አማራዉን ከማእከላዊ ስልጣን የማግለል የረቀቁ ተንኮሎችና መዘዛቸው
አማራዉን ከማእከላዊ ስልጣን የማግለል የረቀቁ ተንኮሎች በመፈጸም ላይ መሆናቸዉን ፍንጮች እየጠቆሙ ናቸው። ያለ በቂ ምክንያት በአማራ ጥላቻ ናላቸው ዞሮ ከወያኔ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያዉያን እርስ በርሳቸው እንዲጨፋጨፉና አለመተማመን እንዲሰፍን ያደረጉ ዘረኞች ዛሬ በአንድነት ስም እንደገና አማራዉን በማግለል ወደ ስልጣን ቀድመው መቅረባቸዉን እያየን ነው።
ማወቅ ያለብን አንድ ሃቅ ከእንግዲህ አማራው ኢትዮጵያን በመምራቱ ላይ መሪ ሚና ካልተጫወተ ሁሉም ወደ ስቃይ ጎሬአቸው እንድሚገቡ ነው። ዛሬ የደቡብ ህዝብ በ፸ የዘር ጎራ ተከፋፍሎ በሰላም ተወልዶ ባደገበት ሃገር እንደ ድኩላ እየታደነ የሚገደለው እንደነ በየነ ጴጥሮስ አይነት ተማሩ የሚባሉ አማራ ጠል ተልካሾች በፈጠሩት በዘር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ጠንቅ ነው። ይህ ሁኔታ ካልተስተካከለና የአማራውና የኢትዮጵያ ጠላቶች ለፍርድ ቀርበው ካልተቀጡ አዴፓ ማእከላዊ መንግስቱን ለመቆጣጠርና የ60 ሚሊዮን አማራ ህዝብ ጥቅም ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የእረጅም ጊዜ እቅድ አዉጥቶ መንቀሳቀስ አለበት።
የሃገሪቱዋ ባለቤት የሆነውንና በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ ተዋልዶና ተዛምዶ የሚኖረውን አማራን ያገለለ መግስትና ስርአት በድቡሽት ላይ እንደተሰሩ ቤቶች ወዲያው ፈርሰው ለማገዶ ብቻ ያገለግላሉ። ሃገሪቱዋን አረጋግቶ በአግባቡ እንደ አባቶቹ ሌሎቹን አቅፎ የመምራት ብቃቱም ሆነ አቅሙ ያለው አማራ ጋ ነው። ይህንን ያልተድበሰበሰ ሃቅ ሁሉም አማራ ተረድቶ በያለበት ለድጋሚ ጭፍጨፋ እንዳይጋለጥ አናሳና አገር አዉዳሚ ቅጥረኞችን ለማምከን የስነልቦናም ሆነ የቁሳቁስ ዝግጁቱን ያለመዘናጋት ያቀላጥፍ።
መስዋእትነትም መከፈል ካለበት ለመክፈል ይዘጋጅ። ከእንግዲህ በዲሞክራሲና በህግ የበላይነት ሁሉም እንደአቅሙ መኖር ካልቻለ ወደ ፈለገው አቅጣጫ ይንጎድ። ሰሞኑን እነ አረጋዊ በርሄን ጨምሮ የምናያቸው የወንጀለኞች የፕሮፋይል ግንባታዎች ሰላም የሚያመጡ ሳይሆን አለመተማመንና ሽፍጥን የሚያመለክቱ ብቻ ሳይሆኑ መዘዛቸው የከፋ ስለሚሆን በአስቸኩዋይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነትና አንድነት ሲባል ቢታረሙ መልካም ነው።