍና መሣሪያ እንደማይሠጠው ሲያውቅ በ1886 ዓ.ም. በሥራው ተፀፅቶ “ይማሩኝ ልግባ” ብሎ ደብዳቤ ለአፄ ምኒልክ ልኮ ተመለሠ።

የትግሬው እጨጌ ኢጣሊያ በአክሱም ከተቀመጡት ከእጨጌ ቴዎፍሎስ ጋር ግንኙነት አድርጎ እጨጌውንና ካህናቱን በገንዘብና በልዩ ልዩ ሥጦታ በመሳብ በትግራይና በትግረ ላሉት የተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች “ምኒልክ በሃይማኖት ከማይመስላቸው ከመስኮብ መንግሥትና ቤተ ክህነት ጋር ግንኙነት አድርገው የኖረውን የተዋህዶ ሃይማኖታችንን ሊለውጡ ነው” የሚል ስብከት በቃልም በፅሁፍም እያደረገ በኢትዮጵያ፣ በኢየሩሳሌም፣ በእስክንድርያና በኢጣሊያ አሥበተነ። ዓላማውም ከእስክንድርያው ጳጳስ ጀምሮ መነኮሳትና መምህራን በአጠቃላይ ሁሉም አማኞች በምኒልክ ላይ እንዲነሱ ነበር።
የትግሬ ባንዳዎች ከአድዋ ጦርነት ጀምሮ በተደረጉት ጦርነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍልሚያውና ግብግቡ ከሶልዳቶ ጋር ብቻ አልነበረም። በአድዋ ከተሰለፈው የጠላት ጦር መካከል ከሦሥት መቶ ሃምሳ ሽህ (350,000) በላይ የሚሆነው ባለመታደል ሆኖ ከትግርኛ ተናጋሪው ሕዝብ የተውጣጣ የባንዳ ሠራዊት ነበር።

ከፍተኛ ማዕረግ ከነበራቸው የድል አጥቢያ አርበኞች መካከል ጥቂቶቹን ብንጥቅስ የአጋሜ ባላባት የደጃች ሰባጋዲስ ተወላጆች ራስ ሥብሃትና ደጃች ሐጎስ ተፈሪ፣ የራስ መንገሻ አባት የታላቁ ራስ አርአያ ልጆች ደጃች ተድላ አባ ጉበን፣ ደጃች ደብብና ታናሽ ወንድማቸው ልጅ አብርሃ፣ ደጃች ገብረሚካኤል፣ ሹም ደራ መንገሻ፣ ደጃች ብሩ ወዘተ ይገኙበታል። ብዙ ታሪክ ፀሐፊዎች ውጊያው ባህርን አቋርጦ ከመጣው ጠላት ሳይሆን ከከሀዲያን ጋር ነበር ይላሉ።

የራስ መንገሻ ክህደት ለሦሥተኛ ጊዜ ከአድዋ ድል በኋላ የትግሬው ገዥ ራስ መንገሻ አዲስ አበባ መጥቶ አፄ ምኒልክ ታላቅ አቀባበል አድርገውለት በጦርነቱ ጊዜ ለተጎዳው ሠው 30,000 የማሪያ ቲሬዛ ብር ዳረጎት ሠጥተው ይሸኙታል። ዝምድናው እየጠበቀ እንዲሄድ በማሰብ የእቴጌ ጣይቱን ታናሽ ወንድም የራስ ወሌን ልጅ ወ/ሮ ከፈይን ያጋቡታል። አሁንም ምኒልክን ለሦሥተኛ ጊዜ ይከዳና ሸፍቶ ኤርትራ ላይ አፈግፍጎ ከተቀመጠው ከኢጣሊያ ወራሪ ጠላት ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ደፋ ቀና ይላል። እባክህ ተብሎ ሽማግሌ ቢላክበትም አሻፈረኝ አለ። ውጊያ ገጠመ፣ ተሸነፈ። “ትግሬን አገረዎን ለወደዱት ይሹሙበት እኔን ለእጄ አስምሩኝ” ብሎ እጁን ለራስ መኮነን ሠጠ። እጁን ቢሠጥም “እየተላላከ ልጆቹን እነደጃች ሥዩምንና የአፄ ዮሐንስን የልጅ ልጅ ደጃች ጉግሣ አርአያ ዮሐንስን አሸፍቷል” ተብሎ ታሠረ። በመጨረሻም እንዲሁ የውርደት ካባውን እንደተከናነበ በ1898 ዓ.ም. አንኮበር ሞተ።

የደጃዝማች ኃይለ ሥላሤ ጉግሣ አርአያ ዮሐንስ ክህደት የትግራይ ክፍለ አገር ምዕራቡ በራስ መንገሻ ልጅ በራስ ሥዩም መንገሻ፣ ምሥራቁ በደጃዝማች ኃይለ ሥላሤ ጉግሣ ይተዳደር በነበረበት ወቅት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ሊወር ሲመጣ ከኢጣሊያ ጎን ተሰልፎ በማይጨው ጦርነት ብዙ ጉዳት ኢትዮጵያ ላይ እንዲደርስ ምክንያት የሆነው ኃይለ ሥላሤ ጉግሣ ነበር። ወረራው ሲያበቃ በእንግሊዞች አግባቢነት ከታሰረበት ምህረት ጠይቆ ተመለሰ። በሌላ በኩል የአፄ ኃ/ሥላሴን ልጅ ልዕልት ዘነበወርቅን አግብቶ ሲኖር ነፍሰጡር ሆና ይደበድባት ሥለነበር በወሊድ ምክንያት እንደሞተች ይነገራል።

በኢጣሊያን ወረራ ጊዜ የፈጀን የትግሬ ባንዳ ዳግመኛ ከወረረን የፋሽስት ሠራዊት ጋር በመሆን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያኖችን መግደሉ ይታወሳል። የካቲት 12 ቀን የግራዚያኒን በቦምብ መቁሠል ምክንያት በማድረግ በተወሰደው ቂም በቀል እርምጃ አዲስ አበባ ለሦሥት ቀናትና ሌሊት በጥይትና በቦምብ ስትነድ ቁሥለኛውን ሳይቀር በሳንጃ እየጨቀጨቁ ከአፈር በመቀላቀል ከሠላሣ ሰባት ሽህ በላይ እሬሳ የቆለሉት የትግሬ ባንዶች ነበሩ። በ1931 ዓ.ም. ከአሥራ አንድ ሽህ (11000) በላይ ሕዝብ ያለጣሪያ ዙሪያውን በታጠረ ሜዳ ላይ በቀን ሐሩር በሌሊት ቁር ያለእህልና ውሃ ለሁለት ሳምንት ሲሰቃይ ቆይቶ ጥቂቱ አይሞቱ ሞት ይሞታል። ቀሪውም በአፋጣኝ አላልቅ ሥላላቸው የዘብጥያው ካራምፕሬ ዝነኛው ዘርዓብሩክ በርሄ ከአለቃው ከማጅሬ ሞሬቲ ጋር በመምከር የእሳት አደጋውን መኪና ናፍታ በመሙላት ያን የደከመ ሊያመልጥ የማይችል ህፃናት፣ ሴትና የአረጋውያን እስረኛ ነዳጅ እንዲርከፈከፍበት አድርጎ ከየማዕዘኑ እሳት ይለቅበታል። ዘርዓብሩክ በርሄ በዚህ ተግባሩ የኒሻን ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። ጎንደር ውስጥ የነበረውም የፋሽስት ጄኔራል አዘዞ ውስጥ “ለመቀጣጫ” በሚል ተመሳሳይ ተግባር ፈፅሟል።

እንግሊዝ ከኢጣሊያን ጋር ተባብራ ኢትዮጵያ የኢጣሊያ ቅኝ ግዛት እንደሆነች ተቀብላ ነበር። ነገር ግን በኋላ ኢጣሊያ በራሷ በእንግሊዝ ላይ ሥለመጣችባት በድንገት እንግሊዝ የኢጣሊያ ባላጋራ ሆና ለኢትዮጵያ አርበኞች ድጋፍ በመሥጠት ኢጣሊያ ድል ሊመታ በቃ። በርካታ ሹምባሾችና ቡልቃሾች የፋሽስትን ሡሪና ቆብ አውልቀው ለእንግሊዝ በትርጁማንነት ማገልገል ጀመሩ። ወዳጅ መሥሎ የገባው እንግሊዝ በኢትዮጵያውያን ላብ የተተከሉትን ፋብሪካዎች የተሠሩትን ህንፃዎችና ድልድዮች ሳይቀሩ የቻለውን ያህል አሥነቅሎ ሲወስድ ያልቻለውን ደብረዘይት ሐይቅ ውስጥ እንዲሠምጥ ያደርጋል። በመነቃቀሉም ሆነ በተሽከርካሪ እያጓጓዙ ሐይቁ ውስጥ ይጥሉ የነበሩት ቀደም ሲል ለኢጣሊያ በማደር በኋላ ላይ ደግሞ ለመጣብን የወዳጅ ጠላት ለእንግሊዝ በማደር የበደል በደል የፈፀሙት እነኚሁ ባንዶች ነበሩ።

የኢትዮጵያ ባንዲራ በነፃነት መውለብለብ ከፋሽስት የተላቀቀውን ኢትዮጵያዊ ሲያሥደስት ባንዶቹን ግን አሥደንግጧል። ለምሳሌ የመጀመሪያው የወያኔ ታሪክ አመጣጥ ጠላት የሠጣቸውን ብረት ይዘው ዱር በገቡ ከሀዲያን እንደነበር አይዘነጋም። ይህም ሳይውል ሳያድር ለመቀጨት ቢበቃም በነመለስ ተግባራዊ ሆኖአል።

የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ያንን ሁሉ ግፍ የፈፀሙ ባንዶችን በመማሩ በድፍን ኢትዮጵያ ተሰግሥገው እንደ እናት ሲመጠምጧት እንደ እንጀራ እናት ሞቷን ሲመኙላት፣ አሁን ለምንገኝበት ሁኔታ አብቅተዋታል። ይህንን ሁሉ ወንጀል የፈፀሙ ጉዶች አፄ ኃ/ሥላሴ ከጦርነቱ በኋላ ምንም ሳያደርጓቸው በመላ አገሪቱ እንደፈለጉ ሲቧርቁበት ኖሩ። እንደውም ከእነአካቴው ከወሎና ከጎንደር ጀምሮ በመላ አገሪቱ ውስጥ በንግዱም በሁሉም መስክ ተሠግሥገው ሲቦጠቡጡና እንድልባቸው ተንደላቀው አገር ሲያደሙ እንዲኖሩ ከማድረጋቸውም በላይ በሹመት ላይ ሹመት ያሸከሟቸውም ነበር። በተቃራኒው ግን የአገር ዜግነት ግዴታቸውን ከአፄ ኃ/ሥላሴ በላቀ መንገድ የተወጡትን ጀግኖች አንድም ሳያሥቀሩ እንደ በላይ ዘለቀ፣ታከለ ወልደ ሃዋርያት፣ራስ ጉግሣ ወሌ ብጡል፣ወዘተ በአሰቃቂ ሁኔታ ጨርሰዋቸዋል።

እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ
የባዕድን ፍልስፍና አንግቦ ኢትዮጵያን በማድማት ላይ ለተሰማሩት ለተገንጣይ ድርጅቶች ለእነሻዕቢያ ቀኝ እጅ በመሆን የኤርትራን መገንጠል ያመቻቹትን፣ የሠይድ ባሬን ወረራ የተባበሩትን፣ አያሌ ወገኖቻችንን በማጥፋትና በማስጠፋት አገራችን የተማረ ሠው አልባ እንድትሆን ያደረጉትን እንዲሁም ለብዙ መቶ ሽህ ኢትዮጵያውያን ሥደት የዳረጉትን ድርጅቶች እነኢሕአፓን ያቋቋሙት እነብርሃነ መሥቀል ረዳ፣ እነተሥፋየ ደበሳይ እነዘሩኪሼን ወዘተ ነበሩ። እነሱ ያቋቋሙት ድርጅት ኢሕአፓ፣ ከኢሕአፓ ወጥተው የዛሬውን ወያኔ የፈጠሩት፣ ኢህዴን በኋላም ብአዴን ከመኢሶን ጋር በመሆን ይችን መከረኛ አገር እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ መቃብሯን እየማሱላት የሚገኙት እነዚሁ ባንዶች ናቸው።

እነመለስ፣ ገብሩ አሥራት፣ ሠየ አብርሃ፣ አረጋዊ በርሄና አብርሃም ያየህ በ1980 ውስጥ የኢትዮጵያ ሳይሆን “የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ)” በሚባለው የባንዳ ድርጅት ውስጥ በአንድ ላይ ሆነው ትግሬን በመገንጠሉ ዓላማ ተሥማምተው አዛዥና ታዛዥ ሆነው በውሎና በጎንደር እየተዘዋወሩ ኢትዮጵያን በጋራ ሲያደሙና “ሥንት አማራ ገደልክ” እያሉ ሲዛበቱብን ነበር። በ1991 ዓ.ም.አዲስ አበባ ከገቡ ጀምሮ ከባንዲራው እስከ ሠው ህይወትና አገር እስከማጥፋት ድረስ አብረው በመካፈል ወንጀል ፈጽመዋል። ዛሬ አንዱ የመለስ ደጋፊ ሌላው የመለስ ተቃዋሚ በመሆን ለኢትዮጵያ አንድነት አሥመሳይ ተቆርቋሪነትን በማሳየት ውሥጣችን ገብተው ለማዘናጋት የሚያደርጉትን ሥናይ ሆዳችን ይደማል።

የትግራይ ባንዳዎች የያዙት የታሪክ ድለዛና ማንነት የመግፈፍ ዘመቻ አደገኛ በመሆኑ መቀጨት አለበት። የሌለ ልዩነትን የወቅቱ አብይ አጀንዳ አድርገው በማቅረብ ፊታችን በተደቀነው ርሃብና ድህነት ላይ በማተኮር የጋራ መፍትሄ የምናገኝበትን መንገድ እንዳንፈልግ መንገዱን አጥረው በመያዝ የችግሩ ሰለባ ሆነን እንድንቀር ባለ አቅማቸው ይረባረቡብናል። ስለሆነም እንደነዚህ ላሉት ደናቁርት እንደ ከዚህ በፊቱ ሜዳውን ትቶ እንዲጨፍሩ መልቀቁ በአገራችን ላይ ትልቅ ቀውስ የሚፈጥር በመሆኑ ምላሹን በሚገባቸው ቋንቋ መስጠት ያስፈልጋል። ያሳየናቸው ሆደ ሰፊነትና ቁጥብነት ለአገራችን መውደቅ ምክንያት በመሆኑ ከእንግዲህ በዝምታ አናልፋቸውም።

በመጨረሻ ማስታወስ የምንሻው የኢትዮጵያን ባላንጣዎች ታሪክ ፈልፍሎ ማጋለጥ የማንም ዜጋ ግዴታ በመሆኑ ከአሁን ወዲያ እቅጩን ከመናገር ወደኋላ አንልም፣ በይሉኝታም አንባዝንም። “ዶሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ (ካሪያ)” ያልነውም ግፍና ውሸት ሞልቶ ሥለፈሰሰና ሥለአንገሸገሸን ዕውነተኛ ተግባራቸውን ዘርዝረን ማጋለጥ ሥለተገደድን ነው።

ማሥታወሻ ሥሁል ማለት “የተሳለ፣ ሹል” ማለት ነው። ይህ የሥሁል ሚካኤል የቅፅል ሥም ሲሆን ከሥሙ ከሚካኤል ቀድሞም ተከትሎም ይነገራል፣ይፃፋል።

ዋቢ መጻሕፍት
ዐፄ ቴዎድሮስ፣ዐፄ ዮሐንስ፣ ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት ከተክለጻዲቅ መኩሪያ
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ከጳውሎስ ኞኞ
የሃያኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ እና

እንዲሁም ከተለያዩ መፅሔቶችና ምንጮች የተወሰዱ ናቸው።


ራስ መስፍን ስለሺ
ራስ መስፍን ስለሺ