ኢትዮጵያዉያን መሪ እያላቸው ስለምን መሪ ፍለጋ እንደሚዳክሩ አይገባኝም
የኦሮሞ ብሄርተኞች አባ ጅፋራቸው የሆኑትን መራራ ጉዲናን ሲቀቡ መላው ኢትዮጵያኖቹ ስለምን በህጋዊ መልኩ ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስበው በሙሉ ድምፅ ፕሬዜዳንት አርገው የመረጡትን የመኢአድ ትንታግ መሪ አቶ የማሙሸት አማረን የመሪነት ድርሻ መቀበል አቃታቸው ? ማሙሸት አማረ እድሜ ዘመኑን ሙሉ ወያኔን ሲታገል የኖረና እናት አገሩን ያልከዳ ስለቆራጥነቱና የአላማ ፅናቱ ብዙ የተባለለት ብሄራዊ ጀግና መሆኑና እስከካሁን ድረሰ በወያኔ ማጎሪያ ቤት ስለ ህዝቡና አገሩ ዋጋ እየከፈለ ያለ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ የህዝብ ተወካይ የሆኑቱ ሁሉ አንተ መሪያችን ነህ ብለው በፕሬዜዳንትነት የመረጡት ሰው ነው፡፡ በተጨባጭም #መኢአድ አሁን ያለውን የነፃነት ትግል ብርቱ ተሳትፎ በማድረግ በተከበሩት የመኢአድ ምክትል ፕሬዜዳንት በአቶ ዘመነ ምህረት እየተመራ መሆኑ አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ በብሄር ፖለቲካ ውስጥ እድሜ ዘመናቸውን ኖረው በራሳቸው ብሄሮች ይሁንታ ተቀብተው ዶ/ር መራራ ጉዲና የዘመናችን አባ ጅፋር ሆነው ሲቀቡ አቶ ማሙሸት አማረን ደግሞ የኢትዮጵያ መሪ አድርጎ በመሾም ህዝባዊ አደረጃጀቱን ስለምን መጠቀም እንዳልተቻለ አይገባኝም፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጥልቀት ሊያውቀው የሚገባው አቶ ማሙሸት አማረ የተከተሉትና ዋጋ እየከፈሉበት ያለው የፖለቲካ ርኢዮት አለም ከመራራ ጉዲና ቢበልጥ እንጅ በጭራሽ አያንስም ስለዚህ የኢትዮጵያ መሪ የነፃነት አቀጣጣዩ የተከበሩ ፕሬዜዳንት አቶ ማሙሸት አማረ መሆኑን አውቆ መሪውን ከማስፈታት እስከ አጠቃላይ የነፃት መዳረሻ ድረስ ብዙ ሳይባክን መሪውን አውቆ የነፃነት ትግሉን ሊያቀጣጥለው ይገባል፡፡
በትግል ውስጥ መሪና ተመሪ የሚባል ልዩ ድርሻ በመውሰድ የበለጠ ዋጋ እንዲከፍል አስገዳጅ ነገሮች ባይኖርም የነፃነት ትግሉን ወደ አንድ መአከል ለማምጣት ሲባል መሪን አውቆ መንቀሳቀስ መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡ በመሆኑም መላው የመኢአድ አመራርና አባላት፣መላው የቀድሞ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፖርቲ አመራርና አባላት የሰመያዊ ፖርቲ አመራርና አባላት የአማራ ብሄርተኛ የህልውናና የማንነት ተፋላሚ የፋኖ አመራሮችና አባላት በኦሮሞ ህዝብ ተቀብተው የአባ ጅፋርን በትረ ዘንግ የተቀበሉቱ ዶ/ር መራራ ጉዲና እና አባሎቻቸው የደቡብ ህዝብ የነፃነት ተፋላሚ አመራርና አባሎቻቸው ሁሉም የነፃነት ተፋላሚ ሁሉ ትግሉን ወደ አንድ መአከል ለማምጣት ሲባል በሰላማዊ ትግል ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍል ለኖረው አሁንም ያለ በደሉና ያለወንጀሉ ፍርደኛ ጋሚዶ ሆኖ ላለው ለአቶ ማሙሸት አማረ የመሪነቱን ድርሻ ሰጥቶ ቀሪ የህዝብ ለህዝብ መዋቅሮቹን ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የፖለቲካ አመራሮችንና ደጋፊዎቻቸውን ድርሻ ድርሻቸውን እንዲወስዱ በማድረግ የወያኔ አንባ ገነን ስርዓት ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ ማስገደድ ይቻላል፡፡
ይሄንን የመሪ አመራረጥ ዝርዝር ሀሳብ በተጨባጭ ጭለማ ቤት ታግተው ያሉ የህሌና እስረኞች እነ አንዱ አለም አራጌ እስክንድር ነጋ (ጋዜጠኛ) እነ በቀለ ገርባ ሁሉ የሚጋሩት የትግል አቅጣጫ እንደሚሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ልብ በሉ ይህ ሀሳብ ምንም አይነት የዘውጌ ፖለቲካ አሰላለፍን የሚያስወግድ ከመሆኑም በላይ የማንነትና የህልውና አደጋ ተጋርጦብናልና እራሳችንን የመከላከል የሞራልም ሆነ የህልውና ግዴታ አለብን ብለው ኦረሞንም ይሁን አማራን ወክለው የተደራጁ የህዝብ ልጆች ሁሉ አገራቸውን ኢትዮጵያን እስካልከዱ ድረስና በተጨባ እንደምናውቀውና እስከ ገባን ድረስ አሁን የተነሳውን ህዝባዊ አቢዮት በማስመልከት ኢትዮጵያን ወክሎ በህዝብ መልካም ፍቃድ ከመላው የኢትዮጵያን ወረዳዎችና ዞኖች በመወከል በፕሬዜዳንትነት ደረጃ መሪያቸውን ከመረጡ በኋላ ፕሬዜዳንት ሆኖ በእስር ቤት ታስሮ ያለ ከተከበሩ አቶ ማሙሸት አማረ ውጭ ማንም የኢትዮጵያ ወኪል ፕሬዜዳንት ስለሌለ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሀቅ ስለሆነ ሁሉም ወገን የሚገነዘበውና አምኖ የሚቀበለው እውነት ነው፡፡