የወቅቱ የአማራ የዉጭና የአገር ዉስጥ ግንኙነት (ስልትና ብልሃት)
መንደርደሪያ
የኢትዮጵያ የዉጭ ግንኙነት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከእየሩሳሌም ከህንድ ከቻይናና ከፋርስ (ወይም ከዛሬዋ ኢራን) ጋር ሲካሄድ የነበረ ነው። ብዙዎች የማያዉቁትና በጣም አስደናቂው ግን በኢትዮጵያና በፖርቱጋል መካከል የተመሰረተው የመጀመሪያው ግንኙነትና ከዚያም አልፎ በአለማችን የመጀመሪያ የጦር ትብብር ነው። ይህም ገና እንዳሁኑ አሜሪካ ገና ሳትመሰረትና አፍሪካዉያን በባሪያ አሳዳሪ ባእዳን አስተዳደር ዉስጥ ሳይገቡ በ16 ክፍለ ዘመን ነበር።
ይህ የመጀመሪያው በሁለት ክፍለ አለማት መካከል የተደረገው ግንኙነት እስከ የጦር ትብብር የደረሰና የኦቶማንን የግዛትና የሃይማኖት የማስፋፋት አላማን የሰበረ ነው። ይህ እስደናቂ የአፍሪካና የኤሮፓ ሃገሮች ትብብር የተመራው በታዋቂው የፖርቱጋል አሳሽና ህንድን ባገኘው የቫስኮ ደጋማ ልጅ በሆነው በክርስቶፈር ዳጋማ ነበር። ሆኖም ግን ክርስቶፈር ዳጋማ ከግራኝ አህመድ ጋር በጀግንነት ከኢትዮጵያዉያኖች ጋር ሲዋጋ በመሰዋቱና አጼ ልብነድንግልም ቀደም ሲል በህመም በማረፋቸው ልጃቸው አጼ ገላዉዲዎስ ከመንዝ (ሰሜን ሸዋ) ተነስቶ ከተረፈው የፖርቱጋል ጦር ጋር በመሆን ግራኝ አህመድንና ወራሪዎችን የኦቶማን ቱርኮችና አረቦች ጎንደር ወይና ደጋ ላይ ድል አድርገዋቸዋል።
ሌላዉ በኢትዮጵያና በሩስያ መካከል የተመሰረተዉ የድሮ ግንኙነት በ1799 ሲሆን ኢትዮጵያዊው አለክሳንደር ፑሽኪን ሞስኮው ዉስጥ የተወለደው እኤአ በ1798 ነው። በሩሲያና በኢትዮጵያ መካከል ደሞ ዘመናዊ ግንኙነት የተመሰረተ 18ኛው ክፍለዘመን ነው።ይህ የሚያስተምረን ታሪክ እራሱን ስለ ሚደግምና ዲፕሎማቶች ታሪክን ካላወቁ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ጥሩ መወዳጀትን ለመፍጠር እንደሚቸገሩ ነው። ወደፊት በዚህ ሃሳብ እንደምናየው ኢትዮጵያ የብዙ ሃገሮችን ልብና አስተሳሰብን የሚማርኩ ቀደም ሲል የተሰሩ መሰረቶች አሉአት::
ዲፕሎማሲይ በተለያዩ ሃገሮች መካከል በረጅም ጊዜ የሚገነባ ግንኙነት ነው። ኢትዮጵያን ከተለያዩ ሃያላንም ሆነ ገለልተኛ ሃገሮች ጋር ያገናኘ መሰረት በንጉስ ልብነድንግል በአጼ ዘርአያእቆብ በንጉስ ምነሊክና በአጼ ሃይለስላሴ ዘመኖች የተጣለ ቢሆንም ይህንን አርሾ ይዘው ወዳጅነት የሚፈጥሩ የተማሩና ሃገር ወዳ ኢትዮጵያዉያን ቦታቸውን እንዲይዙ ካላደረግን ብዙ ወዳጆቻችንን ማጣት ብቻ ሳይሆ ጠላት ልናደርጋቸው እንችላለን። ለምሳሌ በእንግሊዝ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው ግንኙነት በሜክሲኮና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው ግንኙነት በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል የነበረው ጥብቅ ግንኙነት ሙያ በሌላቸው መልእክተኞችና በጸረ ኢትዮጵያ ተሹአሚዎች እየተበላሸ ሃገራችንን አሁን አለችበት ደረጃ ላይ አድርሶአታል።
ታሪክ እራሱን ይደግማል
ከ1936-1938(አኤአ) ሜክሲኮ ቻይና ኒውዜላንድ ሶቬት ህብረት ስፓኝ እና አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ፋሽት ጣሊያን ያደረገችዉን ወረራ ተቃውመው ነበር። ሆኖም ግን እስከመጨረሻ ከኢትዮጵያ ጋር የቆሙት ሩሲያ ሜክሲኮ ነውዜላንድና ቻይና ነበሩ። ሩሲያ በአድዋዉም ጦርነት ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ቆማ የማይናወጥ ወዳጅነቱዋን አሳይታለች:: ታሪክ እራሱን ይደግማል ማለት ይሄ ነው። አሁን በአይናችን በምናይበትና በጆሮአችን በምንሰማበት በዚህ አስቸጋሪ የአሸባሪው ወያኔ ዘመን ሩሲያ ሜክሲኮና ቻይና እንደገና ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸዉን እና የማይታጠፍ ወዳጅነታቸውን ማሳየታቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ግምት ሊሰጠው የሚገባ የክፉ ቀን ዉለታ ነው።
ዲፕሎማስይ ምንድነው?
ዲፕሎማስይ የሚለው ቃል ከግሪክ የተገኘ ነው። “ዲፕሎ” ማለት የታጠፈ የተደረበ ሲሆን “ማ” ደሞ ወረቀት ወይም ሌላ ነገር ማለት ነው። ዲፕሎማሲይ የመደራርደርና በሀገሮች መካክለ ያለ ግንኙነትን በሰላም ተግባብቶ የመጠበቅ የጥበብ ሙያ ነው።
** The art of dealing with people in a sensitive and tactful way!
የዲፕሎማሲይ ግንኙነት የተለያየ ትርጉም ወይም ፍቺ ቢኖረዉም ሁሉም የሚስማሙበት (** The art of dealing with people in a sensitive and tactful way) ዲፕሎማሲይ በሰዎች መካከል ያሉ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋተዉን ጉዳዮችን በጥበብ መያዝ ነው።የሚለዉን ነው።
የዲፕሎማስይ ጥቅም
የእንደራሴ ጽ/ቤትን (ኢምባሲይ) መክፈትና መልእክተኞችን (ዲፕሎማትን) የመሾም ዋናው አላማ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ለመግባባት ለመወዳጀት ለመደራደር ዉሳኔዎችን ወደ ራስ ጥቅም ለማምጣት አጨቃጫቂ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የሃይል እርምጃ ከመዉሰድ ዉጭ ነገሮች በሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው።
በሃገሮች መካከል ለሚደረጉ ግንኙነቶች ጠቃሚ የዲፕሎማስይ መመሪያዎች (Principles)
ብሄራዊ ጥቅምን ማስቀደም
አሳማኝ መሆን
ነገሮችን ገልጾ ማስረዳት መቻል
ነገሮችን በስፋትና በጥልቀት ማየት
ሌሎች የሚሉትን መረዳት
ነቅቶ ነገሮችን ማስተዋል መቻል
ችግሮችን በራሱ ተማምኖና ጸንቶ የሚቁአቁዋም ነው።
የዲፕሎማስይ አይነቶች ወይም ክፍሎች
Politics of pacification:(የሰላምና የመረጋጋት ፖለቲካ):
Gunboat diplomacy፡ (ባለ ጠብመንጃ ጀልባ ዲፕሎማስይ)
Dollar diplomacy: (የገንዘብ ዲፕሎማሲ)
Public diplomacy (የህዝብ ዲፕሎማሲይ)
People’s diplomacy (የሰዎች ዲፕሎማሲይ)
Intermediary diplomacy: (አስታራቂ ዲፕሎማሲይ):
Economic diplomacy (የምጣኔ ሃብት ዲፕሎማሲይ):
Digital/electronic diplomacy: (የዉስጥ መረብ ዲፕሎማስይ)
ትኩረት ሊሰጣቸዉ የሚገባቸወ ጎረቤ አገሮቸ፡-
ሱዳን
ጉዳዮች: –
- የመዘጋ (አል-ፋሻጋ) ድንበር ውዝግብ፤
- ሱዳን ውስጥ ከአማራ ጥቅም ተቃራኒ የሆኑ ታጣቂዎች መኖር፤
- የኢኮኖሚ እና ማህበረሰብ ትስስር፤
- በሱዳን የሚኖሩ ብዛት ያላቸው የአማራ ተወላጆች፤
- በሱዳነ የትህነግ የደህንነት መረብና ጸረአማራ እንቅስቃሴዎች
ኤርትራ
ጉዳዮች: –
- ወልቃይት ጠገዴን በተመለከተ የአማራን እና የኤርትራ ፍላጎት ማጥናት
- ህወሓትን በሚመለከት የጋራ አቁዋም መያዝ እና የአልጀርሱን የኢትዮ–ኤርትራ የድንበር ስምምነት መጠቀም፤
- ኤርትራን በሚመለከት የኢትዮጵያ አገዛዝ በተለዋዋጭነት የሚከተላቸውን አቋሞች በመከታተል የአማራን ጥቅምና ፈላጎት በማጉላት ማንጸባረቅ፤
- ኤርትራ ከምስራቅ ሱዳን ቤጃ ጎሳዎች ጋር የምታደርገው እንቅስቃሴ መኖሩን በመገንዝብ ከሱዳን ጋር በሚኖረን ግንኙነት ይህንን ከግምት ዉስጥ ማስገባት።
ደቡብ ሱዳን
ጉዳዮች
ኬንያ
ጉዳዮች
ጅቡቲ
ጉዳዮች
የአፍሪካ ህብረት
መካከለኛዉ ምስራቅ (ግብጽ እስራኤል ቱረክና ሳኡዲ አረቢያ)
ጉዳዮች
አዉሮፓ (ኤረፓን ዩኒየን፣ እንግሊዝና ሩሲያ)
ኤሺያ
- ህዝባዊት ሪፐብሊክ ቻይና
- ሕንድ
ደቡብ አሜሪካ (ላቲን አሜሪካ)
ሜክሲኮ
ኩባ
ኢስት ኢንዲስ
/ጃማይካ/
ካሬቢያንስና
አገር ዉስጥ ካሉ የተለያዩ ነገዶች ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች
ትገሬ
አፋር
ደቡበ
ኦሮሞ
ሱማሌ
ማጠቃለያ
የአለም አቀፍ ሁኔታ ባለፉት ፷ አመታት ዉስጥ ከፍተኛ ለዉጥ እመርታ እያሳየ ስለሆነ ዘመኑን የሚመጥን ሁሉን አሳታፊና ሁሉን አቀፍ የሆነ የዲፕሎማሲይ እና የአለም አቀፍ ስርአት የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን። ሃያላን ሃገሮች ሌሎች በአለም ያሉ ሃገሮችን በሙሉ አሳትፈው በአለም አቅፍ ግንኙነት ላይ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ህግና ስርአት ላይ ክለሳ አድርገው እንደአግባቡ ካላስተካከሉ ወደፊት ችግር ሊፈጠር እንድሚችል ለመገመት አይስቸግርም።
የዘመኑ ፈጣን የዉስጥ መረብ የመርጃ መለዋውጭያ መንገድ የዲፕሎማሲን አሰራር በጥልቀት ሊቀይረው እንድሚችል ለመረዳት የመረጃ መሰብሰቡን ስራ ሰውሰራሽ እዉቀት (Artificial Intelligence) እንዴት እየተካው እንደሄደ ማየቱ በቂ ነው። ይህም ማለት በአሁኑ ሰአት ብዙ ሺህ ዶላር እየተከፈላቸው በመላው ሃገር ከተላኩ ዋጋቢስ የጎሳ አቀቃኝ መልእክተኞች ይልቅ የተማሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉን በግልም ሆነ በቡድን ማህበራዊ መገናኛዎችን ድረገጾችን እና ሌሎች መንገዶችን በመጠቀም በአለም አቀፍ ደረጃ እንዴት ኢትዮጵያን ከወያኔና ከነሱ ተከታይ ከሆነው ሃገር አፍራሽ ኦነግ አንደተከላከሉና አመርቂ ዉጤት አንዳመጡ አይተናል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ባልተማከለ ስርአት ዉስጥ በመገኘቱዋና በተለይም በአማራዉ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የመኖርና ያለመኖር አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ የአለም አቀፉን በተለይም የሃያላን አገሮችንና የጎረቤት አገሮችን ዉስጣዊ ሁኔታ፣ ፍላጎትና አቁዋም በመቃኘት ግንኙነት መፍጠር እጂግ በጣም አስፈላጊ ነዉ።
ዓባይ፣ ዠማ፣ ተከዜና ሌሎች ትልልቅ ወንዞች መነሻቸዉ ሙሉ በሙሉ ከአማራ ምድር በመሆኑ ለጋራ ብልፅግና ሊውሉ እንደሚችሉ በማሳየት የጎረቤት አገሮች ለአማራ ሕዝብ በስልት አጋር እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል፡፡
የአማራ ፋኖ ድርጅቶችን ደህንነት ለመጠብቅ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች
፩. ፋኖን ለመቀላቀል ወይ ለተልእኮ የሚመጣ ሰዉ ሁሉ ማንነቱንና ይዞ የሚመጣዉን መሳሪያ፣ የእጅ ስልክና ሌሎች ነገሮችን ማወቅና እስከሚጣራ ወይም መልእክተኛም ከሆነ ተመልሶ እሰከሚድ እንዲያስረክብ ማድረግ።
፪. ከዉጭም ሆነ ከአገር ቤት ለፋኖ ገንዘብም ሆነ መሳሪያ የሚሰጡ ቡድኖች፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች እርዳታዉን ከመስጠት ዉጭ በፋኖ አሰራር፣ መመሪያና እርእዮተ ዓለም ዉስጥ ጣልቃ እንዳይገቡ ማድረግ።
፫. በየአንዳንዱ የፋኖ ድርጅት ዉስጥ የደህንነት መዋቅር መዘርጋትና የሚጠረጠሩ ጸረ ዓማራ ፋኖ ሰርጎገቦችን ፈጥኖ ማሰናበት።
፬. አመራር ላይ የሚቀመጡ ሰዎች በአካባቢው የሚታወቁና በአቁማቸዉም ሆነ በንቃተ ህሌናቸዉ አስተማማኝ መሆናቸዉን ማርጋገጥ።
፭. ጦሩን የሚምሩት፣ የደህንነትና የመገናኛ (Communication) ፋኖዎች የአካባቢዉ ተወላጅና ማንነታቸዉ የሚታወቅ የአማራ ልጆች መሆናቸዉን ማረጋገጥ።
፮. ከመቶ አለቃ እስከ ሻለቃ ከሻለቃ እስከ ብርጌድ ከዚያም እስከ እዝ ያለዉን ግንኙነት በዲስፕሊንና በሚስጥር ማደርግ።
፯. ጎንደር፣ ሸዋ፣ ጎጃምና ወሎ እያንዳንዳቸዉ በየአካባቢያቸዉ እዝ ከመሰረቱ በሁዋላ አንድ ላይ ሆነዉ አንድ ወጥ የሆነ የዓማራ መከላከያ ኃይል (ዓህመኃ) ወይም በእንግሊዝኛ Amhara People Defence Force (APDF)ን በከፍተኛ ጥንቃቄ መመስረት።