መኪና በማይገባባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ህዝቡ የሚወክለዉን ፓርቲ እንዳይመርጥ ማስፈራራትና ወከባ እየተደረጉ ነው።

በሰሜን ሸዋ ሰፊው የአማራ ህዝብ በሚኖርባቸውና መኪና በማይገባባቸው የገጠር የምርጫ ጣቢያዎች ህዝቡ ይወክለኛል ብሎ የሚያስበውን ፓርቲ እንዳይመርጥ ከፍተኛ ማስፈራራትና ወከባ እንደተድረጉ ከአካባቢው የሚገኙ ታማኝ መረጃዎች አስታዉቀዋል። በዚህ አመት እንኩንዋን ህዝቡ እፎይ ብሎ የሚመስለዉን ድርጅትም ሆነ ሰው ይመርጣል ብለን ብንጉዋጉዋም በአዴን የአማራን ህዝብ እንደገና የሚያዋርድ ስራ ተመልካች በሌለባቸው የገጠር አካባቢዎች መፈጸሙ ታዉቆአል። ሁኔታዉን በጥልቀት ካወቅን በሁዋላ ለህዝቡ እናሳዉቃለን።

CUD-Addis-Ababa-demonstration.jpeg

ሃገራችን ወደ ዲሞክራሲ ትሸጋገራለች ብለን በትእግስት ብንመለከትም አሁንም ልክ ወያኔ እንዳደረገው የኦሮሙማና የኢዜማ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች የአማራዉን ህዝብ ድምጽ በመስረቅ በስልጣን ማማ ላይ ለመቀመጥና ቀሪዉን የተማረ ህዝብ በማግለል ለባርነት እንዳያዘጋጁት መላው የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ህገ ወጥ ድርጊት እንዲቃወም እናሳስባለን። ይህ ድርጊት ኢትዮጵያ ወደ ሰላም መረጋጋትና ወደ እድገት እንዳታመራ የሚያደርግ አስነዋሪ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሃገሪቱዋ ዉስጥ የታመቀ ብሶት ገንፍሎ ወደ ማያስፈልግ አቅጣጫ ሊያመራ ስለሚችል አስፈላጊ ከሆነም ባስቸኩዋይ በድጋሚ ምርጫ ታርሞ የህዝባችን ድምጽ ይከበር።

ሰላም መረጋጋትና እድገት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ!!!