ከእርቁ በፊት ዓማራን መግደል ማሰር ማዋረድና መዝረፉ ይቁም
ወያኔዎች እርቅ የሚለዉን ቃል ከመናገራቸው በፊት ዓማራን መግደል ማሰር ማዋረድና መዝረፋቸዉን አቁመው ዓማራዉም ሆነ ሌሎች ነገዶች እራሳቸውን ያስተዳድሩ። ከዚያ ውጭ የተለመደ ማዘናጊያቸዉን አማራ እንዳትቀበል!! ስንት ጊዜ ትታለላለህ??????
አማራ ወደ እርቅ የሚሄደው የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ብቻ ነው
፩ የወልቃይት መሬቱ ሲመለስ
፪ ከወሎ የተወሰደው መሬት ወደነበረበት ሲመለስ
፫ ባለፉት ፪፭ አመታት ለተገደለውና ለተሰቃየው ህዝብ ፍት ህ ሲገኝ
፬ ወያኔ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ወርዶ ወደነበረበት ቦታሲመለስና ህዝቡ የሚፈልገው አስተዳደር ያለማንም ጣልቃገብነት ሲመስረትና መረጋጋት ሲፈጠር ብቻ ነው።
ይህ ሳይሆን ወደ እርቅ የሚሄዱ ሰዎች ዓማራን የማይወክሉና ያዉ እንደለመዱት ትግሬዉን ወይም አንዳንድ ለወያኔ የተታለሉ ያልተማሩ አማሮችንና ጥቂት አገዎችን ወይም የሌላ አናሳ ብሄረሰብ አባላትን በመሰብሰብ በአማራ ስም እርቅ እንደተደረገ አድረገው እንደሚያወሩ ይጠበቃል።
ይህም የባሰ አለመተማመንንና ሁከትን በከፍተኛ ደረጃ የሚያጋግል አደገኛ መንገድ ነው። “ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም” ብለዋል ብልሆቹ ወገኖቻችን። እርቅንማ ማን ይጠላል? ግን አማራ ተጠንቀቅ ትግሬ ምንም አይነት የመታረቅ ምልክት እስካሁን አላሳየም። ያው የተለመደዉን አይንህን ጨፍን ከዚያ እንደፈለግሁ ልጫወትብህ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሙአሉ እርቅ ማድረግ ቀርቶ ስለ እርቅ ማዉራት አይቻልም።
አማራ ትግራይ ስትወረር ሌሎች ወንድሞቹን በመምራት አድዋ ድረስ በእግሩ ሄዶ ወገኖቼ በማለት ከባእዳን ወራሪ ደሙን በማፍሰስና አጥንቱን በመከስከስ አድኖአቸዋል። ሲርባቸው አብልቶ ሲታረዙ አልብሶአቸዋል። በደሙ ባቀናው ሃገር ዉስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ሾሞና ሸልሞአቸዋል። እነሱ ግን በዉጭ ሃይሎች በመታገዝና የቀዝቃዛዉን ጦርነት ማብቃት በመጠቀም ስልጣን ከያዙ ጀምሮ ለጆሮም ሆነ ለአይን የሚዘገንኑ ግፎችን እስካሁን ድረስ ያለርህራሄ በመፈጸም ላይ ናቸው።
ሜዳዉም ይኸው ፈረሱም ይኸው። ከእንግዲህ እንዳለፈው የኢትዮጵያን ህዝብ ለማታለል መሞከር የታሰሩበትን ገመድ ከማወሳሰብና በራስ ላይ ጠምጥሞ ከማሳጠር ዉጭ ምንም መፍትሄ አያመጣም። ዐማራ ወያኔ ከቤትህ ሳይወጣና እራስህን ሳታስተዳድር ትጥቅህን እንዳትፈታ። በቃ!