ተጉለት እና የሸዋ ነገስታት ሀረግ
ተጉለት የኢትዮጲያ ዋና ከተማ እንድትሆን ያስቻላት አጼ ይኩኑ አምላክ ነበር። እርሱም ያግባ ጽዮንን ያግባ ጽዩን ወንድም ያራድን ወንድም ወንድም ያራድ ደግሞ አምደ ጽዮንን ወለደ ንጉስ አምደ ጽዮን ደግሞ ንጉስ ንዋየ ማርያምን እና ንጉስ ቀዳማዊ ዳዊትን ወለደ። ንጉስ ዳዊትም ከፈረስ ላይ ወድቆ ሞተ በምትኩም ልጁ ቀዳማዊ ቴወድሮስ ነገሰ። ንጉስ ቴወድሮስም አዛኝ እና ለጋስ ነበር። ቀዳማዊ ቴወድሮስ ሲሞት ወንድሙ ቀዳማዊ ይሰሀቅ ነገሰ። ከእስላሞች ጋርም በመዋጋት ምጽዋን ተቆጣጠረ። ከዚህ በመቀጠል የዳዊት አራተኛ ልጅ የይሳቅ ወንድም ዘርአ ያእቆብ ነገሰ። አጼ ዘርአ ያእቆብም ብዙ ኢትዩጵያንን ወደ ክርስቲያንነት ቀይሯል ለጣኦት እንዳይሰግዱ አድርጓል። ከዚያም ልጁ በእደ ማርያም ነገሰ በእደ ማሪያም ሲሞት ልጁ እስክንድር ወይም ዳግማዊ ቆስጠንጥኒዮስ ነገሰ፡፡
ከ እስክንድር በኋላ ወድሙ ናኦድ ነገሰ። ከዚያ በኋላ ልጁ ልብነ ድንግል ነገሰ። ከዚያ የአጼ ልብነ ድንግል ልጅ አጼ ገላዉዲዮስ ክዚያም ወንድሞ ሚናስ ነገሰ። ከዚያም የሚናስ ልጅ አጼ ሰርጸ ድንግል ነገሰ። ከዚያም ልጃቸዉ ዘስላሴ ወይም ያእቆብ ነገሰ። ከዚያም አጼ ሰርጸ ድንግል የወንድም ልጅ ዘድንግል ያእቆብን በማሸነፍ ነገሰ። ከዚያም ያእቆብ መልሶ አሸንፎ ስልጣኑን ያዘ። በመጨረሻም ሌላው የአጼ ሰርጸ ድንግል የወንድም ልጅ አጼ ሱስኒዮስ ነገሱ።
ከዚያም አጼ ፋሲል ነገሰ። ከዚያም በኋላ ልጁ ቀዳማዊ ዮሀንስ ነገሰ፡፡ ከዚያም የዮሃንስ ልጅ ቀዳማዊ እያሱ ነገሰ። ከዚያም ልጁ ተክለሀይማኖት ክዚያ እርሱ ከሞተ በኋላ የእያሱ ወንድም ቴዎፍሎስ ነግሰ። ከዚያም የያሱ ልጅ ዳግማዊ ዳዊት ነገሰ። ከዚያ የዳዊት ወንድም በካፋ ነገሰ። ከዚያም ልጁ ዳግማዊ እያሱ ነገሰ። እርሱ ሲሞት እዮአስ የሚባለዉ ወንድሙ ነገሰ……እያለ ይወርዳል።
ምንጭ:- እስማኤል በሱፈቃድ (ፌስ ቡክ)
ሰለ ሸዋ ተንቀሳቃሸና የማይነቀሳቀሱ ምሰሎች