አማራ ንቃ ጠላቴ ነህ የሚልህን ወያኔን አታድልብ። በአማራው አካባቢ ያለዉ ጉድ ወደፊት ሲጋለጥ የአለም ህዝብ ሳይቀር ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል። እንኩዋን ዉሃ መብራትና የጤና አገልግሎት ሊያገኝ ቀርቶ ከአቅሙ በላይ ግብር እየከፈለና ያመረተዉን ጤፍ ስንዴና ጥራጥሬ በርካሽ ዋጋ በወያኔና በጸረ አማራ ሰርጎ ገብ ነጋዴዎ በርካሽ በማንአለብኝነት እየተዘረፈ ነው። በደሉ በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በመገናኛ በጤና በትምህርትና በዋና ዋና የእድገት መሰረት በሆኑት የኤሌክትሪክና የዉሃ አገልግሎቶች ላይ ነው።
፪፭ አመት ሙሉ አዉራጃ ከአዉራጃ እንኩዋን እንዳይገናኝ መንገድ አልተሰራም። ብዙ የኛው ደነዞችና የወያኔ አዉቆ ፕሮፓጋንዳ ነዥዎች መንገድ ስለመሰራቱ አፋቸዉን ከፍተው ሲያላዝኑ ያሳፍራል። አዲስ ኣበባ ዉስጥና ወደ ናዝፍሬትና ወደ ሰሜን ለወያኔ መንሸራሺሪያና ለትግሬ ምግብና ሸቀጥ መሸጫ በዓለም ባንክ ብድር የተሰራዉን መንገድ ወያኔ ከኪሱ አዉጥቶ እንደሰራው አርገው የሚያወሩ በቀቀኖችን ብዙ ሰው ያዉቃቸዋል። ታዝቦአቸዋልም።
አሳዛኙ እዉነት ግን በአሁኑ ሰአት አዲስ ኣበባ አጠገብ ያሉ የሰሜን ሸዋ ሰፋፊ አዉራጃዎች መገናኛ የላቸዉም። ለምሳሌ ከተጉለት ወደ መርሃቤቴ ለመሄድ በአዲስ ኣበባ ዞሮ በፍቼ በኩሉ ዞሮ ነው የሚኬደው። ጅሩና መንዝ መንገድ የላቸዉም። አይገናኙም። ስለዚህ ወደመንዝ ከጂሁር ውይም ከእነዋሪ ለመሄ የግድ ደብረብርሃን ሄዶ እንደገና ወደመንዝ መጉዋዝ ያስፈልጋል። መንዝና መርሃቤቴም እንዲሁ መንገድ የላቸዉም። በአጭሩ ከመንዝ መርሃቤቴ ለመሄድ በደብረብርሃን በኩል አዲስ ኣበባ ተደርሶ ነው እንደገና ወደ መርሃቤቴ የሚኬደው።
በሰሜን ሸዋ በወሎ በጎጃምና በጎንደር የቅርብ አውራጃዎች መካከልም ወደ ትግሬ እንደልብ ከሚያስከደው አዉራ ጎዳና በስተቀር በዚህ ሰፊ በሆነው የአማራ ግዛት ዉስጥ የረባ መገናኛ መንገድ የለም። ወያኔወ ች ላለፉት ፪፭ አመታት አማራው ኦሮሞዉና የደቡቡ ህዝብ በገንዘቡና በደሙ የገነባዉን ሃገር ያለ ሃፍረት ከመዝረፋቸዉ በላይ አሁን አማራው ወደሁዋላ እንዲቀር ወጥረው ይዘዉታል። ብዙዎች የአማራ ከተሞች እስካሁን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከማመንጫው አጠገብ ሆነው እንኩዋን አላገኙም።
ለምሳሌ የጎንደር ደብረታቦርን ከተማን ያገለለው ያለሀፍረት ወደ ትግሬ ከ ፪፭ አመት በፊት ተዘርግቶ ትንንሽ መንደሮችን ሳይቀር ያዳረስው የመብራት አገልግሎት የአንተ አንጡራ ገንዘብ መሆኑን አትርሳ። ከመርሃቤቴ ወይም ከወሎ ወደ ባህርዳር ለመሄድ ወደ ደቡብ(አዲስ አባባ)ተጉዞ እንደገና ከአዲስ ኣበባ ነው ወደ ጎጃም ወይም ጎንደር ወይም ባህርዳር የሚኬደው።
ወያኔና ጸረ አማራ ኮንትራክተሮች አሁንም በኢትዮጵያና በብድር የሚሰራዉ የባቡር ሃዲድ ሰሜን ሸዋን ወሎን ጎጃምንና ጎንደርን እንዳይነካ ተደርጎ እንደ ደጋን ጎብጦ ትግሬ ከገባ በሁዋላ የትግሬን ዋና ዋና ከተሞች ለማገናኘትና ተጠቃሚ ለማድረግ በጥንቃቄ የተነደፈ ነው። አማራ ንቃ በስምህ ከአለም ባንክ የሚመጣዉ ገንዘብ የጠላትህ ጡንቻ ማጠንከሪያ እየሆነ ያመረትከዉን እህል እያስረከብክና ከልጆችህ አፍ አየነጠቅ ህ ግብር እየከፈልክ ጠላቴ ነህ የሚልህን ወያኔን አታድልብ።