የኢትዮጵያ መወያያና የአቅም መገንቢያ ማእከል (ኢመአመማ) እኢአ ከነሀሴ 11 እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2021 ዓም ድረስ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ በጥልቀትና በስፋት ተወያይቶበታል። ዉይይቱ በአጠቃላይ አገራችን ያለፈችበትን ፈተና አሁን ያለችበትን ዉስብስብ ዘመን እና ወደፊት ሊከሰቱ ይችላሉ ብሎ ዬገመታቸዉን ስጋትና ተስፋ የተቀላቀሉባቸዉን ሃሳቦች አንሸራሽሮአል:: ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብና መረጃዎችን በመለዋወጥ ጥልቅ ዉይይቶችን አድርጓል። የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ በተለይም አሸባሪው ትነግ በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ ስለጀመረው ወረራና እንዲሁም እሱን ተከትሎ ስለመጣው የአገር ዉስጥ አደናጋሪ አሰላለፍና የውጭ ሀይሎችን ጣልቃ ገብነትን ያጤኑ ኃሳቦች ተስተናግደዋል:: ትኩረት ከተሰጠባቸው ጉዳዮች መካከል ስለ አማራና ኦሮሞ ብልጽግና ግንኙነት እና ስለ አማራ ሀይሎች አደረጃጀት ናቸው::
ስብስቡ ካካሄዳቸው ተከትያታይ ስብሰባዎች በኋላ መደምደሚያ ላይ የደረሰበትን የሚከተለዉን ሃሳብ ለኢትዮጵያ መንግስት፤ ለአማራ አስተዳዳሪዎች፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝባችን እንዲገለጽና ሁሉም በያሉበት ለሃገራችን ደህንነት፣ ነጻነት፣ አንድነት፣ እኩልነትና ለሚቀጥለው ትዉልድ ሲሉ፤ ጸረ ህዝብ (ጸረ ዲሞክራሲ) አፍራሽ አሰራሮችን እንዲያስወግዱ እንደሚከተለው አሳስቧል።
፩) ስለአማራና ኦሮሞ ብልጽግና አሰላለፍ (ግንኙነት):
ምንም እንኳን አዲሱ መንግስት የተመሰረተው በቅርብ በመሆኑ ለመተቸት ጊዜው ባይሆንም ባለፉት ሶስት አመቶች በግልፅ እንዳየነው አብዛኛውን ሃገር ወዳድ ህዝባችንን የሚያሰጋው በአማራ ብልጽግናና በኦሮሞ ብልጽግና መካከል ያለው ያልተገራ ግንኙነት ነው። በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የሚታየው መርህ አልባ ግንኙነት የአገር አስተዳደርን ህግና ስርአት ያልተከተለ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች ተመልክተናል። ብዙዎች በማስረጃ እየተደገፉ እንድሚገልጹት አማራ ብልጽግና ኦሮሞ ብልጽግና የወሰነዉን ወይም የሚፈልገዉን ፖሊሲና ሌሎች ቁልፍ የሃገራችንን ጉዳዮች ከማስፈፀም ዉጭ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በሂደቱ በመሪነት ስለማይሳተፍ ሌላ መዘዝ ሳያስከትል እና አቅጣጫዉን ሳይስት ባስቸኳይ ሊታረምና ሊስተካከል ይገባዋል::
ይህ አግባብ ያልሆነና አለመተማመንን የሚፈጥር አሰራር ተወግዶ ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ እዉቀት ልምድና የሃገር ፍቅር ያላቸዉን ባለሙያዎች በማሳተፍ ካልተሰራ ለዉጭ ጠላቶቻችን መግቢያ በር ከመሆኑም በላይ ህዝባችን እርስ በርሱ እየተባላ በድህነት እየማቀቀ እንዲኖር ያደርገዋል። አሸባሪው ወያኔ በከፈተው ጦርነት እና በተጨማሪም በኦሮሞ አካባቢ በተከሰተው ህግ አልባነት የተነሳ የአርሶ አደር አማራ ገበሬና ንፁህ የከተማ ኑዋሪ መገደል፣ መፈናቀል፣ መሰደድና መሰቃየትቱ በመራዘሙ ብዙ አለመተማመኖችን እና መቃቃሮችን ስለሚፈጥር ባስቸኩዋይ ካልቆመ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት፣ አንድነት፣ ሰላም እና ተረጋግቶ ለመኖር ጠንቅ ይሆናል:: ይህ ግፍ ለሌሎች ነገዶች ጭምር “ነግ በኔ” ስለሆነ በእንጭጩ ከአማራው ጎን በመቆም ማዉገዝና መታገል አለባቸው!!!
፪) የአማራ ሀይሎችን እና የአስተዳደር መዋቅሮችን በሚመለከት
ከዘረኛው ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራው የወያኔ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ መገለልና በደል ተፈጽሟል። ይህ በህገ መንግስት ተብየው ላይ ሳይቀር በግልፅ የተቀመረና በመተግበር ላይ የሚገኝ አሰራር በተለይ አማራው እንዲያንገፈግፈዉና ከዚህ አይነት አዋራጅ ስርዓት እራሱን ለማላቀቅ አማራጭ መንገዶችን እንዲፈልግ አስገድዶታል። ከነዚህም መንገዶች አንዱ ልክ ሌሎች ነገዶች እንዳደርጉት በአማራነቱ መደራጀት ቢሆንም እስካሁን ድረስ በድርጅቱ ዉስጥ በግልፅም ሆነ በድብቅ ጣልቃ እየገቡ ሰላማዊ ሂደቱን የሚያሰናክሉና ሁከት የሚፍጥሩ የዉስጥና የዉጭ ሃይሎች ታይተዋል። የአማራ አላማና አሰራር ኢትዮጵያውዊነትን ያቀፈና የሃገራችንን እንድነት የማይጋፋ እንዲያውም ለማእከላዊ መንግስቱ አጋዥ መሆኑ እየታወቀ የአማራዉን ገንቢ በሆነ መንገድ መደራጀት የሚፃረር አሰራር ሁሉ በአስቸኩዋይ ካልቆመ ሃገራችንን ወደ ማይፈለግ አቅጣጫ ሊወስዳት ስለሚችል በጥንቄ ሊታይ የሚገባ ጉዳይ ነው።
በኢትዮጵያ የአስተዳደር ስርአት ዉስጥ ጠባብ (ኦነግ) ዘረኛና አሸባሪ (ትነግ) ቡዶኖች የተሰገሰጉበት ስለሆነ መተማመንም ሆነ አብሮ ሃገርን ለመገንባት የሚታይ ጥረት የለም። በዚህም የተነሳ ወያኔ በአማራና በአፋር ኦነግ በመተከልና በወለጋ ህዝብ ላይ ያወጀው ዘረኛ እና ኋላቀር ጦርነት በዉስጥ ቅጥረኞች አማካይነት እልባት እንዳያገኝ እየተደረግ ነው የሚሉ ብዙ አሳማኝ ዘገባዎች በየጊዜው እየወጡ ነው። ይህንን በመንተራስ በርካታ ተንታኞች በመረጃ እየተደገፉ ወያኔን በአጭር ጊዜ ማሸነፍ የሚቻለው መከላከያ ሰራዊቱን የአማራዉን ፋኖ ልዩ ሃይልና ህዝባዊ ጦሩን አገር ወዳድ አማራ ሲመራው ብቻ ነው ብለው መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት ማእከላዊ መንግስቱ ያለው አማራጭ ወይ በአማራ ብልጽግናና በኦሮሞ ብልጽግና መካከል ያለዉን የእዝ ሰንሰልት ማስተካከል ወይም አማራው በክልልሉ የራሱን የወታደራዊና የደህንነት መዋቅር ፈጥሮ እራሱንም ሆነ መላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ካለው ቀዉስ እንዲያወጣ መርዳትና መደገፍ ነው።
አማራ ብልጽግና የኦነግን አስመሳይ የድብብቆሽ ጨዋታ የሚያዉቅ አይመስልም። ኦሮሞ ብልጽግናና ትነግ በዉጭ ሃይሎች እየሰለጠኑ እየታጠቁ መረጃና ገንዘብ እያገኙ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ በአላማና በእረዮተ አለም አንድ ስለሆኑ የአማራ መደራጀት ለአማራው ብቻ ሳይሆን ለደቡቡ ለምእራቡ ለምስራቁ ለአፋርና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዋስትና ነው።
ማጠቃላያ
- አማራው በራሱም ሆነ በሃገሩ ኢትዮጵያ ላይ የታወጀዉን ጦርነትና የረጅም ጊዜ ሰው ሰራሽ ቀዉስ ለማምከን የራሱን ጡንቻ በማፈርጠም እና ጠላቶቹ በጎነጎኑ ጂራፍ እራሳቸውን እንዲገርፉ በማድረግ የአካሄድ ስልትና ብልሃቱን በየጊዜው እያረመ ለረጅም ጊዜ የአሸናፊነት ትግል መዘጋጀት አለበት።
- አማራው በክልሉም ሆነ በሃገር ደረጃ የተማሩ ሃገር ወዳድ የሆኑና የዘመኑን የአሸባሪዎችን የዘረኞችንና የዉጭ ሃገር ቅጥረኞችን የሸፍጥ ፖለቲካ ጠንቅቀው የሚያዉቁ ብሩህ አእምሮ ያላቸዉን ሰዎች እየፈለገ በመሪነትና በቁልፍ የስራ ቦታዎች ላይ ማስቀመጥ አለበት::
- ወያኔ ኦነግና ፀረ ኢትዮጵትያ የዉጭ ሃይሎች በአዴፓ በኦዴፓና በፋኖ መካከል በመመሳሰል እየገቡ አማራዉንም ሆነ መላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ነጣጥለው አጣባቂኝ ዉስጥ ለመክተትና እርስ በራሳችን ለማባላት ዉዥንበር ለመፍጠር በከፍተኛ ደረጃ እየተፘሯጡ ስለሆነ፤ የህዝብ መገናኛ ባለቤቶችና ግለሰቦች ነገሩን ሳናጣራ ሃገራችንን ከሚያጠፉ ቡድኖች ጋር እንዳንተባበር ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠበቅብናል::
- የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ደህንነት እና አንድነት የሚጋፉ አሸባሪና ዘረኛ ሃይሎችን ማወቅና ያለማሰለስ አቅም ማሳጣት።
- የተማሩ የአማራ ሊቆችን እና በልምድ የበለፀጉ አባቶችን እየሰበሰቡ በመምከር አቅጣጫ መያዝ::
- ወጣቱን ኢትዮጵያዊነቱን ሳይለቅ በመከላከያ በልዩ ሃይል በፋኖ እና በደጀን (ተጠባባቂነት) ማሰልጠን። ስለሃገሩ ያለዉን ንቃተ ህሊና ከፍ ማድረግ።
- በወሎ፣ በጎንደር፣ በወለጋ፣ በመተከልና በአፋር በአሸባሪዉ ወያኔና ኦነግ ተወረው የሚሰቃዩትን ወገኖቻችን ነጻ ማዉጣጥና እንዲቋቋሙ መርዳት!
- ወያኔ ሰዉን ብቻ ሳይሆን እንስሳትን ጭምር እየጨፈጨፈና ታሪክንም ሆነ መረጃን እያዛባ ስለሆነ በዚህ ግምባር በሚደረገው የዘመኑ የዉስጥ መረብ ዘመቻ ህዝባችንን እና ሃገራችንን መደገፍ!
- በአማራና በኦሮሞ ብልጽግና ወይም በፋኖና በአዴፓ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች አገር ወዳድ በሆኑ ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች በሰከነ መልክ እንዲፈቱ ማድረግ!
- አማራዉ ለረጅም ጊዜ አብሮ ከኖራቸው ነገዶች ጋር የተጋባና የተዋለደ በመሆኑ፤ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምእራብና በምስራቅ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የተወሀዱ ወገኖች አሉት። በመሆኑም እራሱን ብቻ ሳይሆን ይህንን ግዙፍ ህዝብ ይዞ ከሌሎች ሰላምና እንድነት ወዳድ ህዝቦች ጋር በመሆን ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን የመጠበቅና የማረጋጋት ሃላፊነቱ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ሌሎች ነገዶች ተረድተው ለጋራ ጥቅም እንዲተባበሩ ማበረታታት አለብን::
- ሁሉም ባይሆኑም አባዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች መረጃ በማቀበል የህዝባችንን እንድነትና ደህንነት አደጋ ላይየሚጥሉ ስራዎች ሲያከናዉኑ መያዛቸዉን እና እነሱም በግልፅ ሲዝቱ ይሰማሉ። ፖለቲካ በይሉኝታ አይሰራም! ሁኔታው እስከሚጣራ ድረስ በመሃል ሃገር ያሉ የክልሉ ተወላጆች ቁልፍ ከሆኑ መስሪያ ቤቶችና እገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ዉስጥ ማንሳትና ሁኔታዎች እስከሚለይላቸው ደመወዝም እየተከፈላቸው ቢሆን፤ አደጋ ለመጣል በማይችሉባቸው ቦታዎች ቢመደቡ ወይም በጥንቃቄ ክትትል እየተደርገባቸው አርፈው ቢቀመጡ መልካም ነው። ትልቁ ችግር አዴፓ የወያኔና የኦነግ ስዉር የፖለቲካ አካሄድ በፍፁም ሊገባው አይችልም።እስካሁን ድረስ የአማራ ክልል የፀጥታ ቢሮ በወያኔዎች የተበከለ ነው ይባላል። ስለሆነም ከአሸባሪው ወያኔ ጋር የሚደረገዉን ጦርነት በአጭር ጊዜ ለማሸነፍ ከዘመቻው በፊት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአካባቢውን ደህንነት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አለበት።
- ትነግ የኢትዮጵያን ክብር፣ አንድነትና ነፃነት ለመግፈፍና ለማዋረድ ሲል የቀመረው ከፋፋይ ህገ መንግስት የሰፋው ፀረ ኢትዮጵያ አዋራጅ ባንዲራና ህገወጥ ካርታዎች በሚያሳፍር ሁኔታ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለ ፍላጎቱ እስካሁን ድረስ ተጭነዉበት ይገኛሉ። ወያኔን አሸባሪ እያሉ ወያኔ ጽፎ የሰጠዉን ህገ መንግስት ሰንደቅ አላማና ኢትዮጵያዉያን እርስ በርሳችን እየተጋደልን እንድንኖር ተስሎ የተሰጠንን የክልል ካርታ ታቅፈን ኢትዮጵያን ወደ ሰላም፣ አንድነትና እድገት ማሻገር ስለማንችል ይታሰብበት::
- የአማራ ብልጽግና አማራውን በአግባቡ መምራት የማይችል ደካማ ድርጅት መሆኑን ብናዉቅም በዚህ አስቸጋሪ የወያኔ ፀረ አማራ ወረራ ወቅት አዴፓን መቃወም ህዝባችንን አጣብቂኝ ዉስጥ ሊያስገባው ስለሚችል እንደ ስልት ተደርጎ ሁሉ አማራ/ኢትዮጵያዊ ከአሸባሪው ወያኔ ጋር የሚደረገውን ጦርነት በመደገፍና በማበረታታት ከተበዳዩ የአማራና የአፋር ህዝብ ጎን መቆም አለብን።
ሰላም እኩልነትና እድገት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝባችን!!
ለተጨማሪ ማብራሪያ የድርጅቱን ድረገፅ ከፍተው ይዩ https://edcbcuk.com/
የኢትዮጵያ መወያያና የአቅም መገንቢያ ማእከል (ኢመአመማ)
Ethiopian Discussion and Capacity Building Centre in the UK (EDCBC UK)
ለንደን እኢአ ጥቅምት 25 ቀን 2014
London, 03 November 2021