አገር ሠሪ፣ አገር አልባ ሕዝብ!

አገር ሠሪ፣ አገር አልባ ሕዝብ!

 

አገር ሠሪ፣ አገር አልባ ሕዝብ!ዐማራ እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ኢትዮጵያን እንደ አገር ከሠሯት ነገድና ጎሣዎች መካከል አንዱና ግንባር ቀደሙ መሆኑን የአገሪቱ የረጅም የመንግሥትነትና አገራዊነት ታሪክ ያስረዳል። ዐማራው ቋንቋን ከፊደል፣ ሃይማኖትን ከሥርዓት፣ ሕግን ከባህል፣ አጣጥሞና አዋሕዶ ለኢትዮጵያውያን የወል መጠቀሚያነት ያበረከተ ሕዝብ ነው። ጀግናና ኩሩም ነው። የዛሬውን አያድርገውና፣ መብቱ ሲነካበት የማይወድ፣ ለማንነቱና ለነፃነቱ ቀናዒ ሕዝብ የነበረ ነው። እነዚህ መገለጫዎቹ መሆናቸውን የድሆኖ፣ የእንትጮ፣ የሣር ውኃ፣ የመተማ፣ የዐድዋ፣ የአምባላጌ፣ የወልወል፣ የቆራሄ፣ የመቀሌ፣ የማይጨው ወዘተ ጦር ሜዳዎችና የተገኙት ድሎች ሕያው ምስክሮች ናቸው።

ይሁንና ዛሬ የትናንት አገር ሠሪው አገር አልባ እንዲሆን ተደርጓል። በተገኘበት ማንም ያሻውንና የፈለገውን ግፍ የሚፈጽምበት እና የግፍ ዓይነቶች መለማመጃ ሆኗል። ከ1972 ዓም ጀምሮ፣ ወልቃይ፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ራያ እና ቆቦ፣ወረዳና አውራጃዎች ነዋሪ ዐማራዎች ፣እንዲሁም ከ1983 ዓም ጀምሮ ሐረርጌ፣ ወለጋ፣ኢሉባቡር፣ ከፋ፣ ጎጃም(መተከል) ወዘተ ክፍለ-ሀገሮች ነዋሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ፣ የተፈጸመውና እየተፈጸመ ያለው ጅምላ ግድያ፣ እሥራት፣ ግርፋት፣ ማፈናቀል፣ ማዋከብ፣ ዘር ማጥፋትና ዘር ማጽዳት መሠረት …

ሙሉዉን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን መስመር ይጠቁሙ