በአዝጋሚ ሂደት መለወጥ ወይስ መፈጠር
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነት መሰረት አዳም የነበረው ከዛሬ 7208 አመታት (ዓመተ ዓለም) አካባቢ ነው። ይህም 550 ዓመተ ፍዳ ሲደመር 2008 ዓአመተ ምህረት ሲሆን ድምራቸውም 7208ነው። እንደ እኛ ኢትዮጵያዉያን ይህ ዘመን ነው አዳም ከተፈጠረ እስካሁን ያለዉን የጊዜ እርዝመት የሚያመለክተን። ይህም ያለንበት ዘመን 8ኛው ሺህ በመባል ሲታወቅ የክርስቶስ መምጫው መቅረቡንና በሰው ልጅም ላይ ስቃይና መከራ መብዛቱን እንደምልክት አድርገው ያስተምራሉ።
የዘመናችን እምነት የለሾች (atheistst) ግን የዓዳምና የሂዋንን በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰዉን ካለመቀበላቸዉም በላይ የሰው ልጅ በረጅም ጊዜ ዐዝጋሚ ሂደት (Evolutiuon) ከአንድ በአይን ከማይታይ ነብሳት ወደ ዝንጀሮነት ከዚያም ወደሰዉነት በመለወጥ የመጣ ነው ብለው ያስተምራሉ (በነገራችን ላይ እኔ ይህንን አላምንም)።
ይህም ማለት ዛሬ አለምን ኣስጨንቆ የያዘው ሰው ከዝንጀሮ ቀስ እያለ ተለዉጦ ሰዉ የሆነበትን የጊዜ እርዝመት የሚለኩት ከሚያገኙአቸው የአርኪኦሎጂ ቅሪቶች ነው። ስለዚህ በነዚህ በመፈጠር (Creation) ሳይሆን በረጅም አዝጋሚ ለዉጥ አማኞች (atheists) የመጀመሪያው ሰው ቅርጹን የያዘው በሚሊዮን ወይም በቢሊዮን ከሚቆጠሩ አመታት በፊት ነው።
ለምሳሌ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተገኘውና ረጅም ግዜ እድሜ ያለው የብርቅነሽ (ሉሲ) አጽም 3.2 ሚሊዮን እድሜ እንዳለው ተገልጾአል። ስለዚህ እንደ አዝጋሚ ለዉጥ አማኞች (atheists) ሰው ወይም ሰው መሰል ዝንጀሮ ከተፈጠረ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አመታት አልፈዋል ማለት ነው። እዚህ ላይ መሬት የተፈጠረችበትና አዳም የተፈጠረበት ግዜያት የተለያዩ መሆናቸዉን መገንዝብ ያሻል።