ወያኔ በጎጃም አማራ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግፍ በመፈጸም ላይ ይገኛል :: ባለፈው ሳምንት በተጀመረው ሰላማዊ ሰልፍና የእምቢ አልገዛም እንቅስቃሴ እስካሁን ወያኔ በጎጃም አማራ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግፍ በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ የሚደርሱን መረጃዎች አረጋግጠዋል::
ባህርዳር ላይ የተገደሉ ፫፰ ሰምዐታት ፎቶ እና ሌሎች መረጃወች መሰብሰባቸዉን የተለያዩ የህብረተሰብ ዜና ማሰራጫዎች ገለጹ።
መረጃዎቹ እንደገለጹት እስካሁን ፩፬፫ ቁስለኛ ፺ የሚሆኑ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆኑ ህፃናት እና ሴቶች የዚህ አሳዛኝ ሁዋላቀርና ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሰለባ ሆነዋል። ህዝቡም ይህንን ወራዳ የወያኔ ግፍ ለማቆሞ መቁረጡ ታዉቆአል።