አዲስ አበባ የሁላችንም ካልሆነች የማንም አትሆንም!

አዲስ አበባ የሁላችንም ካልሆነች የማንም አትሆንም!

 

አዲስ አበባ የሁላችንም ካልሆነች የማንም አትሆንም!

 

 

አዲስ አበባ የሁላችንም ካልሆነች የማንም አትሆንም!
ጊዮርጊስ የአጼ ምኒልክ አደባባይ

“ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ያሉን አቶ ለማ መገርሳ አዲስ አበባን የኦሮሞ የግል ሀብት ለማድረግ ጠንክረው እየሠሩ እንደሆነ የካቲት 28 ቀን 2011ዓም በወጣው የክልሉን መንግሥት አቋም በሚገልጸው መግለጫ አረጋርጠዋል:: መግለጫውም እንዲህ ይላል “በአዲስ አበባና ኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ እልባት ሳይሰጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ መተላለፋቸው ተገቢ አይደለም::” ይላል:: መግለጫው አያይዞም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በሁሉም አቅጣጫ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ደረጃ በደረጃ እየሠራ መሆኑን አጽንዖት ሰጥቱዋል:: በዚህም ትላልቅ ስኬቶች እየተመዘገቡ እንደሆነ መግለጫው በኩራት ያብራራል:: የአዲስ አበባ ጉዳይ በተመለከተ እና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ስላላቸው ጉዳዮች በሙሉ በቅደም ተከተላቸው መልስ እንዲያገኙ በተሃድሶ ከስምምነት ላይ የተደረሰበት እንደሆነ በማውሳት ይህ ዕውን እንዲሆንም አበክረው እየሠሩ እንደሆን መግለጫው አልሸሸገም:: ከሁሉም በላይ መግለጫው በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ አልባት እስከሚያገኝ የኦሮሚያ ክልል ጥያቄ እያነሳባቸው ባሉ የአዲስ አበባ አዋሳኝ ቀበሌዎች ከክልሉ ወሰን አልፈው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች በዕጣ ማስተላለፍ ትክክል እንዳልሆነ በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዕምነት እንደሆነ ያስረዳል:: መረጃዉን በሙሉ ለማንበብ ይህንን መስመር ይጠቁሙ::