ምልጃ !

 

ምልጃ !

ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ

ነሐኤ 12/13

አማልዱኝ! አማልዱኝ!! አማልዱኝ እባካችሁ፡

ለ እናት ኢትዮጵያ ለእምዬ ብላችሁ!1!

ምልጃ ጠያቂው እኔ ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ፦ ደካማ ሰውነቴን ይዤ በስደት በዛሬው ዕለት የ45 ዓመታት ከ8 ወራት፦ ከ22 ቀናት በስደት ያለሁት፦

በሚያዝያ 66 ግርማዊነታቸው፦ ፍጹም ሥልጣንን ለሕዝቡ በምክር ቤቱ አማካይነት እንዲመልሱ፦ አስፈጻሚውም ጠ. ሚ. ልጅ እንዳልካቸው በጊዜያዊነት እንዲታወቅና፡ ምክር ቤቱ ከ 3_4 የሚኾኑ ለአገራችን እድገትና ሰላም ዕቅዶች አሉን የሚሉትን አወዳድሮ ኹለት ሦስትያ ድምጽ ያገኘው የሥራ ጓደኞቹን መርጦ በን.ነገሥቱ እንዲይጸድቅ፦

በሽግግር መንግሥትነት እንዲታወቅ፦ ዋናው ግዳጁም፦ በመሻሻል ላይ የነበረው ሕገ_መንግሥት ያለ ምንም ተጽእኖና ጥድፊያ ሲያልቅና ሲጸድቅ፦

በዚሁ መሠረት ሕዝቡ አስተዳዳሪውን እንዲመርጥ ማመቻቸት ይኾናል፡፡ አለበለዚያ የወገን ማለቂያ፦ የጠላት መሳለቂያ፡፡ እንኾናለን በማለት ለማንቃትና

ለማስጠንቀቅ የሞከርሁ ነበርሁ፡፡ ውጤቱ፦ ያለንበት ነው፡፡

በ83ዓም በመጋቢት አጋማሽ ላይ የሽፍቶቹን ግስጋሴና የኮሎኔል መንግሥቱን ተግባር በማስተዋል፦ በዕውቁ የእንግሊዝ ቴሌ ቪዥን ላይ፦

‘ አሜሪካንና የጸጥታው ጉባኤ፦ አሜሪካኖች ፈርዲናንድ ማርቆስን ከፊሊፕንስ በማውጣት የአገሪቱን ሕዝብ ከመተላለቅ፦ ንብረቷንም ከማወደም እንዳተረፈች፦ ኢትዮጵያንም ለማዳን፦ ሸንጎ የሽግግር መንግሥት እንዲመርጥ መንግሥቱን ማውጣት፡ ንብረትን ከማውደም በላይ ደም እንዳይጎርፍ ይደረጋል፤፡ ባልኩበት ፕሮግራም ላይ የተ.መ. ረዳት ዋና ጸሐፊ አቶ ጄምስ ጆና ነበሩ፡፡

ይህን እንደመተዋወቂያ ውሰዱልኝና፦ በአማላጅነት

_ የእምነት ተቅዋማትን ስብስብ፡

_ በብጹእ ካርዲናሉ የሚመራው የሰላምና የዕርቅ

ጉባኤና፡_

_ የአገር ሽማግሌርዎችን በክብሮት እለምናለሁ፡፡

ክቡራንና፦ ክቡራት እንደምታውቁት፦ የቅኝ ገዥዎች ጥቁሮችን፦ በተለይም አፍሪካውያንን አኹንም ቢኾን ከሰው አይቆጥሩም፡፡ አፍሪካን እንደልባቸው ሲቀራመቱ፦ በድርሻ እንዳይጣሉ ለመመካከር

በ”በርሊኑ ጉባኤነት” በሚታወቅው ተስማሙ፡፡ በዚያን ጊዜም ቢኾን ምንም እንዲያመልጣቸው የማይፈልጉት ብሩሁ፡ “ እምዬ ምኒልክ በሌለሁበት የተወሰነውን አልቀበልም ” ብለው የዓለምን 2/3 ትገዛ ለነበርችው የእንግሊዝ ንግሥት ጻፉ፡፡ አድዋ የጦር ድል ብቻ ሳይኾን ፦ ሰባዊነትን፦ በጦር ሜዳ የተሸነፈውን ጀግና በክብር መያዝን እንጂ ማዋረድ የኢትዮጵያውያን የጀግንነት ትውፊት ስለሚከለክል በክብር መያዛችን በበለጠ የማይዋጥላቸው መርዝ ኾነ። እነሱ፦ መጀመሪያውኑ በጥቁር አይሸነፉም!!! ከተሸነፉም ከጥቁር የጠበቁት አረማዊ ተግባራትን ኹሉ ነበር፡፡ የአባቶቻችን አያያዝ ግን ፖለቲከኞችን ሲያበግናቸው ስለጦርነቱ ያነበበው ኹሉ ለማለት በሚያስችል፡ ግን የእምዬ ኢትዮጵያና ምኒልክን ዝና አናረው፡፡ መንገዶችንና አደባባዮችንም ሰየሙላቸው ልበል ሰየሙልን!!! ታሪኩ ይብቃ፦ የጥቁር ጥላቻና በባርነት ሊገዙት ምድራዊ ሃብቱንም ሊበዘብዙት የሚፈልጉት እንቅፋት አድርገው የሚያዩት እምዬንና ልጆችዋን ሲኾን፦ በምንና በማን ላይ ማተኮር ግባቸውን እንደሚይስገኝላቸው በማቀድ፡ የደረሰብንን ታውቃላችሁ፡፡ ታሪኩ ይብቃ!!!

በአባሪ የላክሁላችሁን ልታነብቡ ብትችሉ ደስ ይለኛል፡፡ ረዘም ያለበት ምክንያት ጠ. ሚኒስትሩ እንዲገባው በመመኘት ነብር፡፡ ለማንኛውም እዚያ

ላይ፦ሕገ_መንግሥት ተብዬውን ባጸደቁበት ግብዣ ላይ አራት ትላልቆች ምዕራባውያን አምባሳደሮች

“ በዚህ ሰነድ ኢትዮጵያን እጃችን ውስጥ አስገባናት አይደል?..ያሏት እንግዲህ ከጃቸው መውጣት ላይ ይለችውን አገራችን ለማዳን፡ ልጆችዋ ከያሉበት፦

“ ለኢትዮጵያ እንዘምታለን! መቼም፦ የትም፦

በምንም!!!”

ሲሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊነት ተመስጦ ነው!!

በአማላጅነት የደፈርኋችሁ፡ የእምዬ ነገር ኾኖብኝ!!!

እንድታማልዱኝ የምለምናችሁ ጠቅላይ አዝማቹን ነው፡፡ የምዬ ልጆች ቁርጠኝነታቸውን በግብር ጭምር ሲያሳዩ “ እጅ አስገባን ያሉትም!” ኃያላን፦ተመሳሳይ ቁርጠኛነታቸውን በተለያዩ መልኮች ለብዙሃን በማይታዩበትም ዘዴና ተንኮል እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

አላማቸውን ግብ ለማስመታት የቀደምቱና ዋናው “ ምዕራብ ትግራይ!” የሚሏት መውጫ መግቢያና

“ ነጻነት ማወጂያቸው ነች!!”” ስለሷ ደጋግሜ መጻፌን አባሪው ላይ ታገኙታላችሁ፡፡ ትግራይ መቼም ተስፋፍታ ይዛ የእኔ ናቸው የምትላቸው የሷ እንዳልነበሩ በርካታ ካርታዎች ተልከዋል፡፡ አ አ

ጠፍተው አይደለም፤፡ እንዲያውም አንድ በጠ. ሚሩ አካኋን ግራ የገባውና የተጨነቀ ወዳጄ፦ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲመሠረት አገሮች ከቅኝ ገዢዎች የወረሱትን ዳር ድንበር እንዲይዙ ሲኾን፡ ጠበብቶቹና አርቆ አሳቢዎች መሪዎቻችን የኢትዮጵያችንንም የክፍለ አገሮች የሚያሳየውን ላከለት፡፡ የእናንተ፡ የክቡራን/ክቡራት የኢትዮጵያ ልጆች ግዴታ የሚፈለገው ለዚህ ነው፡፡ ከተሰጠኝ ሰበብ አንዱ፦ በመከላክያ ሚንስትሩ በኩል “ እኛ ወሰን ልናስተካክል አይደለም፡፡ እሱ በሕ. መ. በተቋቋመው የደምበር ኮሚሽን በኩል ነው!” ስለዚህም አማራ ሕ. መንግስቱ ሲረቀቅም፦ ሲጸድቅም አባል አልነበረች! ያልተሳተፈችበት .. “ ማስረጃ ኹሉ ጠቅሼ ምንም የለ፡፡ የሚመለከተው “ የፌደሬሽን ም/ቤትም” ተቋቁሞ… ስለአገር.. ስለወገን.. እባካችሁ ሕገመንግሥት ተብዬውንም እንዳሻው እንደሚያያደርገው የአዲስ አበባንና “ አማርኛ የሥራቋንቋ …” የሚለውን ጠቅሼአለሁ፡፡ ከሌላ አገሮችም፡፡

ይኽን ካላደርግን በምዕራብ በኩል በገፍ ያሠለፉብንን ሲያስገቡ ኤርትራም ልትረዳን ብትመጣ “ ከትግራይ ትውጣ!” ሊባል ነው ከአማራ ትውጣ ቢሉ “ እኔ መቼ አልኩና!”ይቀጥላል፡፡ ባጭሩ “ መገንጠል!!! “ ባይ! ባይ!!”

___ ምዕራብ ጎረቤት፦

_፟_ሽብርተኛነቷ ተነስቶላት፦ገንዘብ በገንዘብ ኾና፦

ረዳቶችንና ደጋፊዎችን አሠልፋ፦ የራሷን ወታደሮች በገፍ እያሠለጠነች፦ የኛም ስደተኞች ተብዮች በዚህ ዓይነት እየሠለጠኑና እየታተቁ ጎረቤቶቻችን ከያዙት በላይ ግድባችን ያለበተን የኔ ነው ስትል፦ በእኛ በኩል ወሰነተኛዋ ክልል ተመሳሳይ ሥልጠና ማኪያሄድዋን ታውቁ ይኾን? እኔ አላውቅም፡፡

እንዲያውም አኹን የሠለጠኑት ጦርነት ላይ እያሉ፦ ኹናቴው ባያስፈራ _ አያሳስብም???

እዚህ ላይ የቀድሞ ሠራዊትንና ፖሊስን ላንሳ፡፡ በየስብሰባዎች ለአገር ለመዝመት ዝግጁነታቸውን በዓመታት በሚቆጠር ጊዜ ወትውተው ሰሚ ቢያጡ ወጥተው ተሠለፉ፡፡ጨነቃቸዋ!!! የእምዬን አስጊ ኹናቴ እያዩ!!! “ አይ ሰንደቅ አላማችን!”

ጭንቀታቸውን እጅግ አጉልቶ የሚያሳይ አንድ ነግር አልተመለክታችሁ ይኾን? ባድመ ሲዘምቱ ያላደረጉትን መስቀል አደባባይ ላይ አደረጉት፡፡ ሰበብ ላለመስጠት፡አይ ቆራጥነት!!

አስማትና መተት የተለጠፈበትን ( በብዛት አምባሻ የሚሉትን) ‘ ባንዲራ’ ያዙ፡፡ ሰበብ ላለመስጠት፡፡

ጠ. አዛዡ ያልፈለጋቸው ችሎታቸውን ተጠራጥሮ ነው ወይስ ኢትዮጵያዊነታቸውን? እንዲያውስ ያስገፋቸው

ቆራጥ ኢትዮጵያዊነታቸው ነው! ቢባል ስህተት ይኾናል?

የጀግኖች በላይ ጀግናው ሜ ጄ. የአየር ወለዱ አዛዥ ከነትግል ወንድሞቹ ጋር ኾኖ እባካችሁ! ! እናሠልጥን! ቦታ ስጡን! አመቻቹልን፡፡ እንዘምታለን!! እያሉ በየተራ ወተወቱ፤ ሰሚ ያገኙ ዘንድ እርዱልና!

እንደሌሎቹ የቀድሞው ሠራዊት በሙሉ!!!

እንዲሁም ለቀድሞው የፖሊስ ሠራዊት፡፡ “ ሰነፍ ገረድ መጅ ትደብቃለች!” ይላሉ _ __ አለቃ… እንዳይባል ምከሩልን አደራ!

በውጪ አገሮች የተሠራጩ የኢትዮጵያ ልጆች በተቻላቸው መንገድ ኹሉ እንደዘመቱ ናቸው፡፡ ግን ምን ያደርጋል?! ጠቅላይ አዛዡ መሣሪያውን እንቅ አድርጎ ይዞባቸዋል፡፡ “ የሰሜኑ ዕዝ ተጠቃ!” ይባልልኛል፡፡ ሃሰት! ውሸት! ማጭበርበሪያ መግለጫ ነው፡፡ የሰሜኑ ዕዝ እንደወትሮው በሰላም እተኛበት ቦታ በከሃዲ ጓድ_ወንድም በነበሩት በፍጹም አረመኔነት ተጨፈጨፈ፦ የጭፍጨፋው ዓይነትና ብዛት በየመልኩ መዘርዘር አለበት፡፡ አለበለዚያ ለአረመኔዎች ተገንና ገመና ከታች ኾኖ የወገንን ጭፍጨፋ ዝርዝር መደበቅ ነው፡፡ ይህም ወንጀልን

ከዳተኛነት ነው፡፡ የኾነውን ኹሉ አፍረጥርጦ ማቅረብ፦ የልጆቻችን ጡቶች መቆረጥና መሰል ወጀሎችን በፎቶ ግራፍ አስደግፎ ማቅረብ የተገዛውን ፖለቲከኛውንም ~ኾነ ጋዜጠኛውን አፍ ያስይዝ ነበር፡፡ ለማን ሲባል ነው የተደበቀው?

ክቡራን/ክቡራት አማላጆች ሆይ እባካችሁ ወንጀሉ ኹሉ ይፍረረጥና የወንጀለኞቹን ደጋፊዎች እናሳፍርበት፡፤ ይህ ካልተደረገ፦ የተጨፈጨፉት ደም ይፋረደናል!!!

እዚህ ላይ ልግታውና፦ እንደምታውቁት አባቶቻችን ሲዘምቱ ታቦት ይዘው ሲሄዱ የቀሩት ቄሶቹም ኾኑ ሃጂዎች በጸሎት/በዱአ አብረዋቸው ነበሩ፡፡እንደምሰማው አኹን እግዚአብሔርን ከአዲስ አበባና ትላልቅ ከተሞች እያስወጡት ነው፡፡ በእምነት መሪዎች በኩል ብዙ እንዳልተደርገ እረዳለሁ፡፡

ኾኖም ግብረ ሰዶምና መሰል ዓለምን ያስቀጡ ኃጢአቶች እየናኙ ከተዋህዶ ሊቀ ኅሩያን ደረጀ፦ ከወንጌላውያን ዶር ሥዩም አንቶኒዮስ እየለፉ ነው፡፡ ከሌሎች ሃይማኖቶች ይኖሩ ይኾናል፡፡

የምለምናችሁእነዚህን ልጆቻችሁን እንድታነጋግሯቸውና ለአገር ወገን ድኅነት የሚገባውን ኹሉ ለማድረግ እንድትተባበሩ ነው፡፡

ስደመድም፦ አንድ ግራ የገባኝንም ጉዳይ ከጠ. ሚሩ

ማብራሪያ ታገኙልን ዘንድ ነው፡፡ እነዚህ የጠላት መሣሪያ ባንዳዎች ሲከሰሱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 28

“…የሰው ዘር የማጥፋት …በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር.. ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታደግም፡፡ በሕግ አውጬው ክፍልም ኾነ….በምሕረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም….”

ይህ አንቀጽ በተከሳሾቹ ላይ ለምን አልተጠቀሰም?!

በመጨረሻው አገራዊ ምርጫ ላይ ወደ 2 ሚሊዮን ተኩል አማሮች የደረሱበት አልታወቀም ነበር፡፤ በሕግ መምሪያው መዝገብ ቤት ይገኛል፡፡

“ አማሮች በመኾናቸው ነው!” እንዳይባል ክስ አንቀጽ ውስጥ እንዲገባ ታስትውሱ ዘንድ በአክብሮት ልለምን፤፡

አንድዬ፦ እምዬንና ልጆችዋን ከመተላለቅ ያድንልን!!