፯ ሚዛን ነፋስ (ተኩላ)
፯ ሚዛን ነፋስ ተኩላ
Edit
ይህ ኮከብ በጥቅምት 7 ቀን በመንፈቀ ሌሊት በዐዜብ በኩል ይወጣል ፡፡ በተኩላ ይመሰላል ሚዛን ነፋስ ማለት እህል ና ገለባን የሚለይ የቀትር ነፋስ ማለት ነው አጉረማራሚ እንደ ነብር ነጭናጫና ነጣቂ ነው ይህ ኮከብ ያለው ሰው ሰውነቱ ቁጡ መላሰኛ ጠላቱ ብዙ ሃይማኖቱ ብርቱ ነው ፡፡ ኑሮው በኃዘን ነው መላና ምክር ዐዋቂ ነገር ተርጓሚ የሰው ልብ ገማች ጥምህርት መርማሪ ምሥጢር አዋቂ ነው ሙግት ዕድሉ ነው ጠላቶቹ ይፈራሉ ይደነቃሉ ይሸበራሉ ግርማሞገስ አለው በድንገት መልስ ለመስጠት ዕድለኛ ነው በሰው ሓሳብ ይመራል በግምባሩ ምልክት አለው ኮከቡ ዘዋሪ ነው አያርፍም ዘመዱን ይጠላል ባዕድ ይወዳል አእምሮዉ ብሩህ ነው መጨው ነገር ይገለጽለታል ቤተ-መንግሥት ክፍሉ ነው ሹመትና ንግድ ክፍሉ ነው ንዳድና የኮሶ ምች ያስፈራዋል ልቡ ብሩህ ጭምት ነው የተማረውን አይረሳም ፡፡
ለሰው ቅን በቃሉ ደስ የሚያሰኝ ይመስላል ለመብል እሱር ንፉግ ነው ብዙ ገንዘብ ያገኛል አይሰጥም ለልጁም ቢሆን ከቶ አይሰጥም ገንዘቡ ለባዕድ ይሆናል በእጁ በረከት የለውም አምልኮኛና መሓላ ፈሪ ነው ድሃ አይወድም ከትልቅ ሰው ጋር ሳቅ ጨዋታ ያበዛል ተቀያሚ ኩርፍተኛ በፍርድ አድላዊ ሰው አቃላይ ነው የተመሰገነ ታሪክ ይኖረዋል አገር ላገር በመዞር ሀብት ይሆንለታል ገንዘቡ በዕድሜው እኩሌታ ያለቃል ፡፡ የድውይ መፈውስ ስጦታ በእጁ አለው ፡፡ አይታወቅበትም እንጅ ምቀኛና ሐሜተኛ ነው በመብል ጊዜ ጉምጁና ሆዳም ነው የጆሮ ቁስል ያስፈራዋል በዓይኑ ዘማዊ ነው አውስቦ ይወዳል ቀይ ሴት አግብቶ 7 ልጆች ይወልዳል ፡፡ ትልልቅ የሆነ ነገር የስባል ከፍጻሜ ግን አይደርስለትም ፡፡ ለዛ ያለው ንግግርና ደስ የሚያሰኝ ጨዋታ ያውቃል ስሙን ለማጥፋት ብዙ ጠላት ይነሳበታል ነገር ግን በተንኮላቸው ዝናውን እና ዕውቀቱን ስሙንና ታሪኩን እጅግ ከፍ ያለ ያደርጉታል ፡፡ በድንገተኛ ነገር ድንጉጥና ፈሪ ነው እስራት ያገነዋል ቤቱ ይወረሳል ይበዘበዛል በዓርብ ቀን ትልቅ አደጋ ያገኘዋል ስለሰው መሰዋዕት ሆኖ ሊያልፍ ይወዳል ንግድ ከብት ርቢ እርሻ ክፍሉ ነው ፡፡ ከ፶ ዓመት በኋላ ባለ ጸጋነቱ ይመለስለታል ፍጻሜው በትዳሩ እንዳማረለት ያልፋል ፡፡ በግራ እግሩና እጁ ምልክት አለበት ቁስል ይገንበታል የግራ አካላቱን ያመዋል በዓይኑና በልቡ ዛር አይቶታል እና ዓይኑ ይፈዛል ፡፡ ከጥቁር ሴት ቂጥኝ ያስፈራዋል በጥቁር ሰው የተተነሣ አምባጓሮ ያስፈራዋል በዚህ ምክንያት ከደንቃራ ይገባና ይታመማል ድርጎ የሚባል ዛር ከሰው ተጋብቶበታል ጽኑ በሽታውም የራስ ምታት ነው የሚብሰውም እሁድ ቀን ነው በዘመነ ሉቃስ የደብረታቦር ዕለት ያስፈራዋል ፡፡ በ፴ ዘመኑ በጦርነት ይቆስላል ራሱን ቀይ ሰው ቢያግመው ይሻለዋል ፡፡
ለዚህ መድኃኒቱ የሰው ሰለባ አዝሙድ የጥቁር ውሻ ኩስ 7 ቀን ቢታጠን ይድናል በ፵ ዓመቱ በቀኝ እግሩ እንደ ቁርጥማት ለዚህ መድኃኒቱ በነጭ ፍየል ብራና ኤኮስንና አካስን ጌርጌሴኖንንና አልቦ ስምን አስጽፎ የሸላ ሥጋ ጨምሮ ይያዝ በሀጥቁር ገበስማ ወይም በነጭ ዶሮ ጭዳ ብሎ ሥጋውን በሰሊጥ አሰርቶ ይብላ በኀዘን ምክንያት ያገኘዋል ሠባ ሥጋ ሲበላ የሰው ዓይንና የዛር ውላጅ ያየዋል ወገቡን ሆዱን ጎኑን መላ አካላቱን እየከፈለ ያመዋል ይህ ሕመም ያስፈራዋል ይጠንቀቅ እኩይ ወርኁ መጋቢ ሰኔ ነሐሴ ሰናይ ወርኁ ጥቀቅምትና ሐምሌ ነው ፡፡ ዕኩይ ዕለቱ ሮብ ዓርብ እሁድ ሠናይ እለቱ ሰኞ ማክሰኞ ሐሙስ ነው ፡፡ ጋብቻው ሐመል ጀዲ ናቸው ሸርጣንም ኅብሩ ነው ኮከበ ፀሩ ሑት ሰውር ሰንቡላ አይሆኑትም ቀይና ነጭ ነገር ክፈፍሉ ነው መርበብተ ሰሎሞንንና ኤኮስ አስጽፎ ይያዝ ፡፡ አጋጣሚው አሰድ ጀዲ ሑት ነው ከዕከላዊ ክፍሉ ደለዊ አሰድ ናቸው ፡፡
በዘመነ ሉቃስ ወይም በዘመነ ማቴዎስ ነሐሴ እሁድ ቀን የደብረ ታቦር እለት በ65 ወይም በ፸ ዓመቱ ይሞታል ፡፡
ሚዛን ነፋስ ኮከብ ያላት ሴት የሆነች እንደሆነ ፡፡
በዘመኗ ኁሉ ታማሚ በሽተኛ እራስ ምታትና የሆድ ሕመም አይለያትም እንደ ሥራይ ሰርቶባታል ሆዷን እየበላ ያመነምናታል ዘመደዎቿ መድኃኒት ያቀምስዋታል ፡፡ ምቀኛ ይበዛባተል በፊት ገንዘብ ጣገኛለች ትከብራለች ደግ ልጅ ትወልዳለች የኋላ ኋላ ግን ችግር ያገኛታል የመርገም ደም ይመታታል ብዙ ዛር ያድርባታል በሽታዋ ወደ ጣዖት ያሰግዳታል በመጨረሻ ዘመን ግን ንስሓ ገብታ ወደፈጣሪዋ ትመለሳለች ለንብረትዋ ልባም ናት የራስዋ ፀጕር ረጅም ለስላሳ ነው የምትወልደው ወደኋላ ቆይታ ነው ከጥቁር ሰው ጋር መገናኘት አይሆናትም ክፍሏ ቀይና ነጭ ነው ፡፡