ጋምቤላ ዉስ ጥ እንደገና አለመረጋጋት መንገሱ ተሰማ ! ለብዙ ሺህ አመታት ተፈጥሮን አንግሳ ኮሽ ሳይልባት የኖረች ጋምቤ ወያኔ ኢትዮጵያን በህገ ወጥ መንገድ ከተቆጣጠረ ጀምሮ በከፍትኛ ሽብር ዉስጥ ትገኛለች።
ከዲሴምበር 2003 ጀምሮ ከተካሄደው የወያኔ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሌላ ሰሞኑን ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የታጠቁ የሙርሌ ጎሳ አባሎች የኢትዮጵያን ድንበር አለፈውና ዘልቀው በመግባት ከፍተኛ ጥፋት ካደረሱ በሁዋላ ጋምቤላ ዉስ ጥ እንደገና አለመረጋጋትና ውጥረት መንገሱ ተሰማ። ነዋሪዉ ከቤቱ በመዉጣት ከከተማዉ 17 ኪሎሜትር ላይ የሚገኘውን የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መጠላያን ለማጥቃት ሲተም በፌደራልና በመከላከያ ሰራዊት እንዲቆም መደረጉም ታዉቆአል።
ህዝቡን ያስቆጣው በዚህ ሳምንት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በማለፍ ስደተኞቹ እጅ ቆርጠው አስከሬን ማቃጠላቸው ነው ተብሎአል። በጭካኔ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አስክሬኖች በጫካ ውስጥ ተጥለው መታየታቸውም ተሰምቶአል።
በዚሁ ህዝባዊ ተቃዉሞ ላይ ትናንትና 14 ነዋሪዎች እንደሞቱ ሲታወቅ ባለፈው 15 ኤፕሪል 2016 ሙርሌዎች ባደረጉት ወረራ 208 ሰዎች ገድለው 108 ህጻናትና ሴቶች ፈንግለውና 2000 ከብቶች ዘርፈው መሄዳቸው ሲዘገብ በዚሁ ሽብር የተናሳ ከ21,000 ህዝብ በላይ ከቀየው መፈናቀሉ ታዉቆአል።