፬ ሸርጣን ዉኃ (ቀበሮና ዋላ)
ይህ ኮከብ በሰኔ 21 ቀን ከ3 ኮከቦች ጋር በምሥራቅ በኩል በዶሮ ጩኸት የሚወጣ ነው፡፡ ሸርጣን ነገረ ሰይጣን ይባላል በጃረትና በአጋዘን ይመሰላል ሸርጣን ውሃ ማለት የምንጭ ውሃ ማለት ነው ፡፡ ይህ ኮከብ ያለው ሰው ባህርዩ ልዝብ ጭምት ና አስተዋይ ነው ፡፡ ከአንገት በላይ ሰውን ይወዳል ለትልልቅ ነገሮች ይታገሳል በትንሽ ነገር ይቆጣል ፍቅሩን አይጨርስም ከዳተኛና ውሸታም እምቢተኛ ነው ፡፡ ፈጥኖ ሰውን ይወዳል ፈጥኖም ይጠላል ትልልቅ ኃዘንና ደስታ በየጊዜው የለዋወጡበታል ምክር ያውቃል ገንዘብ ወዳጅ ነው ራሱን ሲላጭ ይታመማል ሰውን ደላይ ወረተኛ ሸፋጭ ነው ተስፋ አይቆርጥም በስንት ተአምራት ከብዙ መከራ ይወጣል በነገረዝሙት የተነሳ ዕሥራት ግርፋት ያገኘዋል ሥራ ወዳጅ ነው ገነዘብ በማጭበርበረ በስጦታ በዉርስ ይገባለታል እንድሁም ይወጣል አይቆምለትም ከዘመዶቹ ጋር ጠብና ክርከር ያበዛል ነፍናፋና ኩርፍተኛ ነው መሓላ ይደፍራል ንግድና እረሻ ክፍሉ ነው ተንኰሉና መዘዙ ክፉ ነው ከፍ ባለ ወነጀል ተከስሶ አደባባይ ለፍርድ ይቆማል ደረቅና እልከኛ ነው የሰው ምክር አይሰማም ለሰውም ደግ አይመክርም ቅንዝረኛ ነው ተንኮለኛ ነው ፡፡
ያመሰገነው ሰው ብቻ ያሞኘዋል የተናገረውን ሁሉ አዎን በሉኝ ባይ ነው ቅኔ ጽሕፈት ተኩስ በገና ግጥም ዕድሉ ነው ጥቂት ጊዜ እስራት ያገኘዋል በሸንጎና ጉባዔ ሕዝብን ለማስረዳት በቂ ንግግር አይሆንለትም ፡፡ ድምጹ ጉሉህ ነው በዓይኑና ደረቱ በክንዱና እምብርቱ ላይ ምልክት አለው ቂም የለውም ይቅር ባይ ነው የሰውን ብልሓት ለማስቀረት ንቁ ነው ኑሮውን ሁሉ ሚስቱ ታዝበታለች በሚስቱ ምክንያት ከዘመዶቹ ጋር ተጣልቶ ይለያያል መጠጥ ያበዛል ስካር ያስሸንፈዋል ፡፡ ገንዘቡን ሁሉ ልጁ ያባክነዋል ልጅ ይሞትበታል ፡፡ ለዚህ ኮከብ ፀረቹ ገውዝ ሰንቡላ ቀውስ ሑት የክፍል ኮከቦቹ ጀዲ ሚዛን ሓመል ናቸው፡፡
ከዘመን ዮሐንስ ከወር ኅዳርና ታኅሣሥ ከቀንም ማክሰኞ ዓርብ እሁድ ያስፈራዋል ከ60 ዓመቱ በኋላ ድኻና ሴሰኛ ይሆናል ባሪያ ዛር ያመዋል በልቡ ሳል ያድርበታል መነኩሴ ይሆናል ሥራይ ያስፈራዋል እሁድ ቀን ይጠንቀቅ ራቅ ካለ አገር አይሂድ ቀይ ሴት አያግባ የሰጠችውንም አይቅመስ በግራሰ አግሩ ምልክት አለበት በማርቆስና በዮሀንስ ይታመማል ሠናይ ወርኁ ሰኔ እኩይ ወርኁ ተኅሣሥ ነው ፡፡ በታመመ ጊዜ መድኃኒቱ የርግብና የፌቆ ሥጋ ከሰሊጥ ጋር አሠርቶ ይብላ መረቁንም ይጠጣ ጠጉራቸውንም አሳርሮ ይታጠን በ40 ዓመቱ ጋኔን አይቶታል እና ደም ያገኘዋል ራሱን ወገቡን ያመዋል በፌቆ ብራና መስጥመ አጋንንትን አስጽፎ ይያዝ ፡፡ በግራ ጎኑ ደዌ ያድርበታል የዛር ውላጅ በአፍንጫው ደም ያነስረዋሰል በሕልሙ ያስደነ ግጥዋል በ10 ዓመቱ ጉሮሮውን የመዋል መብረቅ ያስፈራዋል ማእሰረ አጋንንትና አስማተ ሰሎሞን አስጽፎ ይያዝ ወንጌለ ዮሐንስንም አስነብቦ ይጠመቅ ፡፡ የጥቁር ወሰራ ዶሮ ቡሀ በግ ይረድ ፡፡ ሰናይ ዕለቱ ሰኞ ሐሙስ ቅዳሜ እኩይ ዕለቱ ዓርብ ሮብ እሑድ ፡፡ ሠናይ ወርኁ መስከረም ጥቅምት ጥር የካቲት እኩይ ወርኁ ኅዳር ሚያዚያ ሐምሌ ነው የሱፍና የኑግ ቅባ ኑግ ከሰሊጥ ገር ይጠጣ ፡፡ በምዕራብና ምሥራቅ ጠበል የጠመቅ ፡፡
በየካቲትና ታኅሣሥ ለሞት የሆነ ብርቱ ጦርነት የስፈራዋ ፡፡ ቅዳሜ ቀን ደም አያውጣ መድኃኒትም አይጠጣ የዘመዶቹን ገነዘብ ይወርሳል የሴት ዓይን የስፈራዋል ሆዱን ዓይኑን ያመዋል በጥር በየካቲት ቁስል ያገኘዋል በምንጭ በገደል የምተቀመጥ ሴት ጋኔን ትመታዋለች እረሷ ከዘማዊነቱ የተነሳ እንደቅናት አድርጋ እራሱን ሆዱን ልቡን እየቀሰቀሰች በቀኝ እግሩ እንደ ቁርጥማት ትገባበታለች ብልቱን እነደ ሽንት ማጥ አድርጋ አሳብጣ ታመዋለች በሕልሙ በድቀተ ሥጋ ትገናኘዋለች ለዚህ ሰው መድኃኒቱ የጥቁር ገብስማ ዶሮ በራሱ አዙሮ ያኑር ጉመሮ ጊዜዋ ጠበለል ሥራቸውን ወቅጦ የዶሮዋን ክንፍ ጨምሮ ይታጠን ከነዚህም ሥሮች በሌት ወሃ ዘፍዝፎ 3 ቀን ይታጠብ አስማተ ሰሎሞንንና አቁያጻትን አስጽፎ ይያዝ በ69 ወይንም በ፸ ዓመቱ በዘመነ ዮሐንስ ሮብ ወይም እሑድ ቀን በተፊኣ ደም ይሞታል ፡፡
ሸርጣን ውሃ ኮከብ ያላት ሴት የሆነች እንደሆነ
ዓይነ መልካም ጥርሰ መልካም ናት ቤተሰብ አይስማማትም ነገር ታበዛለች ባለዋን ፈትታ በሰው አገር ተኮበልላለች መድኃኒት ና ደም ያስፈራታል ራሷን ዓይኗን እጅዋን ሆዷን ያማታል ሐር ማተብና ብር ቀለበት ከአነገቷ ባይለያት መልካም ነው የጋላ ዛር ሌሊት ያስተዳድራታል ሰንበትን አቦን ሥላሴን ተጠንቅቃ ታክብር ጠቋር በዶስ የሚባሉ ዛሮች ይመለከቷታል መድኃኒቷ የጥቁር ገበሎ ራስአንድ በቀል ፍዬለ ፈጅ ጥቁር ኢዩባን መርበብተ ሰሎሞንን በጥቁር ፍየል ብራና ብራና አንድነት ጽፈህ አስይዛት ጋኔን ይጸናወታታልና በሜዳ ከወንድ ጋር እንዳትገናኝ ትጠንቀቅ ፡፡