ኢትዮጵያዉያን በቡድን 7 የአለም መሪ አገሮች ስብሰባ ላይ የአማራን የዘር ፍጅት በማዉገዝ ድምጻቸውን አሰሙ እንግሊዝ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በቡድን 7 የአለም መሪ አገሮች ስብሰባ ላይ የአማራን የዘር ፍጅት በማዉገዝ ኮርንወል አይቪስ ከተማ ተገኝተው ድምጻቸውን አሰሙ። የአካባቢው ህዝብም ድጋፉንም ለሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከመግለጹም በላይ ለታሪካዊዋና ለነጻነት ምልክቱዋ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ሰንደቅ አላማ ማክበሩንና መዉደዱን በከፈኛ ስሜት ገልጾአል።