ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የዘመን መለወጫ አከባበርን በሚመለከት ለመላው የዐማራ ልጅ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ነሐሴ ፴ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፯
ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፦ ለመላው የዐማራ ልጅ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ጉዳዩ፦ የመጭውን ዘመን መለወጫ (መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም.) በፈንጠዝያ ሳይሆን፤ ዕለቱን በመሪር ሐዘንና በቁጭት አስቦ ስለመዋል።
ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ በዐማራው ወገናችን ላይ ከፋሽስት ጣሊያን በከፋ መልኩ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ሲፈጽም እነሆ 41ኛ ዓመቱን አገባድዶ በ42ኛው ላይ ይገኛል። በተለይም ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የጅምላ የጥፋት ዘመቻ አውጇል። የአገዛዙ የኅልውና መሠረት የሆነው ነፍሰ በላው የአጋዚ ሠራዊት ዕድሜና ፆታ ሳይለይ፥ ሕፃናትን፣ ወጣቶችን፣ አዛውንትን፣ ጎልማሶችን፣ ወንዶችና ሴቶችን ቤት ለቤት እያደነ እጅግ መርዘኛ በሆነ ጥይት እየደበደበ የዘር ፍጅት እያደረሰ ነው።
የትግሬ-ወያኔ በከፈተው በዚህ ዐማራን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዘመቻ፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ እህት ወንድሞቻችን ተገድለዋል፤ አያሌዎች ቆስለዋል፤ በርካታዎች ታስረዋል፤ ተጫውተው ያልጠገቡ፣ ክፉ ደጉን ያልለዩ ሕፃናት በአረመኔዎቹ ወያኔዎች ተቀጥፈዋል። ልጆቻችን አድገው ከበስቋላው ሕይዎታችን ይታደጉናል ብለው ተስፋ የሰነቁ ወለጆች፣ ተስፋቸውን አጥተዋል፤ ቤተሰብ ፈርሷል። እነዚህ ወንድም እህቶቻችን ሕይዎታቸውን፣ አጥንታቸውን፣ ደማቸውን የሰጡት እና መስዋዕት የሆኑት፣ ለዐማራ የማንነት ጥያቄ ተገቢ መልስ ለማስገኘት ነው። እነርሱ ለእኛ ነፃነት ሲሉ ሞቱ፣ ተሰቃዩ። እኛስ እነርሱ የሞቱለትንና እየተሰቃዩ ላሉበት ክቡር ዓላማ፣ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? ብለን ራሳችን በመጠየቅ፣ ከትውልድና ከታሪክ ተጠያቂነት የሚያድን ተግባር ልንፈጽም ይገባል። ስለሆነም ጀግኖቹ ሰማዕታት እህት ወንድሞቻችን የሞቱለትን ዓላማ ዳር ለማድረስ፣ ዓርማቸውን አንግበን፣ በአንድነት የድሉን ቀን ለማቃረብ በጽናት ወያኔን ልንዋጋው ይገባናል።
ከሁሉም በላይ ትግሉ የሚጠየቀውን ማናቸውንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመክፈል፣ የዐማራው ወጣት ትውልድ ራሱን በሁለንተናዊ መልኩ ማዘጋጀትና ትግሉን በቆራጥነት መቀላቀል ነገ ዛሬ የምንለው ጉዳይ አይሆንም። ማድረግ ካሉብን ድርጊቶች መካከል በጣም በትንሹ በኑሮአችንም ሆነ በሕይዎታችን ምንም ዓይነት ኪሣራ በማያስከትሉት መጀመር ይቻላል። ስለዚህ የሚከተሉትን ተግባሮች በማከናዎን ከዚህ በታች ስማቸው በተዘረዘሩት ሰማዕታት ስም ጥሪያችን እናቀርባለን።
አንደኛ፦ በሚመጣው የዘመን መለወጫ ቀን በዓሉ ከሚጠይቀው ፈንጠዝያ፣ ሣቅና ጨዋታ ተቆጥበን፣ ዕለቱን የሐዘንና የቁጭት መግለጫ የሆነውን ጥቁር ልብስ ለብሰን የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ እያውለበለን እንድንውል፤ ስንበላና ስንጠጣ ሰማዕታቱን በጸሎታችን እንድናስባቸው።
ሁለተኛ፦ ከኢትዮጵያ የሚመጣ እንጀራ እስከ ወዲያኛው ላለመግዛት እንወስን።
ሦስተኛ፦ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለመጓጓዝ እንወስን።
አራተኛ፦ ከወያኔና ከወያኔ ጋር ንክኪነት ካለቸው ድርጅቶች፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች፣ ምግብ ቤቶች፣ ወዘተርፈ አንጠቀም።
አምስተኛ፦ የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ከሆኑ ሰዎች ጋር የነበረንን ግንኙነት እናቋርጥ።
ስድስተኛ፦ ዐማራው መከበር የሚችለውና ወያኔን እስከ ወዲያኛው ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ሥልጣን አሽንቀጥሮ መጣል የሚችለው በማንነቱ ሲደራጅ ነውና፣ በዐማራ ስም የተደራጁ ድርጅቶችን እንደግፍ፤ እንርዳ።
ሰባተኛ፦ በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመውን ዕልቂት ለዓለም ማኅበረሰብ በስፋት ለማሣወቅ፣ በየአለንበት አካባቢ በሚዘጋጁ ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ትዕይንቶች እንሣተፍ፣ የተማጽኖ ደብዳቤዎችን እና መልዕክቶችን ለየአገሩ ፖለቲከኞች፣ መንግሥታት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እናድርስ።
ሠንጠረዥ፦ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም በትግሬ-ወያኔ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችን ስም ዝርዝር
ተራ ቁጥር |
የተገዳይ ሙሉ ስም |
ዕድሜ |
የመኖሪያ አድራሻ |
1. |
ዕድሜዓለም ዘውዱ |
27 |
ባሕር ዳር |
2. |
ገረመው አበባው |
25 |
ባሕር ዳር |
3. |
ተፈሪ ባዩ |
16 |
ባሕር ዳር |
4. |
ሰሎሞን አስቻለ |
25 |
ባሕር ዳር |
5. |
ሙሉቀን ተፈራ |
27 |
ባሕር ዳር |
6. |
አደራጀው ኃይሉ |
19 |
ባሕር ዳር |
7. |
አስማማው በየነ |
22 |
ባሕር ዳር |
8. |
ታዘበው ጫኔ |
21 |
ባሕር ዳር |
9. |
አሥራት ካሣሁን |
24 |
ባሕር ዳር |
10. |
የሽዋስ ወርቁ |
20 |
ባሕር ዳር |
11. |
ብርሃን አቡሃይ |
29 |
ባሕር ዳር |
12. |
ሽመልስ ታዬ |
22 |
ባሕር ዳር |
13. |
አዛናው ማሙ |
20 |
ባሕር ዳር |
14. |
ሢሣይ አማረ |
24 |
ባሕር ዳር |
15. |
ሞላልኝ አታላይ |
21 |
ባሕር ዳር |
16. |
እንግዳው ዘሩ |
20 |
ባሕር ዳር |
17. |
ዝናው ተሰማ |
19 |
ባሕር ዳር |
18. |
ዋለልኝ ታደሰ |
24 |
ባሕር ዳር |
19. |
ይታያል ካሤ |
25 |
ባሕር ዳር |
20. |
እሸቴ ብርቁ |
37 |
ባሕር ዳር |
21. |
ሞገስ |
40 |
ባሕር ዳር |
22. |
አደራጀው ደሣለኝ |
30 |
ባሕር ዳር |
23. |
ማኅሌት |
23 |
ባሕር ዳር |
24. |
ተስፋዬ ብርሃኑ |
58 |
ባሕር ዳር |
25. |
ፈንታሁን |
30 |
ባሕር ዳር |
26. |
ሰጠኝ ካሤ |
28 |
ባሕር ዳር |
27. |
ባበይ ግርማ |
26 |
ባሕር ዳር |
28. |
አብዮት ዘሪሁን |
20 |
ባሕር ዳር |
29. |
ሀብታሙ ታምራት |
27 |
ባሕር ዳር |
30. |
ሞገስ ሞላ |
23 |
ባሕር ዳር |
31. |
ታደሰ ዘመኑ |
26 |
አዴት |
32. |
እስቲበል አስረስ |
19 |
አዴት |
33. |
አበበ ገረመው |
27 |
ጢስ ዐባይ |
34. |
ይበልጣል ዕውነቱ |
24 |
ጢስ ዐባይ |
35. |
ሰሎሞን ጥበቡ |
30 |
ቻግኒ |
36. |
በረከት ዓለማየሁ |
28 |
ዳንግላ |
37. |
ያየህ በላቸው |
30 |
ዳንግላ |
38. |
ዓለማየሁ ይበልጣል |
27 |
ዳንግላ |
39. |
ሽመልስ ወንድሙ |
28 |
ቡሬ |
40. |
አለበል ዓይናለም |
28 |
ደብረማርቆስ |
41. |
ስሙ ገና የሚጣራ ደካማ እናት ያሉት |
ደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03 |
|
42. |
ዓይንአዲስ ለዓለም |
24 |
ደብረወርቅ |
43. |
አበጀ ተዘራ |
28 |
ወረታ |
44. |
ደመቀ ዘለቀ |
22 |
ወረታ |
45. |
አለበል ሃይማኖት |
24 |
ወረታ |
46. |
መሣፍንት አማራ |
22 |
እስቴ |
47. |
በለጠ ካሤ |
32 |
ደብረታቦር |
48. |
ይህነው ሽመልስ |
30 |
ደብረታቦር |
49. |
ማዕረግ ብርሃን |
ደብረታቦር ቀበሌ01 |
|
50. |
መምህር ተስፋዬ ብርሃን |
ደብረታቦር ቀበሌ01 |
|
51. |
ባየሁ |
ጎንደር |
|
52. |
የቻፖራ ወንድም |
ጎንደር |
|
53. |
በለጡ መሐመድ |
አዘዞ |
|
54. |
እንጀራ ባዬ |
አዘዞ |
|
55. |
ግርማቸው ከተማ |
ላይ አርማጭሆ |
|
56. |
አዛናው ደሴ |
አርማጭሆ |
|
57. |
አራጋው መለሰ |
አርማጭሆ |
|
58. |
ሲሣይ ታከለ |
አርማጭሆ |
|
59. |
ሊሻን ከበደ |