ቅድሚያ ለአማራ ህዝብ ህይወትና ደህንነት
ወይም
ቅድሚያ ለአማራ የመኖር መብትና የህይወት ደህንነት
ቅድሚያ ለአማራ ህዝብ ህይወትና ደህንነት ወይም ቅድሚያ ለአማራ የመኖር መብትና ደህንነት ማለት፣
፩. አማራ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ህይወቱ፣ የመኖር መብቱ፣ ደሀንነቱና ጥቅሙ በአገባቡ እንዲጠበቅ ማደረግ፡፡
፪. ከ1960 እስከ ዛሬ ድረስ አማራን በመግደል የዘር ማጥፋት ሲፈጽም፣ ሲያስር፣ ሲያፈናቅልና ሲያሳድድ የቆየዉን ወንጀለኛ ስርአት ከስሩ ነቅሎ በመጣል አማራዉ የመሪነት ሚና እንዲጫወት በማድረግ ወንጀለኞችን በሙሉ እያደኑ ለፍርድ ማቅረብ፡፡
፫. ወደፊት በአማራዉ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልና በደል እንዳይደገም ህግና ስርአት የሰፈነባት ኢትዮጵያን በጠለቀና በሰፋ መሰረት ላይ መገንባት።
እዉቀት የህዝብ መገናኛ