አንድ ቀበሌን ወይም ኢትዮጵያን ነጻ ለማዉጣት ጉልበት ይጠይቃል
ሸንቁጥ አየለ
ወያኔ ያቦካዉ መርዛማ ጭቃ ዉስጥ ቆመህ: ወያኔ የሰራዉን የህግ ማዕቀፍ እያጣቀስክ ስለምንም ነገር አትከራከር ማንንም ህዝብ አትዝለፍ:: በኢትዮጵያ ምድር ላይ የሚሆነዉን ነገር ሁሉ መወሰን የሚቻለዉ የምትቆምበት የክርክር ሜዳ አንተ ያበጀህዉ የምትነጋገርበት እና የምትከራከርበት ሁኔታ ብሎም በዉይይት እና በስምምነት ሊወሰን የሚችል አጠቃላይ ሀገራዊ ሂደት ሲኖር ነዉ::
ወያኔ የሰራዉን ክልል እያነሳህ እና እያጣቀስክ በማንኛዉም ነገር ላይ እከራከራለሁ ሀሳብ እሰጣለሁ ወይም ሰዉ አሳምናለሁ ብለህ ከተነሳህ ግን አንድ ግልጽ ያልሆነልህ ነገር አለ ማለት ነዉ:: እናም እራስህን መርምር::
በትክክል ወያኔን የምትቃወም እና የምትጠላ ጀግና ከሆንክ አንድ ነገር ወስነህ ተነሳ:: የወያኔ የሆነን ነገር ሁሉ አፍርሰህ እና ንደህ ተነስ:: የወያኔን አስተሳሰብ ናደዉ:: ሆኖም ከወያኔ የጭቃ ሜዳ ዉስጥ ገብተህ ክርክር እንዳትገጥም ከባድ ጥንቃቄ አድርግ::
በወያኔ የህግ ማዕቀፍ ዉስጥ ሆነህ ምንም ነገር እንዳታስብ:: ወያኔ የሰራዉን ክልል ሁሉ እንደሌለ ቆጥረህ በማሰብ ተነስ:: ይሄ አካባቢ ለዚያ ወይ ለዚህ ብሎ ወያኔ የሸነሸነዉን ሁሉ እርሳዉ:: ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ እንድትሆን የሚለዉን መርህ ይዘህ ተነስ::
በብሄርህ ልትደራጅ ትችላለህ ወይም በኢትዮጵያዊነት ልትደራጅም ትችላለህ አለዚያም እጅግ ከምታምናቸዉ ከሰፈርህ ልጆች ጋር ብቻ ሆነህ ወያኔ ለመደምሰስ ልትዘጋጅም ትችል ይሆናል:: አደረጃጀትህ ወያኔ ለመጣል ከሚደረጉ ታክቲኮች አንዱ ብቻ ነዉ:: የፍጻሜ ግብህ ግን በቅንነት መላዉን የኢትዮጵያን ህዝብ ለማዳን እና ሁሉም የሚስማማበትን አጠቃላይ ሀገራዊ መሰረት ለመፍጠር ቆርጠህ መነሳትህ ይሁን:: አባቶችህ የደከሙበትን መሰረት ወደ ታላቅ መሰረት የመዉሰድ ግዴታህን ለመወጣት ወኔ ካጣህ ግን ቀድመህ በወያኔ አስተሳሰብ ተሸንፈሃል ማለት ነዉ:: ወያኔ የሚፎክረዉ የቀደመዉን መሰረት ሁሉ ንጄዋለሁ ብሎ ነዉ:: ወያኔ በምቀኝነት የሚፏልለዉ ኢትዮጵያ የሚባለዉን ሀገር ወደ አለመኖር ጠርዝ ግፍቼዋለሁ ብሎ ነዉ::
ወያኔ የሰራዉን የተጨመላለቀ የክልል ጉዳይ የተወሳሰበ የጎሳ መርዛማ ጥላቻ በኢትዮጵያዉያን መሃከል እንዳለ ቁም ነገር አድርገህ አትዉሰድ:: በወያኔ መርዝ የተለወሱትን ሁሉ ከምድሪቱ ጠርገህ እና ደምስሠህ የመጣል ህሳቤን ይዘህ ተነሳ:: ጀግና ከሆንክ በቀበሌ ደረጃም ተዋጋህ ወይም በሀገር ደረጃም ተዋጋህ የጦርነቱ ድምዳሜ አንድ መስመር ላይ እንደሚገናኝ አትርሳ::
ሀገሩ መፈወስ አለበት:: ህዝቡ መዳን አለበት:: አንድን ቀበሌ ወይም አንድን ወረዳ ወይም አንድን ክልል ወይም ኢትዮጵያን በአጠቃላይ በጉልበት ከወያኔ እጅ ፈልቅቆ ለመዉሰድ ጉልበት ይጠይቃል:: ስለዚህ ዉጊያህ ስለአንድ ቀበሌ ወይም ስለ አንድ ክልል ሆኖ እንዳይወሰን ከመነሻህ ጥራት ባለዉ ሃሳብ ተንደርደር:: ኢትዮጵያን አድን ! የአባቶችህን ሀገር!!
ጀግነህ እና ታላቅ ሆነህ ተነስ:: ስለ ታላቂቱ የአባቶህ ሀገር ስለ ኢትዮጵያ ተነስ! አከናዉንም:: ኢትዮጵያን እጅህ ስታደርግ የምትወደዉን ሁሉ ታድናለህና:: ከዉጊያህ በፊት ግን የፍናፍንት ህሳቤ የሆነዉን የወያኔ ሃሳብ ሁሉ ረግጠህ ጣለዉ:: እንደቆሻሻም ቁጠረዉ::