የመኢአድ ህጋዊ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ብቻ ነዉ
መኢአድ 483 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አሉት:: ከጥቅምት 28/2007 እስከ ጥቅምት 30/2007 በተካሄደዉ ጠቅላላ ጉባኤ 483 የጠቅላላ ጉባኤ አባላቱ በተሳተፉበት በ477 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አመራሩን መረጠ:: በዚህ ምርጫም አቶ ማሙሸት አማረ የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ሆነዉ ተመረጡ::
ሆኖም ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤዉን ዉጤት ህጋዊ ነዉ ብሎ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነምና ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥር 3/2007 ዓም እንዲጠራ ተወሰነ:: ሁለተኛዉ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲካሄድ ሲጠራ ከ483 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ዉስጥ 425 አባላት ተገኝተዉ መሪያቸዉን የመምረጥ ስልጣን ያላቸዉ እነሱ ብቻ መሆናቸዉን አስረግጠዉ አስረዱ:: በዚህም ዉሳኔአቸዉ መሰረት የድርጅቱ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ መሆኑን በአንድ ድምጽ ወስነዉ ሄዱ::
ዝርዝሩን ለማንበብ መገናኛዉን ይጠቁሙ