እሱን ተይ ብላችሁ አትጨቅጭቁኝ
ያለሱ ለመኖር እኔ አይቻለኝ
ይሁን አመል ካለው ለኔ ከሆነኝ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
እሱን ተይ ብላችሁ አትጨቅጭቁኝ
ያለሱ ለመኖር እኔ አይቻለኝ
ይሁን አመል ካለው ለኔ ከሆነኝ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ታጨች ታጨች ብለው እሷን ሊድሯት
ታገባለች ብለን ስንጠብቃት
ሴሰኛ አርጎ ያጫት ቆማ አስቀራት
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ጉልቻው ተሰብሮ ከጎደለ አንዴ
አዲስ ልግዛ እንጂ ለድስት ለምጣዴ
ቀን ጠብቂ ይጠገን ትላላችሁ እንዴ
መሸ ነጋ ገሉ አይጠቅምም እንግዴ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ፊተኞች ኋለኞች ሆነና ተረቱ
የተገላቢጦሽ እንዲባል ድርጊቱ
ያጨለማ ነበር ያገባው መብራቱ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
በዝናቡ ጭጋግ ይጠቁራል ሰማይ
ክረምቱ ሲያበቃ ስትወጣ ፀሀይ
መስከረምንና አመጣን አደይ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ጉች ጉች ቢልም ጡቱ ከደረት
ካልተወለደበት አይወጣው ወተት
ለምንም አይጠቅም ሁሌም ያዳምጡት
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ከሠዎች ሸሽቼ ዝም ብዬ ሲያዩኝ
አውራ አውራ ብለው አደፋፈሩኝ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
የህመምስ ነገር በምን ይደበቃል
ገልጠው ባያወሩት በመልክ ያሳብቃል
ይሄ ነው ህመሜ ባትል ባንደበቷ
እኔስ ተረዳኋት አይቼ ግርጣቷ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ፈጣሪ ልክ ነው እንዳታማርሩት
ስለሁሉም ነገር እውነተኛ በሉት
በአፍ ብቻ ሳይሆን በልባችሁ አትሙት
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ጠብቄሽ ነበረ በብርድ በክረምቱ
በመስከረም ቀረሽ ምንድነው ምክንያቱ
እምቢ አልመጣ ያልሽው ያለጥቅምቱ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ቁምነገር ሳይሰሩ አለቀ ዕድሜያቸው
ከረፈደ ወዲያ ዛሬ ቢቆጫቸው
ምን ያደርጋል ዛሬ ያመጣደፋቸው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ሲጀመር ከማህፀን ሲቀጥል በጡቷ
ልጇን ስትመግብ ለጥፋ ደረቷ
ታጥባ እሷም ትብላ ለራስ ጤንነቷ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ወገኖች ሁላችሁ ይህንን አድምጡ
የትዳር ጓደኛ አጋር ስትመርጡ
አጥንታችሁ ይሁን ኋላ እንዳትቀጡ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
እውቅናና እውቀት ተደባልቆባቸው
የጥያቄ መልሱ ገብቶ ከእጃቸው
እነዛ በለጡን በጭንቅላታቸው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
አምሮኛል አምሮኛል ማለት አብዝታለች
ኧረ ጉዷን ስሙ አርግዛልኛለች
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ከእንግዲህ ከናንተ አልሆንም ያላቸው
ፈጣሪ በነዚያ የጨከነባቸው
ሲልከሰከሱበት አይቶ በርምጃቸው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ፈጣሪ እንደሆነ ሀያልና ብርቱ
ንጉስ መሠከረ በአፉ ባንደበቱ
ምስክር ሆኖታል ደንግጦ መምጣቱ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
እምቢ ብዬ ነበር ከመጀመሪያው
መሸሽ ነበረብኝ እስከፍፃሜው
ከዳተኛንና ዓመፀኛው ሠው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ለቁርስ ብጠብቅህ ትመጣለህ ብዬ
ለምሣም ቀጣኸኝ ጨካኝ ነህ አንተዬ
ብድራቴን እንጃ ሠጋሁ አላገኝም ብዬ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ለተቅበዘበዙት በጎች እንጃላቸው
ሃላፊነት ሊወስድ አንዱ መጣላቸው
ብሎ እየማለ እኔ ልረዳቸው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
አዋጅ አዋጅ ስሙ ከማዶ እስከ ማዶ
የምስራች እንጂ አላወራም መርዶ
በጁ የገባለትን በፈቃዱ ወዶ
በተለያየሱስ አይለቅም አጥምዶ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
እግዚአብሄር ደግ ነው ደግሞም ቸር ነውና
ልጁ እንደሆነ የህይወት ጎዳና
ሚስጢሩን አስረዳኝ አብራራልኝና
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ይቅር በለኝ ማረኝ ሲለው ተንበርክኮ
እንታረቅ ቢለው ሽማግሌ ልኮ
ምነው መጨከኑ ገርሞኝ ነበርኮ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ድግሱን ሊነግረው ፀበል ቅመስ ያለው
ይሁዳ ምን ነካው ጌታስ ምን በደለው
ደግሰው ሲያጠምዱ መረብ የሆናቸው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ምንም አልጠቀመው ትልቅ ነኝ ማለቱ
አዳልጦ ጥሎታል ጉራና ትዕቢቱ
ታናሹ ቀደመው በጥበብ በስልቱ
ታላቅየው የታል ጠፍቷል በኩራቱ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
የማይረባ ሸክላ ብለው የናቁት
ማይጠቅምም እያሉ ስፍራ ያሳጡት
ተቀምጦ ታየ በማዕዘኑ ላይ
ተቀብቶ አምሮ ያኛውማድንጋይ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ቀርበን አላየናት አልሆናት ዘመዷ
ችግሯን ሳንጠይቅ ያለውን በሆዷ
ርቃን ስለሄደች እኛም አልናት እብዷ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
አንድ ነን
በአንድነት ሆነው ተስማምተው ሲኖሩ
እየተረዳዱ ተጋግዘው ሲሰሩ
በትርፋማ ህይወት ያላንዳች ኪሳራ
ክፉና መልካሙን ሲወጡት በጋራ
በረፍታቸው ጊዜ በአንዲት ቀን ጨዋታ
የአንድነታቸው ሠንሠለት ተፈታ።
አይን አፈጠጠ ሁሉን በላጭ ሆኖ
በሁሉም ላይ ጮኸ እራሱን አግንኖ
“እወቁ እኔ ነኝ የሁላችሁ በላይ
ባላስተውልና ነገሮችን ባላይ
መኖር አትችሉም የለም እኔን መሳይ”
“ማን ታላቅ አረገህ አይናማው ፈጣጣ
ብትቁለጨለጭም ብትሆን ገልማጣ
ብትቅበዘበዝም ምንም አታመጣ
እኔ ባልሰራና ባልንቀሳቀስ
ባልተገኘ ነበር ጢኖ ሚቀመስ”
“እጅ ስትናገር በደንብ አስተውላ”
አለች እመት ምላስ ቶሎ ተቀብላ
“ብታመጣም እንኳ የሚቀማመስ
አንተ አትቀምሰው እኔጂ ምቀምስ
ክፉና መልካሙን ጣፋጩን መራራ
እኔ ምላስ አለሁ ሁሉን የማጣራ”።
“በይ በይ እመት ምላስ ድንበር አትዝለይ
የማትሰሪውን አደረኩ አትበይ
ክፉና መልካሙን ለይቼ የማሸት
በተገኘሁበት ያላንዳች መታከት
የሽቶ መዓዛ የቆሻሻ ግሙ
ሲደራርቡብኝ ጉንፋንና አስሙ”
ብሎ ሳይጨርሰው ጋሽዬ አፍንጫ
ምላስ ተንጠራራች ልትመታው በርግጫ
ገላጋይ ቲፎዞ ሆ ብሎ ተንጫጫ።
ዝም ብሎ ያዳምጥ ነበር አቶ ጆሮ
ልብም አስተዋለ ሁሉንም መርምሮ
ሁለቱ አንድላይ ተመካከሩና
ፍረደን እባክህ ዳኛችን ህሊና
ብለው ተናገሩ መሪያቸው ነውና።
ታላቁ ህሊናም ነገሩን አዳምጦ
ሲመረምር ቆየ መዝገብ አገላብጦ።
አንድ ቀን ማለዳም ስብሰባ ተጠራ
ሁሉ ቦታ ያዘ ገብቶ በየተራ
ፕሬዘዳንቱም ሄደው ከመድረኩ ወጡ
ተግሳፅና ምክር መመሪያ ሊሰጡ።
“እንደምን አላችሁ ብልቶች በሙሉ
እኔንም ጨምሮ የምንሆን አካሉ
ያኔ በሰማሁት አፀያፊ ወሬ
ስብከነከነ ከረምኩኝ እጅግ ተገርሜ
ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት የት ይገኛል?
ሁሉስ ጆሮ ቢሆን ማየት የት ይገኛል?
በተለይ ምላሲት በሰራሽው ሥራ
በጣም አፍሬአለሁ ውስጤም ደሞ ፈራ
ህይወትና ሲዖል በእጅሽ እያሉ
እስቲ ተገቢ ነው ለዱላ መዝለሉ?
ይልቅ ሁላችንም ይህንን እንወቅ
የትም አያደርስም መምሰል ታላቅ ታላቅ
ለማንም አይጠቅምም ባልንጀራን መናቅ
አንድሽ ተነጥለሽ ብቻሽን ላትኖሪ
በሞኝነት ዕውቀት ሰምጠሽ አትክሰሪ”
የፕሬዘዳንቱ ድምፅ ይህን ሲያስተጋባ
ጉባዔው ተሞላ በታላቅ ጭብጨባ።
እውነት ነው ልክ ነው የምን መለያየት
ተስማምተን እኖራለን ተባብረን ባንድነት
ብለው ተታረቁ የተጣሉት ሁሉ
አንድ ነን ምንጊዜም ብለው ተማማሉ።
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ፈጣሪ እንደሆነ ሀያልና ብርቱ
ንጉስ መሠከረ በአፉ ባንደበቱ
ምስክር ሆኖታል ደንግጦ መምጣቱ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
እምቢ ብዬ ነበር ከመጀመሪያው
መሸሽ ነበረብኝ እስከፍፃሜው
ከዳተኛንና ዓመፀኛው ሠው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ለቁርስ ብጠብቅህ ትመጣለህ ብዬ
ለምሣም ቀጣኸኝ ጨካኝ ነህ አንተዬ
ብድራቴን እንጃ ሠጋሁ አላገኝም ብዬ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ለተቅበዘበዙት በጎች እንጃላቸው
ሃላፊነት ሊወስድ አንዱ መጣላቸው
ብሎ እየማለ እኔ ልረዳቸው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
አዋጅ አዋጅ ስሙ ከማዶ እስከ ማዶ
የምስራች እንጂ አላወራም መርዶ
በጁ የገባለትን በፈቃዱ ወዶ
በተለያየሱስ አይለቅም አጥምዶ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
እግዚአብሄር ደግ ነው ደግሞም ቸር ነውና
ልጁ እንደሆነ የህይወት ጎዳና
ሚስጢሩን አስረዳኝ አብራራልኝና
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ይቅር በለኝ ማረኝ ሲለው ተንበርክኮ
እንታረቅ ቢለው ሽማግሌ ልኮ
ምነው መጨከኑ ገርሞኝ ነበርኮ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ድግሱን ሊነግረው ፀበል ቅመስ ያለው
ይሁዳ ምን ነካው ጌታስ ምን በደለው
ደግሰው ሲያጠምዱ መረብ የሆናቸው
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ምንም አልጠቀመው ትልቅ ነኝ ማለቱ
አዳልጦ ጥሎታል ጉራና ትዕቢቱ
ታናሹ ቀደመው በጥበብ በስልቱ
ታላቅየው የታል ጠፍቷል በኩራቱ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
የማይረባ ሸክላ ብለው የናቁት
ማይጠቅምም እያሉ ስፍራ ያሳጡት
ተቀምጦ ታየ በማዕዘኑ ላይ
ተቀብቶ አምሮ ያኛውማድንጋይ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
ቀርበን አላየናት አልሆናት ዘመዷ
ችግሯን ሳንጠይቅ ያለውን በሆዷ
ርቃን ስለሄደች እኛም አልናት እብዷ
♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣ ♣
One thought on “በዐይናዲስ ደግፍ”
Please login to leave your messages or Contributions