ከእለታት አንድ ቀን አንድ መንገደኛ ዘመድ ለመጠየቅ ሲገሰግስ ከፍተኛ ዝናብ ጥሎ ስለነበር በመንገዱ ላይ የሚገኝ ወንዝ ሞልቶ ለመሻገር ሲዘጋጅ እባብ በፍጥነት የሚዎርደው ዎንዝ ከድንጋይና ከእንጨት ጋር ጠልፎ ይወስደኛል ብሎ ፈርቶ ሰዉየዉን “እባክህን ይህንን ወንዝ ኣሻገረኝ” ብሎ ጠየቀው። ሰዉየም “አንተ መርኛ እባብ ነህ እንዴት አምኘ ልርዳህ” ይለዋል። እበቡም እየተቅለሰለስ “እባክህን ኣሻግረኝ እኔ ዉለታ ብትዉልልኝ አመሰግንሃለሁ እንጂ ለምን እነክስሀለሁ?” እያለ በእግሩ ስር በመለማመጥ ይቅለሰልስ ጀመር።”
ሰዉየም መልሶ “ለማሻገር እንኩዋን ብፈልግ እንዴት አድርጌ ነው የማሻግርህ” በማለት ጠየቀው። እባቡ “ግድ የለም እራስህ ላይ እንደ አንገት ልብስህ ጠምጥመኝ” አለው። ሰዉየው ጥቂት ካሰላሰለ በሁዋላ “ምንም እባብ ቢሆን የእግዜር ፍጡር ነው ብረዳው ምንአለበት” በማለት እራሱ ላይ ጠምጥሞት ወንዙን እየዋኘ ከተሻገረ በሁዋል “በል እንግዲህ እሻግሬሃለሁ ከራሴ ላይ ዉረድ አለው”። እባቡም “አይ አሎርድም” አለው። ሰዉየውም ደንግጦ “አመስግኘህ እወርዳለሁ አላልክም እንዴ? እረ እባክህ ዉረድ” ቢለው “አይ ሳልነድፍህ አልወርድም:: እባብ መሆኔን እያወቅህ መጀመሪያዉኑ እራስህ ላይ ማዉጣት አልነበረብህም። አንተ ሞኝ አሁን ጠላቴን ሰዉን አግኝቼሃለሁ ስለዚህ ነድፌ እገልሃለሁ” በማለት እቅጩን ነገረው።
ሰዉየም አሰብ አድሮግ “ዉለታ ዉየልህ እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? እስቲ ሰዉም ሆነ የዱር እንሰሶች ይፍረዱና አንተ ትክክል ከሆንክ ግደለኝ” ብሎ ለመነው። እባብም መቼም አንዴ እራሱ ላይ ወጥቻለሁ ምናባቱ ይሆናል ብሎ ተስማማ። መጀመሪያ ዝንጀሮ ጋ ሄደው ሁኔታዉን ኣስረዱ ዝንጀሮም ስቆ “አንተ ሞኝ ሰው ድሮ እባብን ተንኮሉን እያወቅህ እንዴት እጭንቅላጥ ላይ አዉጥተህ ታስቀምጣለህ? ጥፋቱ ያንተ ነው ነድፎ ይግደልህ!!” ብሎ ለባቡ ፈረድ። ቅጥሎ አንበሳ ጋ ሔዱ “አንበሳዉም እንደ ዝንጀሮው በሰው ላይ ፈረደ። ድኩላና ቅጭኔ ጋም ሀዱ ሁሉ በሰውየው ላይ ፈረዱ።
በመጨረሻ እባቡ ሰዉየዉን ነድፎ ሊገለው ሲል ሰዉየው እባክህ ከመግደልህ በፊት አንድ እድል ስጠኝና ግደለኝ በማለት ለመነው። እባቡም አሁን ማን እንዲዳኝ ትፈልጋለህ” አለው። ሰዉየዉም “ቀብሮ” በማለት መለሰ። እባቡ ምን ያመጣል ብሎ “እሺ ቀበሮ የመጨረሻ ዳኛህነች አለው”። ሰዉየዉም ተስማቶ ወደ ቀበሮ አመሩ። ቀበሮም ሰዉዬ ወደሷ ጋ እያመራ መሁን አዉቃ በእርቀት ለምን እንደመጣ ጠየቀችዉ። ሰዉየዉም “ይኸዉ እግዜር ያሳይሽ አቶ እባብን ተቸግሮ አግኝቸው ወንዝ እሻገርኩት። አሁን አሎርድም ነድፌ እገልሃለሁ ጥፋቱ ያንተ ነው አለኝ። እባክሽን ፍርድሽን ስጭን” አላት።
ቀበሮም ፈንጠር ብላ “በእርግጥ እንደ እባብ ያለ ተንኮለኛና መርዘና ፍጡር እራስህ ላይ አዉጥተህ መጠምጠም አልነበረብህ። ግን ከመፍረዴ በፊት አንድ ጥያቄ አለኝ አለች ቅበሮ። እባብና ሰዉም ጥያቄዉን ለመመለስ ተስማሙ። ቀብሮ እንዲህ አለች “አቶ እባብ ሰዉየዉን ከወንዝ ዳር ስታገኘው እንዴት ነበር ብላ ጠየቀቻቸው”። እባብም እንዲህ አለ “እሱ እየገሰገሰ ወደ ወንዙ ሲዎርድ እኔ አንገቴን ቀና እድርጌ እንዲያሻግረኝ ጠየቁት” በማለት መልሰላት። ቀበሮም ፈጠን ብላ እስቲ እንዴት እንደነበርክ ዉረድና ኣሳየኝ አለችዉ። እባብም ዱብ ብሎ ዎርዶ አገቱን ቀና ሲያደርግ። ቀበሮ ሰዉየዉን እያየች “ሰው ምን ትጠብቃለህ እባብ ከእግርህ ዱላ በጅህ” ስትለው ወዲያው ነቅቶ እባቡን እራሱን በያዘው ዱላ ቀጥቅጦ ገደለው ይባላል።
ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ
ይቀጥላል።
ቀበሮና ሰው