የሰሜን ሸዋን ህዝብ ቁጥርና አስተዳድራዊ መዋቅር በሚመለከት
የሰሜን ሸዋ አማራ ህዝብ ኢትዮጵያን ከመሰረቱትና ጠብቀው ካቆዩት ነገዶች መካከል ግምባር ቀደሙ ሲሆን የአዲስ አበባንና ዛሬ ኢትዮጵያው ዉስጥ ያሉትን ሌሎች ከተሞች ሁሉ የመሰረተ ጥንታዊና ገድለ ብዙ ህዝብ ነው። የህዝብ ብዛቱም ሆነ የመሬቱ ስፋት እንዲህ በህገወጥ መንገድ እንደተቆራረጠና በዉሸት እንደሚያሰራጩት ሳይሆን እጅግ ሰፊና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል:: ይህ ታላቅ ህዝብ ለሚወዳት ሃገሩ ማእከልና መሰዋእት በመሆን አማራዉን ከሌሎች ነገዶችና ጎሶች ጋር አስተሳስሮ ለብዙ ዘመን ዘልቆአል። እግዚአብሄር የፈጠረዉን ሰው ማንም ሊያሳንሰው አይችልም። የሸዋ ህዝብ ቁጥር በደርግም ሆነ በሃይለስላሴ ጊዜ ከትግሬ ሃገር የበለጠ ነበር። የወያኔ የህዝብ ቆጠራ የሰሜን ሸዋን ህዝብ በሞቶ ሺህ አሃዝ ጽፎ የሚያስተጋባው ዉሸት ነው።
ትክክል የሚሆን ከሆነ ለሌሎች አካባቢዎ የተሰጠው የህዝብ ቁጥር ሁሉ ዝም ብሎ የተጻፈ ውሽት ነው ማለት ነው። ለምሳሌ ሃረሪና ስልጢ በመሬት ስፋትም ይሁን በህዝብ ብዛት ካየናቸው የሰሜን ሸዋን አንድ ወረዳ ከተማን እንኩዋን አያህሉም ግን እንደ ዞን ተቆጥረው በጀትም ሆነ ሌላ ግልጋሎት በዚያው መጠን ነው የሚሰላላቸው። በእዉነት እንነጋገር ከተባለ ሰሜን ሸዋ ቢያንስ ሁለት ዞን መሆን ነበረበት።
ደቡብ ዉስጥም አንድ የሰሜን ሸዋን ወረዳ ግማሽ የማያህሉ አካባቢዎች ዞን እየተባሉ ሚሊዮን ህዝብ አላቸው ይባላል። በእዉነት ካላቸው ጥሩ ነው ግን ይኸ ነገር እንደገና መጠናትና መረጋገጥ ያለበት ጉዳይ ነው። እኔ ኢትዮጵያን ከሰሜን እስከ ደቡብና ከምስራቅ እስከ ምእራብ በምርምር ላይ ተሰማርቼ ያየሁት ስለሆነ ትንሽ ግንዛቤ ስለአለኝ ነው። ለማንኛዉ ይህን ሁሉ ሸፍጥ ወደፊት ታሪክ ያጋልጠዋል።
ህዝቡ ግን የወያኔ ተላላኪ ካድሬዎችና በየመስሪያቤቱ የተወሸቁ ድብቅ ጸረ አማሮች የሚለጥፉአቸዉን የዉሸት መረጃዎችና የድንበር ምልክቶች ታማኝ የሆነ የሰሜን ሸዋ ተወካይ ወይም ህጋዊ ማእከላዊ መንግስት እስከሚመሰረት ድረስ ማመን የለበትም። ወያኔ ትግሬዎች ተከዜን አቁአርጠው ሲመጡ አማራን በተለይም የሰሜን ሸዋን አማራ ለመግደል ለመዝረፍና ለማዋረድ መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም። ከዚያም አልፎ ሰሜን ሸዋ አዲስ አበባንና ናዝሬትን እንደሚያጠቃልል ከአሁኑ መታወቅ አለበት። ከእንግዲህ ዝም አንልም!!
ይህ ሁሉ ሁዋላቀር አሰራር ለኢትዮጵያ አንድነት ባለዉለታዉን አማራን በተለይ የሰሜን ሸዋን አማራ ለማሳነስና ከማንኛዉም እድገት ነክና የስልጣን እርከን እንቅስቃሴ ለማግለል ነው። ደግነቱ ከአሁን በሁዋላ አይቻልም። እስከዛሬ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲል እያወቀ እንዳላወቀ ተበድሎአል። መንግስት አለ ብሎ ከእርሻ ዉሎ ሲመለስ ተገድሎአል:: የዘር ማጥፋት ሱስ ባለባቸው ከሃዲዎች ከፍተኛ ግፍ ተፈጽሞበታል። ከእንግዲህ ይህ እንዲፈጸምበት አይፈቅድም።
የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈልግ ሁሉ ይህ አግባብ ያልሆነ አሰራር በአስቸኩዋይ እንዲቆም አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት። ኢትዮጵያ ዉስጥ የነገድ ፖለቲካው ካልተገታና ህዝቡ ወንደ አንድነት መንፈሱ እስካልተመለሰ ድረስ የሰሜን ሸዋ አማራ ከሌሎች ወንድም አማሮችና ሌሎች ሰላምና አንድነት ወዳድ ነገዶች ጋር ሆኖ አባቶቹ እንዳደርጉት የራሱንና የኢትዮጵያን ህልዉና ለሚቀጥለው ትዉልድ ጠብቆ ለማስተላለፍ በመጠራራት ላይ ይገኛል። ታሪክ እራሱን ይደግማል። ያልዘሩት አይበቅልም!!