ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የዓባይ ግድብና ስዉሩ ጸረ ኢትዮጵያ ተንኮል

Ze Addis with Taye Tadesse and 27 others.

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴና አስጀምረው ያስመረቁት ያባይ ግድብና ያልተተገበሩት ግድቦች
( የፊልም ማስረጃ :: እባክዎ ይሄንን ፊልም ይመለከቱ)
—————————————————-—————-
የዓባይ ግድብ ሙሉ ጥናት የተጠናቀቀው በ1950ዎቹ መሆኑን ያውቃሉ?
እውን ኃይለሥላሴ እንደ ክፉ ወንጀለኛ ታንቀው መገደል ነበረባቸው?

እ .ኤ .አ 1930 ዎቹ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ G. J White Engineering Corporation of New York የተባለ ድርጅትን ለመጀመርያ ግዜ ኢትዮጵያ በመጋበዝ : ከጣና ሐይቅ በመጀመር የአባይን ግድብ ሁኔታ እንዲጠና አዘዙ:: ይሄ አሜሪካዊ ድርጅትም ጥልቅ ጥናት አካሂዶ የግድቡ ስራ ሊጀመር ሲል በጣልያንና በንግሊዝ ተንኮል ግንባታው እንዲቆም ሆነ::

ከጣልያን ወረራ በኋላ በ1950ዎቹ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የውሃ ሀብት መምሪያ እንዲቋቋም አዘዙ:: ነሓሴ 1957 እ. ኤ. ኣ የኢትዮጵያ መንግስትና የ አሜሪካው USAID የጋራ የውሃ ልማት ስምምነት ተፈራረሙ:: በስምምነቱም መሰረት 15 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ በማድረግ የአባይ ተፋሰስ ጥናት ተጀመረ::

ይሄው የአሜሪካውያንና የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን የያዘው የጥናት ቡድን ከስድስት ዓመት ጥናት በኋላ( 1958- 1964 እ ኤ አ) ጥናቱን በ 1964 ዓ.ም በ አስራ ሰባት ተከታታይ ቅጾች አሳተመ:: ይሄውም ጥናት የተለያዩ ስፋት ያላቸውን 33 የኃይል ማመንጫና የመስኖ ግድቦችን ፕሮጀክቶችን አቅርቧል:: ከነዚህም ግድቦች መካከል አራቱ ግዙፍ ግድቦች ሲሆኑም እንዲሰሩ የተጠናው በአባይ ወንዝ ላይ ነው:: የግድብ አቅማቸውም 51 ቢሊዮን ኪዪቢክ ሜትር ነው:: ይሄው ጥናት ለመስኖ የሚሆን 434,000 ሄክታር መሬትና 38 ቢሊዮን ኪሎዋት / በዓመት የሚያመነጩ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ያጠቃለለ ነው::

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለቱን ግድቦች እንዳሰሩ የግብጽና የሱዳን ጩኅት በረታ:: እነዚሁ ሀገራትም በወቅቱ ይንቀሳቀስ የነበሩትን የ ኤርትራ አማጽያን ( በተለይ ጀብሃን) በከፍተኛ ሁኔታ ማስታጠቅና ማሰልጠን ጀመሩ:: ኣጼ ኃይለሥላሴም በ 1966 በተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተገደሉ::

እ ኤ ኣ በ 1985 የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም መንግስት ( ኢህድሪ) ኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ ) ከጣልያም መንግስት ባገኘው የ ሁለት መቶ ቢሊዮን ሊሬ ( 230 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 300 ሚሊዮን ዶላር) ግዙፉን የጣና በለስን የ መስኖና ሃይል ማመንጫ ግድብ ጀመረ:: ግድቡንም ጣልያናውናን ኮንትራክተሮች አሸንፈው ሥራው ተጀመረ::

የኮሎኔል መንስግቱ መንግስት ሲገረሰስ ስልጣኑን የተረከበው የኢህአዴግ መንግስት የጣና በለስን ፕሮጀክት ብትንትኑን አወጣው:: ይህንን ፕሮጀት በተመለከተ የያኔው ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ እና ፕሬዝዳንት መለስ አላስፈላጊ ; ወዘተ በማለት በይፋ መግለጫ እስከመስጠት ደረሱ:: ሱዳንና ግብጽም በደስታ ፈነጠዙ::

ኢህ አዴግ ስልጣን በያዘ በአስረኛው ዓመት የውሃ ህብት ልማት ሚኒስቴር የሆኑ አቶ ሽፈራሁ ጃርሶ የጣና በለስ ፕሮጀት መፍረሱ መጸጸት በሚመስል ሁኔታ ከተናገሩ በኋላ ፕሮጀክቱ መልሶ እንደሚጀመር አስታወቁ::

ከጥቂት ዓመታት በፊትም 1950ዎቹ አባይ ላይ እንዲሰሩ ተጠንተው ከነበሩት አራት ግድቦች መሃል አንደኛው ተጀመረ:: ስለፕሮጀክቱ ብዙ ተወርቷል:: ስለታሪካዊ አመጣጡ ግን አንድም ቀን ሲነገር ሰምቼ አላውቅም:: ታሪኩ ግን ይሄን ይመስላል:: ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ያሰቡትን በግዜያቸው መፈጸም ባይችሉም ያስጠኗቸው ፕሮጀክቶች ግን ከሳቸው በኋላ ለተነሱ መንግስታት አጀንዳ መሆኑ አልቀረም:: ሁሉቱም መንግስታት ( ኢህድሪም ሆነ ኢሃዴግ) እሳቸው ያስጠኑትን ፕሮጀክቶች ( የ ኣጼ ኃይለሥላሴን ራዕይ ) ለማስፈጸም ጎንበስ ቀና ማለታቸው አልቀረም::

ዋቤ መረጃዎች

( የ USAID መዛግብት አክሰስ ያላችሁ ወገኖች በ 1950ዎቹ ተጠንተው አሁን እየተተገብሩ ያሉ 33ት ግድቦችን ጥናት ማግኘት ትችላላችሁ:: የዶክመንቶቹ ኮፒዎች ሌሎች ትላልቅ የአሜሪካ ዩንቨርስቲዎች አሉ:: እድሉ ያላችሁ ፈልጉት :: )

የጣኛ በለስ ፕሮጀክት ዋና መሃንዲስ Giodano Sivini ይባላል::Resistansce to Modernization in Africa , Giordano Sivini የሚል መጽሃፍ ጽፏል:; በኮሎኔል መንግስቱ ግዜ ተሰርቶ የነበረው ጣና በለስ ፕሮጀክት እና ዝርዝር የሰፈራ ሁኔታዎችን ጽፎታል:: በአማጺው ሃይልም እንዴት እንደፈረሰ ይገልጠዋል::

በአጼው ዘመን ተጠንተው ስለነበሩት ግድቦችና የወቅቱን ሁኔታ ደግሞ እዚህ ሀርቫርድ ያሳተመው መጽሃፍ ላይ ያገኙታል::Baxter, Richard R., The Law of International Waterways, Cambridge, Mass., Harvard University Press, 1964.

The Nile : historical, legal and developmental perispective Gebre Tsadik Degefu , New York