የዐማራው ጥያቄዎች የሚመለሱት በራሱ ዐማራው ትግል ነው!
የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) ለመመሥረት ምክንያት ከሆኑት መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ፦ በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ድርጊት መንግሥታዊ መዋቅርን ተከትሎ የመፈጸሙና በትግሬ-ወያኔው የተረቀቀውና ፀደቀ የተባለው ሕገመንግሥት ዐማራውን አገር አልባ በማድረጉ ነው። የድርጅቱ
መሠረታዊ ዓላማም በዐማራው ላይ የተከፈተውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ድርጊት ማስቆም፣ በዐማራው ላይ የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖችን ለፍትሕ ማቅረብ፣ ዐማራው የአገሩ ባለቤትነትን ዳግም ማረጋገጥ፣ የዐማራውን ሁለንተናዊ ማንነት ማረጋገጥ፣ ለእነዚህ ሁሉ ዕውን መሆን በትግሬ-ወያኔና በኦነግ ትብብር የአገሪቱንና የሕዝቡ
ገዥ ሕግ የሆነውን ሕገ-መንግሥትና ሥርዓቱን ከሥሩ ማፍለስና ዐማራ እንዴ ሌሎች ማኅበረሰቦች በእኩልነት የሚሳተፍበት ዴሞክራሲያዊ ሕገመንግሥትና ሥርዓት መዘርጋት ነው።