የአማራ/የኢትዮጵያ አኩሪ ሰንደቅ አላማ

የአማራንና ቀሪዉን የኢትዮጵያ ህዝብ በሃይል ለማዋረድና ቅስም ለመስበር በወያኔ የተጫነው ጸረኢትዮጵያ ባንዲራ መለወጥ አለበት። ኢትዮጵያዊው አማራ በዉጭ ሃገር ቅኝ ያልተገዛ ስለሆነ አዲስ ሰንደቅ አላማ አያስፈልገዉም። አዲስ ሰንደቅ አላማ የሚያስፈልጋቸው በባርነት የተገዙና ቀደም ሲል ሰንደቅ አላማ ያልነበራቸው ሃገሮች ነጻ ሲወጡ ነው። ስለዚህ የአማራ ህዝብ ሰንደቅ አላማ አረንጉዋዴ ብጫ ቀይ ሲሆን ምስሉ ደሞ አንበሳ ነው። ክልል ተብለው የተፈጠሩ አካባቢዎች ባንዲራቸውን እንደፈለጉ ነው የቀረጹት። ወያኔና ኦነግ ባንዲራቸዉን ሲቀርጹ የአማራን ወይም የደቡብን ህዝብ አማክረው አይደለም። የአማራ ክልል አረንጉዋዴ ብጫ ቀይ ሰንደቅ አላማን ተቀብሎ ወደ ቦታዋ ከመለሰ መላው የአማራ ህዝብ በሙሉ ልብ ይደግፈዋል። ይህ የመጀመሪያ በጎ አማራን የማክበር እርምጃ የክልሉን መንግስትና ህዝብ የሚያቀራርብና አብሮ መስራትን የሚያበረታታ ይሆናል።

Amhara Ethiopian Flag
Amhara Ethiopian Flag

በተጨማሪ ይህ የአማራ ክልል ፈርቀዳጅ እርምጃ ሌሎች ክልሎች የኢትዮጵያን ህዝብ ታሪካዊ ድል አድራጊ የሰላምና የነጻነት ምልክት የሆነችዉን ሰንደቅ አላማ ወደ ነበረ ክብሩዋ ሊመልሱዋት ይችላሉ። ሌላው መታወቅ ያለበት ጉዳይ የአማራ ክልል ዋናዉና ትልቁ የፌደራል መንግስቱ አካል ስለሆነ የፌደራል መንግስቱ ሰንደቅ አላማም የአብሮነትና የኢትዮጵያን የተለያዩ ብሄረሰቦች የጋራ ታሪክ ቁርኝትን የሚያመለክት እንዲሆን ጠንክሮ መስራት አለበት። የፌደራል መንግስቱም ሰንደቅ አላማ ቢሆን የአማራ ህዝብ ካልተስማማበት ሊጸድቅ አይችልም!! የኢትዮጵያዉያንን የቆየ አንድነትና ነጻነት የሚያንቁዋሽሽ ሰንደቅ አላማ በምንም አይነት የፈደራል መንግስቱ ሰንደቅ አላማ እንዳይሆን ህጋዊ በሆነ መንገድ መገታት አለበት። ክልሎች የዉስጥ አስተዳደራቸውን ያከናዉኑ ማለት ለአማራም ጭምር እንጅ ሌሎች በአማራ ጉዳይ ሲሆን እየገቡ ይዘባርቃሉ ማለት አይደለም።

ለማጠቃለል:-

፩) አማራ የራሱን ሰንደቅ አላማ ህዝቡን በማሳተፍ በወሮበሎች የተነጠቀውን የአባቶቹን የነጻነት ምልክት አረንጉዋዴ ብጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ወደቦታው ይመልስ።

፪) የፌደራል መንግስቱ ወደ ነበረበት ህጋዊውና የአፍሪካ የነጻነት ምልክቱ አረንጉዋዴ ብጫ ቀይ ሰንደቅ አላማው ከተመለሰ የአማራው ሰንደቅ አላማ አንበሳ በመጨመር ከፌደራል መንግስቱ ጋር ትንሽ ልዩ እንዲሆን ማድረግ ይችላል። ይህ ከሆነ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ኢትዮጵያ ዉስት ሰላምና መረጋጋት ይፈጠራል።

፫) ሌላው አማራ መጠንቀቅና ጠንክሮ መስራት ያለበት በፌደራል (ሃገር አቀፍ) ሰንደቅ አላማ ላይ ነው። ያለ አማራ ስምምነት ፈደራል መንግስት ዉስጥ ያሉ ጥቂት ጥንፈኞች ባለፈው እንዳደረጉ የራሳችዉን ከፋፋይ ባንዲራ በኢትዮጵያ ህዝብና በሌሎች ክልልሎች ላይ ድጋሚ ለመጫን ቢሞክሩ በምንም አይነት ልድገመው በምንም አይነት አማራ መስማማት የለበትም። ከ80% በላይ ህዝብ ያልተቀበለውን ርኩስ ባለኮከብና ባለግብረ ባለጌ ቀለም ባንዲራ አማራው ብቻም ሳይሆን ሌሎች የሃገራቸውን አንድነትና ነጻነት የሚወዱ የደቡብ ህዝቦችና ሌሎች ነገዶች ሁሉ ማሶገድ አለባቸው።

ሌሎች አናሶች ክልላችን ዉስጥ ሌላ ሰው መኖር የለበትም እያሉ የሰዉን ልጅ እስከመግደል ነጻነት ሲያገኙ አማራ ለምን ብሎ ነው በፌደራል ዉስጥ ያለዉን የራሱን ነጻነትና ድርሻ እያሳለፈ ሌሎች በሱ ሃገራዊ መብት ላይ እንዲወስኑለት የሚፈቅደው????? አማራ ከእንግዲህ በሚወክለውና ባመነነበት ሰንደቅ አላማና ህግ ብቻ ነው መተዳር ያለበት።  ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም ብሎ አማራ የራሱን ህዝብ አሳርዶአል። ገንዘቡን ተዘርፎአል። ክብሩን አስነክቶአል። ትልቅ ሆኖ በትንንሾች ተገዝቶአል። ከእንግዲይ ከመገደል ከመዘረፍና ከመዋረድ ሌላ ነገር ስለማይመጣ በመርህ ላይ ቆሞ የአማራን አስተዳደር ስል ጣን ሳይሸራርፉ መጠቀም ያስፈልጋል። በዚያ ባረጀና ባፈጀ የማታለያ መንገድ ይሄ ካልሆነ እገነጠላለሁ ማለት ለአክራሪ ተገንጣዮች መከራን እንጂ ደስታን ሊያመጣላቸው አይችልም።

ድል ለአስተዋዩ ነጻነትና ፍትህ ወዳዱ ዓማራና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ!!