ሸንቁጥ አየለ
ኢሳት ሲቋቋም ወያኔ ክ ጭነት እንደተጫነበት እና ወገቡ እንደተገጠበ አህያ በጣም መቅበጥበጥ ብቻ ሳይሆን ኢሳት የሚባል ሚዲያ እንዳይጠር ማንኛዉንም መጨርጨርና ጫና አድርጓል::ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ሲመሰረት የወያኔ ደም ብዛት ከፍ ያለዉ ያለ ምክንያት አይደለም::
አንድ የተቃዋሚ ሚዲያ : ወይም አንድ ነጻ ሚዲያ : ወይም አንድ የሲቪል ማህበራት ሚዲያ ሲቋቋም የወያኔ የመጀመሪያ ጥያቄ ይሄን ሚዲያ እንዴት አድርጌ ላጥዉ የሚል ነዉ::እንደሚታወቀዉ በርካታ ዌብ ሳይቶችን በማን ህዝብ መርጃ ያልደረሰዉ :ያልነቃ እና የደነቆረ አካል ሆኖ እንዲቀጥል አሁንም ወያኔ የተለያዩ ክ ስልቶቹን ቀጥሏል::
አንድ ደር ነጻ ጋዜጠኛ: ወይም አንድ ጸሃ ከህዝቡ መሃከል ብቅ ሲል የወያኔዎች ቀንድ ይቆማል:: ልባቸዉ ይመታል:: ምቀኝነት ያንቀጠቅጣቸዋል:: የቅናት ዛራቸዉ ይነሳል::እንዴት አድርገዉ እንደሚያጠትም ሳያሰልሱ ያስባሉ:: ያቅዳሉ:: አቅደዉም አይተዉም:: ስንቱን ጀግና ደር ጋዜጠኛ እና ጸሃ እስር ቤት ወርዉረው ለጊዜዉ ግፍ እየጸሙ እፎይ ይላሉ::
ወያኔ ብቻ ሳይሆን ማንኛዉም አምባገነን ሀይል ከሽህ ሰራዊት በላይ አንድ ደካማ ሚዲያ ይራል:: ግን ለምን? የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደትን ጠንቅቀዉ የተመራመሩ: ዲሞክራሲ በአንዲት አገር ዉስጥ ጎልብቶ እንዲቀጥል የዲሞክራሲ ትጥቅና ስንቅ ሚዲያ መሆኑን የሚያበስሩ ምሁራን አለ ሚዲያ ዲሞክራሲ ግንባታን ማሰብ ቀልድ ነዉ ይላሉ::እነዚሁ ምሁራን እንደሚሉት የአምባገነንነት ጸር ጠመንጃ ሳይሆን ሚዲያ ነዉ ይላሉ::
የዲሞክራሲና አስተዳደር ማዕከል (CENTER FOR DEMOCRACY AND GOVERNANCE) የሚባለዉ ተቋም የሚዲያ ሚና በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ( “…promoting the transition to and consolidation of democratic regimes throughout the world.” THE ROLE OF MEDIA IN DEMOCRACY:A STRATEGIC APPROACH ) በሚለዉ የስትራቴጅ ጽሁ እንደሚያብራራው ስለ ዲሞክራሲ ግንባታ የሚያስብ ማህበረሰብ/አካል/ቡድን የመጀመሪያ ስራዉ ሚዲያ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ : ሚዲያንም በርትቶ መገንባት መሆኑን አብራርቶ ያቀርባል:: ከዚህ በተጨማሪም ከላይ ከተጠቀሰዉ ሰነድ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ በርካታ የጥናት ጽሁፎች የሚስማሙበት አንድ ጭብጥ ቢኖር ሚዲያ የዲሞክራሲ ሀይላት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ::
አምባ ገነኖች ከማህበረሰቡ የሚደብቁት ግፍ: ዝርያ: ሸፍጥ: ዘረኝነት: ተንኮል: ግዲያ: ዜጎችን ማናቀል: መግት እና ህገወጥ አገዛዞች ወደ ህዝብ ጆሮ ከደረሱ እንደሚያከትምላቸዉ ያዉቃሉ:: የነቃ: በመረጃ የታጠቀ: ስለ መብቱ ያወቀ ማህበረሰብ የአምባ ገነኖች የጉሮሮ አጥንት ብቻ ሳይሆን መቃብራቸዉን በፍጥነት ቆፍሮ መቀመቅ የሚከታቸዉ ጉልበትንም ታጥቆ የተቀመጠ እምቅ ሀይል መሆኑን ያውቁታል::
ስለዚህ የአምባ ገነኖች የመጀመሪያ ስራ ህዝብን ማደንቆር ነዉ:: ህዝብን ለማደንቆር ዋናዉ መንገድ ደግሞ ሚዲያዎች እንዳይኖሩ ማድረግ ነዉ:: የደነቆረ ህዝብ ልክ እንደ ከብት በተለገዉ አቅጣጫ ይነዳል እና አምባ ገነኖች የህዝብ ንቃተ ህሊና እንዳያድግ ማንኛዉንም መስዋዕትነት ያደርጋሉ::ፕሮፖጋንዳቸዉም የነሱን ግፍ የሚያጋልጥ ጸረ አምባ ገነንነት ሚዲያ እንዳይኖር ለማድረግ ነዉ::
ስለዚህ ህዝቤን እወዳለሁ: አገሬን እወዳለሁ: የነገዉ ኢትዮጵያዊ ትዉልዴ የዲሞክራሲ አየር የሚተነፍስ እንዲሆን እልጋለሁ የሚል ማንኛዉም ዜጋ ሚዲያዎችን አበክሮ መርዳት አለበት:: አንዳንድ ሰዉ አንድ ሚዲያ ወይም ሁለት ሚዲያ የሚበቃ ይመስለዋል:: የዲሞክራሲ ትግሉ ዉስብስብነት በደንብ ያልገባዉ ሰዉ ምናልባት በጥቂት ሚዲያዎች እረክቶ በጀርባዉ ለጥ የማለት ዝንባሌ ይታይበት ይሆናል::የዲሞክራሲ ትግል ግን ዉስብስብ እና ዘር ብዙ ነዉ እና በርካታ ሚዲያዎች የግድ ያስልጋሉ::
ስለሆነም ሚዲያ ሲባል አንድ ወይም ሁለት አይደለም:: ብዙ ዌብ ሳይቶች: ብዙ ሬዲዮን ጣቢያዎች: ብዙ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የግድ ያስልጋሉ:: ዲሞክራሲ ግንባታ ሂደቱ: አምባ ገነኖችን የመዋጋት ስልቱ እና ማህበረሰብን የማንቃት ትግሉ እጅግ ዉስብስብ እና አድካሚ ነዉና ዉስብስብ ስትራቴጅና ስልት ያስልጋል:: በብዙ ምክንያት ህዝብ በቀላሉ በአንድና በሁለት ሚዲያ የሚነቃ አይሆንም::
ህዝብ ብዙ የመረጃ እሳት ሊነድበት ይገባል:: በጥቂት ጋዜጠኞች ጥረት ወይም በጥቂት ጸሃያን ጥረት አለዚያም በጥቂት የዲሞክራሲ አቀንቃኝ ሀይላት ህዝብ ለመራራዉ ትግል አይዘጋጅም:: ብዙ ሚዲያዎች: ብዙ ጋዜጠኞች: ብዙ የዲሞክራሲ አቀንቃኞች እና ብዙ የዲሞክራሲ ታጋዮች ያስልጉታል:: ብዙ ተቋማት: እና ብዙ ዉስብስብ ስትራቴጅዎች: ስልቶች: አጻጸሞች እና አካሂያዶች ያስልጋሉ::
ሚዲያ የዲሞክራሲ ሀይላት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ:: አሁን ባሉት ኢሳት: ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN): የተወሰኑ ዌብ ሳይቶች እንዲሁም አንድ እና ሁለት ጋዜጦች ላይ የሞረሽ ሬዲዮ መታከል ለዲሞክራሲያን ሀይላት ትልቅ ጉልበትን ይጨምራል:: የማህበረሰብ እና ተቋማት ጥናት ተመራማሪዎች አበክረዉ እንደሚመክሩት ማንኛዉንም አይነት መሰረታዊ የህብረተሰብ ለዉጥ ለማምጣት ካስልገ እያንዳንዱን እማህበረሰቡ እጅ ላይ ያሉ ተቋማትን በማስተባበር : በእጃቸዉ ላይ ያለዉን እዉቀት ብሎም ሀብት በማቀናጀት ብሎም ለአንድ ግብ እንዲሰሩ ማድረግ የሚቻለዉ የመጀመሪያ ደረጃ አዎንታዊ የተግባቦት እና የትብብር መንስ ሲገነቡ ነዉ::
በመሆኑም ማንኛዉ በዲሞክራሲ ትግል ላይ ያለ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ: ተቋም እና ሀይል የሞረሽን ሚዲያ ምስረታ ጥረት በመደገፍ ነገ ለሰ ትብብር ቅድመ መሰረት መጣል ይጠበቅበታል:: የትግሉ ሂደት ግብ አንድ ነዉ:: ለሁሉም ዜጎቿ የተመቸች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መፍጠር::ማንም ወገን በዘሩ: በሀይማኖቱ: በፖለቲካ አመለካከቱ እና በግለሰብ ፍልስፍናዉ የማይገለልባት ሀገር መገንባት ነዉ::
ይሄ ሂደት ግን እንዲህ ወረቀት ላይ እንደመጻፍ ወይም ተሰብስቦ እንዲሚወራዉ ቀላል ጉዳይ አይደለም:: ነገሩን ከባድ ከሚያደርጉት ሁኔታዎች ዉስጥ ዋናዉና አንዱም የነቃ ማህበረሰብን እና በመረጃ የታጠቀ ህዝብን የመፍጠር ሂደቱ ብዙ ሀብት: እዉቀት እና ጉልበት የሚልግ መሆኑ ነዉ::
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም የዲሞክራሲ ሀይል አንድ ወይም ሁለት ሚዲያዎችን ብቻ ሳይሆን መርዳት ያለበት አቅሙ በቻለዉ መጠን በርካታ ሚዲያዎችን መርዳት ይጠበቅበታል:: ስለ ሆነም አሁን በመቋቋም ሂደት ላይ ያለዉን የሞረሽ ሬዲዮ ጣቢያ ለመርዳት ሁሉም ወገን ቁርጠኛ ተነሳሽነት በማድረግ የዲሞክራሲያን ክንድ እንዲረጥም ማገዝ ይጠበቅበታል::
አንዱ ሲደክም አንዱ እዳር ቆሞ አይሆንም:: አንዱ ሲደክም ሌሎቻችን አይዞህ በርታ ከማለት በተጨማሪም በተጨባጭ የቻልነዉን እርዳታ በማድረግ ነገን ደግሞ ለሰ ትብብር እና የኢትዮጵያን ህዝብ የዲሞክርሲ ጥም ለመቁረጥ የሚያስችል መሰረት መጣል ወሳኝ ነዉ::
ተነሱ : አታመንቱ የሞረሽ ሚዲያ ምስረታ እዉን ይሆን ዘንድ እንርዳ! ሚዲያ የዲሞክራሲ ሀይላት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ !
https://www.facebook.com/S.Ayele.Eth/posts/1024078357641216