አማራና ኢትዮጵያ

የአማራዉን የወደፊት አላማና የትግል ስልት የሚያመለከት አቁዋም፣ ፍላጎትና አቅጣጫ

የአገር ዉስጥ ከሃዲዎችና ጥቂት የዉጭ ጸረ-አማራ ባእዳን አዲሱ የረቀቀ ተንኮል አማራ የራሱን ሃገር (ኢትዮጵያን) ጠላት አድርጎ እንዲያይና ትግሉም እነሱ ሊያፈረሱዋት ካልቻሉት ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሆንላቸዉ ነው። ይህንን አዲስ ስልትና ብልሃት የተከተሉበት ዋናዉ ምክንያት እነሱ በተናጠልም ሆነ ተባብረዉ ኢትዮጵያንም ሆነ አማራን ማጠፋት እንደማይችሉ ከተረዱ በሁዋላ ነዉ። አማራን ካጠፉ ኢትዮጵያን ከፋፍለዉም ሆነ ወይም ስሙዋን ቀይረዉ ፍላጎታቸዉን ያሳካሉ። አንደሚታወቅዉ መጀመሪያ የአማርኛ ፊደሎችን የቀረጸዉ የአማሮች አባት ኢትዮጵ (ኢትኤል) ኢትዮጵያን ከመሰረተ በሁዋላ በተለያየ ዘመን ብዙ ነገዶች መጥተዋል። ከነዚሕ ዉስጥ የቅርቦቹ ማለትም የ16ኛ ክፍለ ዘመን ወራሪዎች አማራ የመሰረታትን ሃገረ ኢትዮጵያን ለማፍረስና ለማጥፋት ወይም አማራዉ ሃገር አልባ ሆኖ እንደ ኩርድ ህዝብ ተበትኖ እንዲጠፋላቸዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም ላይ ናቸዉ። እዚህ ላይ በደንብ ማስተዋል ያለብን ኢትዮጵያን ማጥፋትና አማራን ማጥፋት ሁለቱም አንድ መሆናቸዉን ነዉ።

አማራዉ ዘረኞች ጊዜ እየጠበቁ በተደጋጋሚ ግፍ ስለፈጸሙበት በህይወት ለመኖር፣ ለደህንነቱ፣ ለጥቅሙ፣ ለመብቱና ቀጣዩን ትዉልድ ለማዳን ያለዉ አማራጭ በእዉቅት ተደራጅቶ ማሸነፍ ብቻ ነወ። የአማራዉ ቀጣይ ተግባር በመሰረታት አገሩ ዉስጥ እየኖሩ ዘሩን ያጠፉትንና ያፈናቀሉትን ጸረ-አማራ ዘረኛ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብና ፍትህ እንዲሰፍን ለማድርግም ጭምር ነዉ። ለምሳሌ ከ16ኛዉ ክፍለ ዘመን በፊት ወለጋ ቢዛሞ እና ዳሞት፣ ኢሊባቡር እናርያ፣ ጅማ ገሙ፣ ሰላሌ ግራርያ፣ አርሲ ፈጠጋር፣ ሃረርጌ ደዋሮ፣ ወሎ ላኮመልዛ ወይም ቤተአማራ፣ ራያ አንጎት፣ ባሌ ባሊ ይባሉ ስለነበር በትክክለኛ የጥንት ስማቸዉ እንዲጠሩና ወደነበሩበት የአማራ አጽመርስትነታቸዉ ለመመለስ ብቻ ሳሆን ታሪክን ለማጥፋት ሲባል አሁን ባለንበት ዘመን በህገ ወጥ መንገድ ደብረዘይትን ቢሸፍቱ፣ ናዝሬትን አዳማ፣ አሰበ ተፈሪን ጭሮ፣ ደቡበ ምእራብ ኢትዮጵያን ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባን ፊንፊኔ  እያሉ አዲሰ ስም ማዉጣታቸዉን ለማስቆምና ወደፊት አማራዉ በሃገሩ በኢትዮጵያ ዉስጥ ንጹሃን ወገኖቹ በማንኛዉም የዉስጥም ሆነ የዉጭ ሃይል ግፍ እንዳይፈጸምባቸዉ ለማድረግ ነዉ።

አማራነትን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት ለይቶ መገንዘብ ያስፈልጋል። አማራነት “ነገዱ” ሲሆን ኢትዮጵያ ደሞ “ሃገሩ ነች”። ይህንን ጠንቅቀዉ ባለመገንዘብ ጥቂት አማሮች ተንኮሉ ሳይግባቸዉ አማራዉን የሚያጠፋ ፕሮፓጋንዳ ከተኩላዉ ጸረ-አማራ ሙዋርተኛ ጋር ተቀላቅለዉ እንዳያስተጋቡ መጠንቀቅ አለባቸዉ። ኢትዮጵያን ከአማራዉ የመነጠል ተንኮል እጅግ አደገኛና አማራው ታሪኩን ማንነቱን የአባቶቹን ሃገርና ስልጣኔ በሙሉ አዉልቆ ጥሎ እንዲዋረድ ለማድረግ ነው። ከመጽሃፍ ቅዱስ ጀምሮ የኢትዮጵያ ታሪክ በሙሉ የአማራ ታሪከ መሆኑን አለመረዳት የአማራዉን ማንነት ለመግፈፍና ታሪክ አልባ ለማድረግ ነዉ። ለምሳሌ ያህል “ኢትዮጵያ እጆቹዋን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች” እና “ግዮን (አባይ) ወንዝ በኢትዮጵያ ይፈሳል” ሲል ስለ አማራ መነገሩን መገንዘብ ያስፈለጋል። ስለዚህ የአማሮች ጠላት ኢትዮጵያ ሳትሆን ወያኔ፣ ኦነግና የነሱ አዝማች ባእዳን አግሮች ናችዉ።

ይህንን ስንል ሌሎች መገንጠል የሚፈጉ ነገዶች ካሉ ባለ ታሪኩ አማራ የጥንት የኢትዮጵያን ግዛቶች ተቆጣጥሮ ተገንጣዮቹ ከየት ተነስተዉ ወዴት እንደሚሄዱ ከተረዱ አያወዛግብም።ነገር ግን አማራው የሚገባዉን የመምራትና የማስተዳደር ስልጣን ተሳትፎ ሳይኖረዉ በአንድነት ስም እየተገደለ እየተዘረፈ፣ ታሪኩና ማንነቱ እየቆሸሸ በኖረበት ህግ-አልባ የመከራ ስርአት ዉስጥ በምንም አይነት ተመልሶ አይማቅቅም። ከሌሎች ነገዶች ጋር በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር በሰላም አበሮ ለመኖር ከተፈለገ አማራዉ በራሱ ተማምኖ ሌሎች ነገዶችን ሳይጋፋ ተደራጅቶ ኢትዮጵያን በህግ የመምራት የዲሞክራሲ መብቱ መረጋገጥ አለበት። አማራና ኢትዮጵያ ልክ የግእዝና የአማርኛ ፊድሎች ግንድ ቃሎቻችዉ አንድ በመሆናቸዉና ባለቤታቸዉም አማራ በመሆኑ ሊነጣጠሉ ስለማይችሉ። ምናልባት ጥቂት አክራሪ ነገዶች ከኢትዮጵያ ተነጥለው ለመሄድ ቢፈልጉ እንኩዋን አማራው ከሃገሩ ከኢትዮጵያ በህገወጡ ወያኔ በሃይል የተከለለዉን ቁራጭ መሬት ይዞ የትም አይሄድም። ሲጠቃለል ሌሎች ነገዶች አብረዉት ኖሩም አልኖሩ አማራና የታሪኩ ማህደር ኢትዮጵያ ሃገሩ ለዘለአለም አብረዉ ይኖራሉ።

One thought on “አማራና ኢትዮጵያ

  1. በእዉነትና በጨዋነት ሃሳብዎትን ያካፈሉን። እግዚአብሄር ይስጥልን። Please comment with honesty and courtesy. Thank you!

Leave a Reply