የዓማራ ታሪክ ባጭሩ: ትንሽ ስለ አማራው የሰሎሞን ስረወ መንግስት
ከክርስቶስ ልደት በፊት ጣናና የረር (ሸዋ) አካባቢ የነበሩ አማሮች በጌምድር (ጎንደር) ላይ በከብት እርባታና በእርሻ ከበሩ። ከዚያም ንግድ ጀምረው ስለበለጸጉ ወደ ባህር ለመጠጋት አክሱምን መሰረቱ። አክሱም ላይም በአለም ገናናዉን መንግስት መስርተው ረጅም ዘመን በተድላና በደስታ ኖሩ:: ከአክሱም በአካባቢው የእስልምና መስፋፋትና በዮዲት አመጽ ምክንያት የንጉሳቸዉን ልጅ አንበሳ አዉድምን ይዘው እየተዋጉ መጥተው መረሃቤቴ ላይ ሰፈሩ።
መርሃቤቴ ላይ ከፍተኛ ዉጊያ ተደርጎ ዮዲት ከተደመሰሰች በሁዋላ ተመልሰው አክሱም ላይ 40 አመት ነግሰው ቆዩ:: ይሁንና የሰለሞን ስርወ መንግስት በመዳከሙ የዛጉየ ስርወመንግስት ሲያስተዳድር ቆይቶ በሁዋላ በሽምግልና ዘዉዱ ለሚገባው ለሶሎሞናዊዉ ስርወ መንግስት በሰላም ተላለፈ። ከዚያም ይሄው የሶሎሞን ስረወ መንግስት ሸዋ (መንዝንና ተጉለት) ላይ ሆኖ ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን ካስተዳደረ በሁዋል የግራኝ መሃመድ ወረራ በአጼ ልብነድንግል ዘመን ተካሄደ።
አጼ ልብነድንግልም የቅድም አያቶቻቸዉን ሃገር ያዉቁ ስለነበር እየተዋጉ በጌምድር ገቡ (ስሙ እራሱ ለምን እንደተቀየረ አላዉቅም):: ከዚያም ግራኝ ከሁዋላ ሆኖ እየተዋጋ ስለተከተላቸው አጼ ልብነድንግል ደብረዳሞ ተራራ ላይ ሆነው ዉጊያው ቀጠለ። ይሁን እንጂ ግራኝ በቱርኮችና (Ottoman empire) እየታገዘ የሚቻል አልነበረም:: ዐጼ ልብነድንግልም በዚያን ጊዜ ክርስቲያን ከነበረችዉ የፖርቱጋል ንጉስ ጋር አንድነት ለመፍጠር ደብዳቤ ጻፉ። የፖርቱጋሉም ንጉስ በሁነታው በጣም አዘነ (በዚያን ጊዜ ኤሮፕ ዉስጥ ኢትዮጵያ “የቅዱሳን ሃገር” ተብላ ነበር የምትታወቀው)።
የፖርቱጋሉ ንጉስ ኢማኑአልም ቤተክርስቲኣን ሄዶ ለኢትዮጵያ ከጸለየ በሁዋላ በክርስቶፈር ዳጋማ (ህንድን ያገኘው የቫስኮ ዳጋም ልጅ) የሚመራ ምርጥ ጦሩን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ በባህር ንጉስ (ዛሬ ባእዳን ባወጡላት ስም ኤርትራ የምትባለው) ኢትዮጵያ ግዛት ሲደርሱ የአካባቢው ሃገረገዥ የሚሸኙአቸው አጃቢ ሰጥተው ወደ ጎንደር አመሩ። ይሁን እንጂ ንጉሱ በህመምና በርጅና አርፈው ስለነበር ባለቤታቸው እቴጌ ሰብለወንጌል ጦሩን ተቀብው አስተናገዱ።
በዚያን ጊዜ ልጃቸው አጼ ገላዉዲዎስ ሸዋ ዉስጥ በድብቅ ተቀምጦ ጦር እየመለመለ ነበር። ክርስቶፈር ዳጋማም የኢትዮጵያና የፖርቱጋል ወታደሮች ጦርነቱን እንዲጀምሩ ፈለገ። የግራኝን አቅም የሚያዉቁት እቴጌ ሰብለወንጌል ግን ለክርስቶፈር ዳጋማ ልጃቸው ተጨማሪ ጦር ከደብረብርሃን ይዞ እስከሚመጣ ዉጊያው እንዳይደረግ ሃሳብ አቀረቡ።
ነገር ግን ክርስቶፈር ዳጋማ ጦሩ ያለስራ በመቀመጡና ምግብና ዉሃ አቅርቦቱ እንዳይረዝም ብሎ ዉጊያውን በጀግንነት ሲያካሂድ ከቆየ በሁዋላ በግራኝ እጅ ዉስጥ ገብቶ ግራኝ በጭካኔ አንገቱን በመቅላት ወረወረው። ንግስት ሰብለወንጌል የፈሩት አልቀረም ኢትዮጵያና ፖርቱጋሎች በቱርክ መሳሪያ ተሸነፉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የልብነድንግል ልጅ አጼ ገላዉዲዮስ ከሸዋ ተጨማሪ ጦር ይዞ ጎንደር ገባ። የፖርቱጋሉም ጦር የተረፉትን ወታደሮችና መሳሪያዎች አሰባስቦ ከሸዋ ከመጣው ጦር ጋር አቀናጅተው ግራኝን ጎንደር ዉስጥ ወይና ደጋ በሚባል ቦታ ላይ ገጠሙት። ጀግኖቹ ኢትዮጵያዉያንና የፖርቱጋል ጦር የቱርክና የኦቶማንን መሳሪያ ድጋፍ የሚያገኘዉን ግራኝን ብትንትኑን አወጡት።
ከዚያ በሁዋላ ነው እንግዲህ የሰሎሞን ስርወ መንግስት ጎንደር ላይ ተመስርቶ ብዙ ታሪክ ያስመዘገበዉን እምየ ጎንደርን የገነባው። ከዚያም እንደገና ጎንደር ቤተመንግስት ዉስጥ በአሽከርነት ተቀጥሮ ሲሰራ በነበረ አንድ ስኡል በሚባል ትግሬ የተነሳ ኢትዮጵያ ተመሰቃቀለች:: ወደ ጎጥ ወረደች። ያም “ዘመነ መሳፍንት” ይባላል። ዘመነ መሳፍንትን ያንበረከኩት አጼ ተዎድሮስ በበዝብዝ ካሳ (የትግሬው ዮሃንስ) ክህደት ከተገደሉ በሁዋላ ኢትዮጵያ የነበራት ስርአት እየፈረሰ በጎጃምና በወሎ ወገኖቻችን ላይ ዮሃንስ የሚዘገንን ጭካኔና ብዝበዛ አካሄደ።
ቀጥሎም የትግሬዉ ዮሃንስ ከእንግሊዞች ጋር ሆኖ ሱዳንን ነጻ ለማዉጣት የሚታገሉ ድርቡሾችን ስለወጋና ብዙ ህይወት ስላጠፋ ሱዳኖች ተናደው ሊወጉትና ሊበቀሉት መምጣታቸዉን ሰምቶ ወደ መተማ አመራ። ጦርነቱ ተጀምሮ ሰአታት ሳይቆጠሩ የሱዳን ድርቡሽ ዮሃንስን በመግደልና አንገቱን በመቀላት ተጠናቀቀ። የሱዳን ድርቡሾች የዮሃንስን አንገት በመቁረጣቸዉና ጎንደርን ሊያጠቁ ይችላሉ በማለት ምኒልክ ጦራቸውን ከተቱ (ሱዳንን ለመደምሰስ ተዘጋጁ)። ድርቡሾች የሸዋን (የምኒልክን) ጦር አይበገሬነት ስለሚያዉቁ የዮሃንስን አንገት ይዘው እየጨፈሩ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ። ምኒልክ ሱዳን ወደመጣበት መመልሱን ሲሰሙ ህዝቡን አረጋግተዉና አስተባብረው የሰሎሞን ስረመንግስትን መልሰው መስመሩ ዉስጥ አስገቡት:: ታላቁ ንጉሰ ነገስት ምኒልክ የሰሎሞንን ስረወ መንግስት መቀመጫን ከደብረ ብርሃን ወደ አንኮበር አዛዉረው በመጨረሻ የአያቶቻቸዉን ፈለግ በመከተል ዛሬ ሁሉንም ሰብስባ የያዘችዉን ጥንቱዋን የዳዊት ከተማ (በረራን) አዲስ አበባን እንደገና በመመስረት የኢትዮጵያ ማእከል አደረጉዋት።
እዉቀት ዓለሙ