በኢትዮጵያ የሲቪልና የወታደር የማዕረግ ስሞች!!!
እነ አያ እንቶኔ የእኛ የሆነው ሁሉ በቀና አይታያቸውም የማጥላላት ልክፍታቸው ይነሳባቸዋል እንከፍ ሁላ። የድሮ ስራት ናፋቂ ትሉ የለ ይሄን የመሰለ የማዕረግ ስም ባንናፍቅ ነበረ የሚገርመው። እወን የመሳፍንትም በሉት የአፄዎች ስራት የእኛው ከእኛው ከራሳችን ነበር ከሄትም በቅኝ ገዥዎች አልገባም፣ የእኛው የራሳችን የአባቶቻችን የማዕረግ ስሞች ነበሩን። ይሄው አሁን ሰርጅን፣ ኮንስታብል፣ ምናምን ምናምን ትሉ የለም ከእንግሊዝ ገልብጣችሁ። እውነት ነው ጀግኖች አባቶቻችን ግን የራሳቸው ነበራቸው።
ጀግኖቹ አባቶቻችን የጦርና የሰቪል የማዕረግ ስሞች በአሁኑ አቻ አነጋገር ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ሞክሩ፣ ሌሎች የተረሱ ካሉም ጨምሩበት።
#ዐጼ (ንጉሠ ነገሥት)
#እቴጌ (የንጉሠ ነገሥቱ ባለቤት)
#ንግሥት ( ንጉሠ ነገስቷ)
#አፈ_ንጉስ ፦ ቃል በቃል ሲተረጎም የንጉሱ አንደበት ማለት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ አቻ ትርጉም ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጋር ተመጣጣኝ ስልጣን ሊሆን ይችላል።
#ራስ፦ መሪ ማለት ሲሆን በንጉሱ ግዛት ውስጥ በሹመት ራሱን ችሎ የሚያስተዳድርና የሚመራው ግዛት ያለው ባለማዕረግ ማለት ነው።
#ቢትዎደድ፦ በንጉሱ የተወደደ ማለት ሲሆን የንጉሳዊ ቤተሰብ አካል ላልሆነ ሰው የሚሰጥ ከፍተኛ ማእረግ ነው፣ በደረጃ ከራስ ቀጥሎ ማለት ነው።
#በጅሮንድ፦ ለገንዘብ ጉዳዮች ኃላፊ የሆነ ሹም የመንግስት ገቢና ወጪን የሚቆጣጠር ማለት ሲሆን በአሁኑ አጠራር ከገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ስልጣን ነው።
#መርድ_አዝማች፦ በወታደራዊ ትርጉሙ አዛዥ አዝማች ማለት ሲሆን ወደ ኃላ ላይ ግን ይህን ማዕረግ ሙሉ በሙሉ የሚጠሩበት ልዑላኑ ነበሩ። ለምሳሌ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ የመጀመሪያ ልጅ እና አልጋ ወራሽ የነበሩት ልኡል አስፋወሰን የሚጠሩት መርድ አዝማች አስፋወሰን ተብለው ነበር።
#መስፍን ፦ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የንጉሳውያን ቤተሰብ መጠሪያ ሲሆን፣ ለምሳሌ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሁለተኛው ወንድ ልጃቸው ልኡል መኮንን ‘‘መስፍነ ሀረር መኮንን’’ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጉሙም መኮንን የሀረሩ መስፍን ማለት ነው።
#ልጅ፦ ይህ ማዕረግ የመሳፍንቱ ልጆች ብቻ የሚጠሩበት ነው። ለምሳሌ ከአፄ ምኒሊክ በኃላ ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ የመሩት ልጅ ኢያሱ ንጉሰ ነገስት ተብለው ዘውድ ስላልጫኑ በታሪክ የሚጠቀሱት ‘ልጅ ኢያሱ’ ተብለው ነው፣ ልጅ እንዳልሃቸው መኮነንም ልጅ ይባሉ ነበር።
#ደጃአዝማች፦ (የጦር ሜዳ አዝማች) ማለት ሲሆን በወታደራዊው መስክ የጦር ዘመቻዎች መሪ ሲሆን በሲቪል ማዕረግነቱ ደግሞ ከቢትዎደድ አንድ ደረጃ ዝቅ ያለ ነው።
#ፊታውራሪ ፦ (ቀድሞ የሚዘምት ሰራዊት መሪ) እንደ ወታደራዊ ማዕረግ የጦር ሰራዊቱ ዋና አዛዥ ማለት ሲሆን፣ በሲቪል ደግሞ ከደጅአዝማች ዝቅ ብሎ የሚገኝ ማዕረግ ነው።
#ቀኝ_አዝማች፦ (በጦር ሜዳ በስተቀኝ ያለውን ሰራዊት መሪ፣ ቀኝ መሪ) በወታደራዊ ማእረግነቱ ሲሆን በሲቪል ደግሞ ከፊታውራሪ ዝቅ ብሎ የሚገኝ ነው።
#ግራ_አዝማች ፦ (በጦር ሜዳ የግራ ክንፍ ሰራዊቱ መሪ፣ የግራ አዝማች) ማለት ሲሆን በሲቪሉ ደግሞ ከቀኝ አዝማች ዝቅ ብሎ የሚገኝ ማዕረግ ነው።
#ባላምባራስ ፦ በወታደራዊ መስክ የምሽግ አዛዥ፣ የቀበሌ ወይም የጦር ሰፈሩ ጠባቂ አዛዥ ማዕረግ ሲሆን፣ በሲቪል ደግሞ በቤተመንግስት ባለሟልነት ወይም በእልፍኝ አሽከርነት ታላቅ አገልግሎት ላበረከተ ባለሟል የሚሰጥ ሹመት ነው።
ከላይ የጠቀስናቸው ከሻለቃ በላይ ያሉት የጦር ሰራዊት ማዕረጎች በአሁኑ ጊዜ በወታደራዊ ማዕረግነት አያገለግሉም። ከሻለቃ በላይ ያሉት የቀድሞ የወታደራዊ ማዕረጎች በወቅቱ የመከላከያ ሰራዊታችን አዋጅ መሰረት ከታች ወደ ላይ በቅደም ተከተል ሲቀመጡ እንደሚእንደሚክከተልው ናቸው።
#ሌተናል_ኮለኔል፣ #ኮሎኔል፣ #ብርጋዴር_ጀነራል፣ #ሜጀር_ጀነራል፣ #ሌተናል_ጀነራል፣ #ጄነራል (አሁን #ፊልድ_ማርሻል ተጨምሮበታ) እንዲህ ከሚባሉት የወታደራዊ ማዕረጎች ጋር ደረጃቸው ተመጣጣኝ ሊባሉ የሚችሉ ማዕረጎች ነበሩ።
#ሻለቃ፦ዛሬም ድረስ የዘለቀ የሺህ ወታደር አለቃ ወይም መሪ ማለት ሲሆን በስራ ላይ ባለው በመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 809 ∕2007 አንቀፅ 19 ስር ባሉት የዘመኑ የመከላከያ ሰራዊታችን የማዕረግ ደረጃዎች መሰረት በሻምበል እና በሌተናል ኮሎኔል መሃል የሚገኝ ማዕረግ ነው።
#ሻምበል፦ ይህ ነባር ማዕረግ ደግሞ በመከላከያ ሰራዊት አዋጁ የማዕረግ ደረጃ መሰረት በአንድ ደረጃ ከመቶ አለቃ በላይ ከሻለቃ በታች ያለ ወታደራዊ ማዕረግ ነው።
#መቶ አለቃ፦ ይሄም ነባር ወታደራዊ ማዕረግ ዛሬም ድረስ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን የመቶ መሪ ማለት ነው። ድሮ እኔ ከሃምሳ አለቃ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ያለ ማዕረግ ይመስለኝ ነበር ግን አይደለም። በመከላከያ አዋጁ መሰረት በሃምሳ አለቃና በመቶ አለቃ መሀል ዘጠኝ የማዕረግ መሰላሎች አሉ። በቅደም ተከተል ከታች ወደ ላይ ስናስቀምጣቸው #መጋቢ_ሃምሳ_አለቃ፣ #ሻምበል_ባሻ፣ #መጋቢ_ሻለቃ #ሻለቃ_ባሻ፣ #ጁኒየር_ዋራንት_ኦፊሰር፣ #ሲኒየር_ዋራንት_ኦፊሰር፣ #ማስተር_ዋራንት_ኦፊሰር፣ ቺፍ_ዋራንት_ኦፊሰር እና ከምክትል መቶ አለቃ በኋላ ነው የመቶ አለቅነት የማዕረግ ደረጃ የሚገኘው።
#ሀምሳ_አለቃ፦ ወታደራዊ ማዕረግ ሲሆን የሀምሳ ወታደሮች መሪ ማለት ነው። ማዕረጉ አሁንም ስሙ ሳይቀየር አገልግሎት ላይ የሚገኝ ሲሆን በስራ ላይ ባለው የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ከአስር አለቃ ቀጥሎ የሚገኝ ማዕረግ ነው።
#አስር_አለቃ፦ ወታደራዊ መዕረግ ሲሆን የአስር ወታደሮች አዛዥ ማለት ነው፣ በመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 809 ∕2007 አንቀፅ 19 ስር ባሉት የዘመኑ የመከላከያ ሰራዊታችን የማዕረግ ደረጃዎች መሰረት ከመጨረሻው የበታች ማዕረግ ከምክትል አስር አለቃ ቀጥሎ ያለ ማዕረግ ነው ሌላ ካለ ጨምሩበት።
የአማራ ነገስታት የማዕረግ ሥሞች። በማሙሸት አማረ ተጽፎ ከእውቀት ድረገጽ ላይ የተወሰደ
~ ዐጼ (ንጉሠ ነገሥት)
~ እቴጌ (የንጉሠ ነገሥቱ ባለቤት)
~ ንግሥት ( ንጉሠ ነገስቷ)
~ ራስ
~ ራስ ቢትወደድ
~ ቢትወደድ
~ መርዕድ አዝማች
~ ደጃዝማች
~ ፊታውራሪ
~ ግራዝማች
~ ቀኝ አዝማች
~ ዋግ ሹም (በዋግ አካባቢ ለመኳንንት የሚሰጥ ማዕረግ ነው።)
~ ጃንጥራር (አባሰል አካባቢ ለአፄ ገላውዲወስ ትውልድ የሚሰጥ ማዕረግ ነው)
~ ባለምበራስ
~ ብላታ
~ቤጅሮንድ
~ ሊጋባ
~ ቀኝ ጌታ
~ ግራ ጌታ
~ ሙሉጌታ
~ ሊቀ መኳስ ( ለአዝማሪዎች)
~ልጅ
~ ባሕረ ነጋሽ (ኤርትራን ( ባህረነጋሽ) አካባቢ ለሚያስትርዳድሩ መኳንንት ከአፄ አምድ ፅዮን ዘመን ጀምሮ የሚሰጥ ማዕረግ ነበር)
~ ባልደራስ
~እልፍኝ አስከልካይ
~ አቃቢ ስዓት
~ ጽሐፊ ትዛዝ
~አጋፋሪ…..
ወደ ማንነትህ ተመልሰህ ትልቅ ስትሆን