በታሪክ ምስክርነት ፣በዓለም የጠበብቶች ብራና በአኩሪ ገድል የሚታወቀው የአፄ ቴዎድሮስ የእጀን አልሰጥም ዘላለማዊ ክብር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ዋና አዛዥ በቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ በድጋሜ በሸዋ ምድር መርሐቤቴ አውራጃ ተደገመ። ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም የአገዛዙ ነፍሰ በላ ቡድን በሸዋ ክፍለ ሀገር በመርሐቤቴ አውራጃ ከአለም ከተማ በመነሳት በአካባቢው አጠራር ወደ ገረንና በርቃቶ ቀበሌዎች በማምራት አማራ ጠል መሆኑን በግልፅ ለማሳየት ትግሉ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸውን አምስት ግለሰቦች ከግብርና ስራቸው ማለትም በጤፍ ውቂያ ውድማ ላይ ላይ የነበሩ ስማቸው
1መኳንንት ሲያሰኝ
2 ጫብሰው አማረ
3 ደምሰው ሽታው የተባሉትን አርሶ አደሮች ከገረን ቀበሌ ሁለት ክፉኛ የቆሰሉ ስማቸው 1አባቴነው ማርቆስ እና የቻለሰው ንጉስ የተባሉትን ክፉኛ በማቁሰል እንዲሁም ከበርቃቶ ቀበሌ አፍኖ ያመጣውን አርሶአደር ስሙ ብርሀኑ ተሰማ የተባለ ግለሰብ በመግደል በአጠቃላይ 4(አራት) ሲቪሊያንን በመግደል እጃቸውን በገዠራ አይናቸውን በሰንጢ አውጥቶ ሁለት ግለሰቦችን በማቁሰል በርካቶችን በማፈን ፍፁም አረመኔነቱን ተጠቅሞ በግፍ ከገደለ በኋላ አስከሬናቸውን በየቦታው አስቀምጧል። ያኔ ነበር “የአማራ ህዝብ ሆይ ካንተ በፊት ሞቴን፣ከአንተ አጠገብ ብስራቴን ያድርገው” ብሎ ለራሱና ለህዝቡ ቃል የገባው ሞት አይፈሬው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ዋና አዛዥ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ ከሌሎች ሁለት አመራሮችና አጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን በቅርበት ለስራ እንቅስቃሴ እያደረጉ ባሉበት ሁኔታ ያን በህዝባችን ላይ የፈፀመ አረመኔነት ሰሙ ያኔ ነው ተወርውረው ጠላትን ፊት ለፊት የተጋፈጡት።
አዎ ያማል ወገንህ አገር ሰላም ብሎ በተቀመጠበት እጁ ተቆርጦ አይኑ ወጥቶ ስታይ እንኳንስ ክላሽ ይዘህና በድንጋይም ቢሆን መጋፈጥ የጥንት ስሪታችን የአማራ ስነልቦናችንም ነው። የወገኖቹ የግፍ ግድያ ያንገበገበው ግፍና መከራ ያንገሸገሸው ቀኝ አዝማች ይታገስ አዳሙ ለአንድያ ነፍሱ ሳይሳሳ የያዘውን ዘጠና የክላሽ ጥይት ጠት ላይ አርከፍክፎና ሦስት ኤፍ ዋን ቦንብን አረመኔው ላይ አዝንቦ በርካቶችን እስከወዲያኛው ሸኝቶ በርካቶችን ክፉኛ አቁስሎ በስተመጨረሻም እጅህን ለጠላት አትስጥ የሚለውን የመቅደላውን ጀግና የቴዎድሮስን ተግባር ማተቡ ላይ በማሰር በቀረችው አንድ ጥይት ራሱን ሰማዕት አደረገ። ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል፣ላይጠናቀቅ የተጀመረ የአማራ ትግል የለም።ይብላኝ እንጂ እንመረዋለን የሚሉትን ህዝብ ጨፍጫፊ ቡድን እያሰማሩ ወገናቸውን በግፍ የሚያስገድሉ የደም ፊርማ የሚፈርሙ የክልል፣ የዞንና የመርሐቤቴ ወረዳ ካድሬዎች ምድሪቷ እሾህ ፣ሰማዩ ደግሞ እሳት ሲሆንባቸው!
ድል ለአማራ ፋኖ ክብርና ሞገስ ለተሰው ሰማዕታት፡፡
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም