እኛ ኢትዮጵያውያን በማንነታችን አኩሪ የሆነ ታሪክ እያለን በራሳችን ቁዋንቁዋ የተጻፈዉን ታሪካችንን እንኩዋን እንዳናነብ ልባችን ወደ ዉጭ ብቻ እንዲያተኩር በማድረግ ተደነጋረን ቆይተናል። ታሪካችን ተደብቆ በትምህርተ ስርአታችን ዉስጥ ባለመካተቱ ኢትዮጵያ የለችም ለሚሉ ጥራዝ ነጠቅ ታሪክ በራዦች ዉዥንብርም አጋልጦን ይገናኛል። ለምሳሌ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን በአገራቸው ይኮራሉ ግን ስያሜው ከየት እንደመጣ ወይም ትርጓሜውን ባለማወቃቸው አንዴ አቢሲንያ ነህ ሲሏቸው ሲያሻቸው ደግሞ ቆዳችሁ በጸሃይ የጠቆረ ማለት ነው እየተባለ የተሳሳተ ታሪክ ሲነገራቸው ኖረዋል። ትክክለኛው የኢትዮጵያ መጠሪያ ታሪኩ ግን እንደሚከተለው በጥንታውያን መጽሐፍቶቻችን በመጽሐፈ ሱባኤ ሳይቀር ተመዝግቦ ይገኛል:: እነሆ፥ –
የሳሌሙ ንጉስ ጻድቁ መልከ ጽዴቅ አብርሃምን ከባረከው በኋላ አብርሃም አስራት ከፍሎ በሰላም ወደ ኬብሮን ተመለሰ። (ኦ. ዘ. 14:18-20 ) እንዲህም ሆነ የእግዚኣብሔር ካህን መልከ ጸዴቅ ሶስቱን ልጆቹን ይዞ ሃሎ ወደተባለ ቦታ በመሄድ ለእግዚአብሔር የእህል መስዋት አቀረቡ። ልጆቹም እጣ ክፍላቸውን ያውቁ ዘንድ የተቀበሉትን እንቆአርያ (ዛጎል)፥ ህብስት ይዞ የነበረውን ሞሰበ ወርቅ፥ እና ወይን ይዞ የነበረውን ወርቅ ጽዋ እጣ ተጣጥለው ተካፈሉት። እንቆአርያውም ለመጀመሪያ ልጁ ኢትኤል፥ የወርቅ ጽዋው ለሁለተኛው ለሳሙኤል፥ መሶበ ወርቁምለሶስተኛው ለአበመሌክ ደረሳቸውና ሁሉም ድርሻቸውን ወሰዱ።
መልከ ጽዴቅም በመንፈስ ተሞልቶ ትንቢቱን በእነርሱ ላይ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፥ አንተ የግዮን ውሃ የምትጠጣና ግዮን በሚፈስበት ምድር የምትኖር እንቆአርያ የደረሰህ ኃያል ሆይ ለሰላሙ ንጉስ እና ለካህናት አለቃ ለቸሩ ጌታ የደረሰህን እንቆአርያና እጣ ክፍልህ ከሆነው ምድር የምታገኘውን እንቀኦጵና የከበረውን ሉል፤ ከወርቅ ሐመልማል የተሰራውን በፍታ ገጸበረከት ብለህ አቅርብለት። እጥዓንም አምጥተህ መድኃኒትህ ይሆን ዘንድ አጢስለት ስሙንም አንተ ክርስቶስ ነህ ብለህ ጠርተህ ለክብሩ ስትል ቀድስ። ፊቱ ተንበርክከህ ስገድለት አለው። ኢቴልም ክርስቶስ የምትለው የሰላሙ ንጉስ መጥቶ የሚነግስበት ቀንና ጊዜው መቼ እንደሆነ እርሱ ከማን ዘር እንደሚመጣና በየት እንደሚነግስ ወይም የመምጫውን ጊዜ እንዳውቀው ለይተህ ንገረኝ አለው።
መልከ ጼዴቅም እርሱ ራሱን የሚገልጽበት ዘመኑ እስኪደርስ ድረስ እንቆአርያውን በየአመቱ ተመልከተው። ዘመኑ የራሃብና የቸነፈር ዘመን ሲሆን መልኩ ይዝጋል። እንደአንተም ይጠቁራል። የእህልና የበረከት ዘመን ሲሆን ይጠራል፤ ነገር ግን የንጋቱ ኮኮብ ብርሃን ነጸብራቅ በሆነ ጊዜ ጊዜው እንደደረሰ ታውቃለህ። የብርሃኑ ጨረርም አገሩን ያመለክትሀል። እርሱም እንዳንተ እርሱ ባለበት ላይ መጥቶ ሲሰግድለት ታያለህ። ይህ ሁሉ ይፈጸማል፤ ለልጅ ልጅህ እንዲተላለፍና በልባቸው እንዲጽፉት ለአስተዋይ ልጆችህ በአንደበትህ ንገራቸው።
ግዮን ከሚፈስበት ጀምረህ እስከ ምንጩ ባለው ምድር ንገስ፤ ክህነትህንም ጠብቅ አምላክህንም ለዘላለም ቀድስ አለውና ከአርባ ዘጠኝ ካህናት ጋር ሾሞ ወደ ምድያም ምድርሰደደው። ኢቴልም ከሃሎ ተነስቶ ሲን ምድር ደረሰ። ክዚያም በእግዚአብሔር መንፈስ እየተመራ ከሲን ተነስቶ በአራት መቶ ቀኑ አንኤል የተባለውን የግዮን (አባይ) ወንዝን ተከትሎ ከምንጩ ደረሰ። በዚያም ምድር “ኢያስጲድያና ዮጵ” የተባለ ወርቅ ይገኝበታል። እርሱም ኢትኤል መባሉ ቀረና ስሙ ለዘላለሙ ኢትዮጵ ተባለ። ኢት ዮጵ (ያ) የሚለው የሃገራችን ስም የተወሰደው “ኢት” ከኢትኤል የተወሰደ ሲሆን “ዮጵ” ደግሞ ኢያስጲድያና ዮጵ ከሚለው በሃገራችን ብቻ ከሚገኘው የከበረ ድንጋይ (ወርቅ) ስም የተወሰደ መሆኑን ለመገንዘብ አያስቸግርም። በአባይ ምንጭና በረጅሙ ተፋሰስ ላይ እግዚአብሄር ያነገሰው ኢትኤልም ግዮን የሚያስገብራቸውን ወንዞች የፈለቁበትን ምድር ስሙንና ወርቁን በማገናኘት “ኢትዮጵ”(ያ) ብሎ ሰየመው። ትርጉሙም ለእግዚአብሔር የሚሰጥ (የተሰጠ) የወርቅ ስጦታ ማለት ነው። ይህ የመልከጼዴቅ የበኩር ልጅ ነው የመጀመሪያዉን ማንበቢያና መጻፊያ የሆነዉን የዓማርኛ ፊደል የቀረጸውና ኢትዮጵያን ያቀናው። ይህም የኢትኤል አባትና እናቱ ብቻ ሳይሆኑ ኖህን ጨምሮ ያለፈው ትዉልድ አማርኛ ይናገሩ ነበር ለማለት የሚያስደፍር ነው።
ትንሽ ስለ አማራው የሰሎሞን ስረወ መንግስት
ከክርስቶስ ልደት በፊት ጣናና የረር (ሸዋ) አካባቢ የነበሩ አማሮች በጌምድር (ጎንደር) ላይ በከብት እርባታና በእርሻ ከበሩ። ከዚያም ንግድ ጀምረው ስለበለጸጉ ወደ ባህር ለመጠጋት አክሱምን መሰረቱ። አክሱም ላይም በአለም ገናናዉን መንግስት መስርተው ረጅም ዘመን በተድላና በደስታ ኖሩ:: ከአክሱም በአካባቢው የእስልምና መስፋፋትና በዮዲት አመጽ ምክንያት የንጉሳቸዉን ልጅ አንበሳ አዉድምን ይዘው እየተዋጉ መጥተው መረሃቤቴ ላይ ሰፈሩ።
መርሃቤቴ ላይ ከፍተኛ ዉጊያ ተደርጎ ዮዲት ከተደመሰሰች በሁዋላ ተመልሰው አክሱም ላይ 40 አመት ነግሰው ቆዩ:: ይሁንና የሰለሞን ስርወ መንግስት በመዳከሙ የዛጉየ ስርወመንግስት ሲያስተዳድር ቆይቶ በሁዋላ በሽምግልና ዘዉዱ ለሚገባው ለሶሎሞናዊዉ ስርወ መንግስት በሰላም ተላለፈ። ከዚያም ይሄው የሶሎሞን ስረወ መንግስት ሸዋ ላይ ሆኖ ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን ካስተዳደረ በሁዋል የግራኝ መሃመድ ወረራ በአጼ ልብነድንግል ዘመን ተካሄደ።
አጼ ልብነድንግልም የቅድም አያቶቻቸዉን ሃገር ያዉቁ ስለነበር እየተዋጉ በጌምድር ገቡ (ስሙ እራሱ ለምን እንደተቀየረ አላዉቅም):: ከዚያም ግራኝ ከሁዋላ ሆኖ እየተዋጋ ስለተከተላቸው አጼ ልብነድንግል ደብረዳሞ ተራራ ላይ ሆነው ዉጊያው ቀጠለ። ይሁን እንጂ ግራኝ በቱርኮችና (Ottoman empire) እየታገዘ የሚቻል አልነበረም:: ዐጼ ልብነድንግልም በዚያን ጊዜ ክርስቲያን ከነበረችዉ የፖርቱጋል ንጉስ ጋር አንድነት ለመፍጠር ደብዳቤ ጻፉ። የፖርቱጋሉም ንጉስ በሁነታው በጣም አዘነ (በዚያን ጊዜ ኤሮፕ ዉስጥ ኢትዮጵያ “የቅዱሳን ሃገር” ተብላ ነበር የምትታወቀው)።
የፖርቱጋሉ ንጉስ ኢማኑአልም ቤተክርስቲያን ሄዶ ለኢትዮጵያ ከጸለየ በሁዋላ በክርስቶፈር ዳጋማ (ህንድን ያገኘው የቫስኮ ዳጋም ልጅ) የሚመራ ምርጥ ጦሩን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ በባህር ንጉስ (ዛሬ ባእዳን ባወጡላት ስም ኤርትራ የምትባለው) ኢትዮጵያ ግዛት ሲደርሱ የአካባቢው ሃገረገዥ የሚሸኙአቸው አጃቢ ሰጥተው ወደ ጎንደር አመሩ። ይሁን እንጂ ንጉሱ በህመምና በርጅና አርፈው ስለነበር ባለቤታቸው እቴጌ ሰብለወንጌል ጦሩን ተቀብው አስተናገዱ።
በዚያን ጊዜ ልጃቸው አጼ ገላዉዲዎስ ሸዋ ዉስጥ በድብቅ ተቀምጦ ጦር እየመለመለ ነበር። ክርስቶፈር ዳጋማም የኢትዮጵያና የፖርቱጋል ወታደሮች ጦርነቱን እንዲጀምሩ ፈለገ። የግራኝን አቅም የሚያዉቁት እቴጌ ሰብለወንጌል ግን ለክርስቶፈር ዳጋማ ልጃቸው ተጨማሪ ጦር ከደብረብርሃን ይዞ እስከሚመጣ ዉጊያው እንዳይደረግ ሃሳብ አቀረቡ።
ነገር ግን ክርስቶፈር ዳጋማ ጦሩ ያለስራ በመቀመጡና ምግብና ዉሃ አቅርቦቱ እንዳይረዝም ብሎ ዉጊያውን በጀግንነት ሲያካሂድ ከቆየ በሁዋላ በግራኝ እጅ ዉስጥ ገብቶ ግራኝ በጭካኔ አንገቱን በመቅላት ወረወረው። ንግስት ሰብለወንጌል የፈሩት አልቀረም ኢትዮጵያና ፖርቱጋሎች በቱርክ መሳሪያ ተሸነፉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የልብነድንግል ልጅ አጼ ገላዉዲዮስ ከሸዋ (ከደብረ ብርሃን) ተጨማሪ ጦር ይዞ ጎንደር ገባ። የፖርቱጋሉም ጦር የተረፉትን ወታደሮችና መሳሪያዎች አሰባስቦ ከሸዋ ከመጣው ጦር ጋር አቀናጅተው ግራኝን ጎንደር ዉስጥ ወይና ደጋ በሚባል ቦታ ላይ ገጠሙት። ጀግኖቹ ኢትዮጵያዉያንና የፖርቱጋል ጦር የቱርክና የኦቶማንን መሳሪያ ድጋፍ የሚያገኘዉን ግራኝን ብትንትኑን አወጡት።
ከዚያ በሁዋላ ነው እንግዲህ የሰሎሞን ስርወ መንግስት ጎንደር ላይ ተመስርቶ ብዙ ታሪክ ያስመዘገበዉን እምየ ጎንደርን የገነባው። ከዚያም እንደገና ጎንደር ቤተመንግስት ዉስጥ በአሽከርነት ተቀጥሮ ሲሰራ በነበረ አንድ ስኡል በሚባል ትግሬ የተነሳ ኢትዮጵያ ተመሰቃቀለች:: ወደ ጎጥ ወረደች። ያም “ዘመነ መሳፍንት” ይባላል።
ዘመነ መሳፍንትን ያንበረከኩት አጼ ተዎድሮስ በበዝብዝ ካሳ (የትግሬው ዮሃንስ) ክህደት ከተገደሉ በሁዋላ ኢትዮጵያ የነበራት ስርአት እየፈረሰ በጎጃምና በወሎ ወገኖቻችን ላይ ዮሃንስ የሚዘገንን ጭካኔና ብዝበዛ አካሄደ።
ቀጥሎም የትግሬዉ ዮሃንስ ከእንግሊዞች ጋር ሆኖ ሱዳንን ነጻ ለማዉጣት የሚታገሉ ድርቡሾችን በክህደት ስለወጋና ብዙ ህይወት ስላጠፋ ሱዳኖች ተናደው ሊወጉትና ሊበቀሉት መምጣታቸዉን ሰምቶ ወደ መተማ አመራ። ጦርነቱ ተጀምሮ ሰአታት ሳይቆጠሩ የሱዳን ድርቡሽ ዮሃንስን በመግደልና አንገቱን በመቀላት ተጠናቀቀ። የሱዳን ድርቡሾች የዮሃንስን አንገት በመቁረጣቸዉና ጎንደርን ሊያጠቁ ይችላሉ በማለት ምኒልክ ጦራቸውን ከተቱ።
ድርቡሾች የሸዋን (የምኒልክን) ጦር አይበገሬነት ስለሚያዉቁ የዮሃንስን አንገት ይዘው እየጨፈሩ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ። ምኒልክ ሱዳን ወደመጣበት መመልሱን ሲሰሙ ህዝቡን አረጋግተዉና አስተባብረው የሰሎሞን ስረመንግስትን መልሰው መስመሩ ዉስጥ አስገቡት::
ታላቁ ንጉሰ ነገስት ምኒልክ የሰሎሞንን ስረወ መንግስት መቀመጫን ከደብረ ብርሃን ወደ አንኮበር አዛዉረው በመጨረሻ ዛሬ ሁሉንም ሰብስቦ የያዘዉን አዲስ አበባን (ጥንታዊዋን በረራን) እንደገና መናገሻ ከተማ አደረጉዋት:: አጼ ምኒልክ ከአባታቸው ከንጉስ ኃይለመለኮት ስለጥንታዊቱዋ በረራ በልጅነታቸው ሲነገር ይሰሙ ነበር ይባላል። ለዚህ ይመስላል እንደገና ተመልሰው አዲስ አበባን የሃገሪቱዋ ማእከል ለማድረግ የወሰኑትና የተሳካላቸው::
ዓፄ ምኒልክ የሰሎሞን ስወ መንግስትን ከአባታቸው ከአጼ ሃይለመለኮት በመዉረስ ሲነግሡ መቀመጫቸው ከአንኮበር ወደ እንጦጦ (የዛሬው ደጋማ የአዲስ አበባ አካባቢ) በማዛወር አዲስ አበባ ብለው ዉብ ስም በማዉጣት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አደረጉዋት።
ሌላው እጅግ አስደናቂ ነገር ምኒልክ አዲስ አበባን ዋና ከተማ እንድት ሆን የመረጡበት ብዙ ምክኛቶች ቢኖሩም ዋናው ግን አዲስ አበባ ኢትዮጵያ እምብርት (መሃል ላይ) መሆኑዋ ነበር። ይህም ሁሉንም የኢትዮጵያ ልጆች እኩል እንድታይና እንድትጠቅም አድርጎአታ። ምንም እንኳን ጥቂት ዘረኞች ወዳጅና ጠላታቸዉን ባለማወቅ የምኒልክን ክብር ለመንካት ቢደክሙም 90% የሚሆነው ህዝብ ያከብራቸዋል:: ይወዳቸዋል። ወድፊትም ገድላቸዉን መጭው ትዉልድ ሑሉ ይዘክረዋል።
እቴጌ ጣይቱም ዝቅተኛዉ ቦታ ላይ ወደ ሰማይ እየተወረወረ የሚወጣዉን የፍልዉሃ ምንጭ አይተው ስለወደዱት ቤተመንግስት ሰሩ። እቴጌ ጣይቱ የሰሩት ቤተመንግስት የት እንደሆነ ሲጠየቁ “ዉሃው ፊን እያለ የሚወጣበት ነው” በማለታቸው ፍልዉሀና አካባቢው “ፊን ፊኔ” እየተባለ መጠራት ጀመረ። “ፊን” ማለት ዉሃ በቀጭኑ ወይም ቅርጽ ይዞ ሲረጭ የሚገልጽ የአማርኛ ቃል ነው።
አዲስ አበባ ብዙ ችግርም ደስታም አሳልፋለች። ከጠላት ወረራ በሁዋላ አጼ ሃይለስላሴና በወቅቱ የነበሩ ለቀጣዩ ትዉልድ የሚያስቡ የተማሩና ያልተማሩ ሰዎች ደክመው በመገንባት አለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች ዋና ከተማ እንድት ሆን አድርገዋል። የከተማዋ ኑዋሪዎች በጣሊያን ፋሽት ወራሪዎች ከፍተኛ ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል። በአብዮት ስምም በድብቅ ዘረኖችና ጸረ ኢትዮጵያን ተንኮል ብዙ የተማሩና ምርጥ ልጆችዋ ተፈጅተዋል። በመጠኑም ሆነ በአይነቱ የከፋው ግን የትግሬ ነጻ አዉጭ ድርጅት በህገ ወጥ መንገድ ከሌሎች ጸረ ኢትዮጵያዉያን ጋር በማበር ከተማዋን ከተቆጣጠረ በሁዋላ የተፈጸው ዘግናኝ የዘር ማጥፋትና የዝርፊያ ወንጀል ነው
ነገር ግን ይህች በከፍተኛ ድካምና መሰዋእትነት የተገነባች ከተማ ልጆቹዋ የበይ ተመልካች ሆነው የከሃዲ ጸረ ኢትዮጵያዉያን መፈልፈያና መደራጃ ከመሆን አልፋ እንደ ወያኔ አይነት ጸረ ዓማራና ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች ምሽግ ሆና ትገኛለች። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር እንደ እባብ ተስበው የገቡትን እርኩስ መንፈሶች አዲስ አበቤዎች ልክ እንደ አባቶቻቸው ቀጥቅጥው ያሶጡአቸዋል።
አስደናቂዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ይቀጥላል :: ይህንን መስመር ይጠቁሙ
እዉቀት ዓለሙ