ትክክል √ | ስህተት Χ |
ምን አልክ | ምን እያልክ ነው ያለኸው ? |
እኔ የምለው | እኔ እያልኩ ያለሁት |
መጣሁ | መጣሁኝ |
አለሁ | አለሁኝ |
ሄድኩ | ሄድኩኝ |
መጣሁ ወይም እየመጣሁ ነው | እየመጣሁኝ ነኝ |
ሰንደቅ ዓላማ | ባንዲራ |
የግድ ነው (ግዴታ ነው) | ግድ ይላል |
ማሰላሰል | ማንሰላሰል |
ጎታ | ጎተራ |
እንጥፍጣፊ | እንጭፍጫፊ |
ቢላዎ | ቢላ |
አስበን (አስበንበት) | ታሳቢ አድርገን |
አወንታ | አሉታ |
እሽታ | አወንታ |
ዓይነ ዉሃው አላማረኝም | የዓይኑ ቀለም አላማረኝም |
ማስካካት | ማሽካካት |
ከሙከራ/ከልምድ | ተሞክሮ/ተመክሮ |
ንግግር መናገር:- ለአንድ ውይም ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚደረግ የቁም ነገር ንግግር | ወሬ ማዉራት: የተረጋገጠም ይሁን ያልተረጋገጠ ተራ ወሬ ማዉራት |
ስለ ዓማርኛ ቁዋንቁዋ ጥራት ዉይይትና ሃሳብ መስጫ
አማርኛን ከእንግሊዝና ጋር እየቀላቀሉ መናገር በጣም አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ አብዛኛው አዳማጭ የተናጋሪዉን ሃሳብ አይረዳዉም። እንዲያዉም አንዳንድ ጊዜ አዋቂ መስለው ለመታየትም እንደሆነ እንጃ ትሩጉሙን እንኩዋን በደንብ ሳያዉቁ የእንግሊዝኛ ቃሎች እየጨመሩ ህዝብን የሚያደናግሩ ደካሞችም አሉ። አልፎ አልፎም አንዳንድ ሰዎች የተሳሳተ አማርኛ ሲነገር እየሰሙ ያንኑ የተሳሳተ ቃል በመያዝ በአደባባይ ያወሩበታል ወይም ይጽፉበታል።
እርግጥ ነው አማርኛ በደንብ የማይችሉ በዉጭ ሃገር ተወልደው ያደጉትን ወይም ደግም አልፎ አልፎ አግባብ ያለው ትርጉም አጥተው ጣል ካደረጉ በሁዋላ ማብራሪያ የሚሰጡትን ልንታገሳቸው እንችል ይሆናል። እንግሊዝኛ በአለም ውስጥ ከፍተኛ ህዝብ የሚናገረው ቋንቋ ከመሆኑም በላይ ለመረጃ መሰብሰቢያ ለምርምርና ለዉጭ ግንኙነት አስፈላጊ ስለሆነ መማርና ማወቁ በጣም ተቃሚ ነው።
ነገር ግን አማርኛን በደንብ እየቻሉ ለትልቁም ለትንሹም የእንግሊዝኛ ቃል ማስገባት ያስገምታልና ሁላችንም ልናስብበት ይገባል። አማርኛ ከሁሉም ቁዋንቁዎች ቀደም ስለሆንና የራሱ ፊደሎች ስላሉት የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የሰውን ልጅ ታሪክ ከመንፈሳዊ ሃይል ጋር አያይዞ የዚህን ዓለም ሚስጥር ለማወቅ ስለሚረዳን በጥልቀት መማር አለብን። በተረፈ ይህንን ድረገጽ (ብሎግ) በመጠቀም አሁን ያለው ትዉልድ የሚናገረውን የተሳሳተ አማኛ እያረምን ለሌሎችም እናስተምር። ይህም መማሪያ ገጽ የባህልና ቱሪዚም ሚንስቲር ለሚሰራው ስራም አጋዥና መረጃ ማግኛ ይሆናልና ያለውን እዉቀት ሁሉም ሰው ያካፍል።የጥንት ኢትዮጵያዉያን የመማርና የማስተማር ስርአት